በብራዚል እስር ቤት ውስጥ በተነሳ ጠብ 57 ሰዎች ሞቱ

ከአደጋው በኋላ የፖሊስ አባላት የእስር ቤቱን ቅጥር ግቢ ከውጪ ሆነው ሲጠብቁ Image copyright Reuters

ብራዚል እስር ቤት ውስጥ በተነሳ ጠብ ቢያንስ 57 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። ጠቡ የተካሄደው በተቀናቃኝ የወንበዴ ቡድኖች መካከል ነው የተባለ ሲሆን ለአምስት ሰዓታት ያህል ቀጥሎ እንደነበር ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ጠቡ የተፈጠረው ፓራ ግዛት ውስጥ አልታሚራ በተባለ እስር ቤት ውስጥ ሲሆን አንደኛው የወንበዴዎች ቡድን ወደ ሌላኛው የወንበዴዎች ክልል በመሄድ ጠብ መቆስቆሱን ተናግረዋል።

ከሞቱት መካከል አስራ ስድስቱ አንገታቸው ተቀልቶ ቀሪዎቹ ደግሞ በተነሳ እሳት ታፍነው መሞታቸውን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

በጠቡ ወቅት ታግተው የነበሩ ሁለት የእስር ቤቱ ሰራተኞች መለቀቃቸውም ታውቋል።

ብሔራዊ ውትድርና መንፈሳዊ ህይወቱን የነጠቀው ኤርትራዊው ዲያቆን

አምባሳደር ሬድዋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለምን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አላቀረቡም?

እስር ቤቱ የተሰራበት መንገድ እሳቱ በፍጥነት እንዲስፋፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም እስረኞች ታፍነው ሊሞቱ ችሏል።

የእስር ቤቱ አስተዳደር ሁለቱ የወንበዴዎች መካከል ጠብ ሊቀሰቀስ እንደሚችል የሚያስገምት ነገር ቀድሞ እንዳልታየ የተናገሩ ሲሆን እስረኞች ከእሳቱ ለመሸሽ ጣሪያ ላይ ወጥተው ታይቷል።

ማረሚያ ቤቱ 200 ሰው መያዝ እንዲችል ተደርጎ የተገነባ ሲሆን አሁን ግን 309 እስረኞች ይገኙበታል። የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ማረሚያ ቤቲ በእስረኛ ብዛት መጨናነቁን ክደዋል።

የፍትህ ሚኒስትር የዚህ አመፅ ጠንሳሽ ይበልጥ ጥብቅ ወደ ሆነ ማረሚያ ቤት እንደሚዛወሩ ተናግረዋል።

ብራዚል በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያለው እስረኞች የሚገኙባት ሲሆን ይህም በዓለም ላይ ሶስተኛዋ ትልቋ ሀገር ያደርጋታል።

በብራዚል 700 ሺህ እስረኞች ያሉ ሲሆን በእስር ቤት ውስጥም በተደጋጋሚ አመፅ እየተነሳ በርካቶች ሕይወታቸውን ያጣሉ።

በፍጥነት እየመጣ ወደነበረ ባቡር በኤርትራዊው የተገፈተረው ታዳጊ ህይወቱ አለፈ

በግንቦት ወር በአራት እስር ቤቶች በተመሳሳይ ቀን በተነሳ ጠብ 40 እስረኞች መሞታቸው ይታወሳል። በነጋታው ደግሞ 15 ሰዎች በእስር ቤት ውስጥ በተነሳ ጠብ ተገድለዋል።

በ2017 ታህሳስ ወር ላይ 130 ሰዎች በእስር ቤት ውስጥ በተነሳ ጠብ መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ጠቡን ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ ነበር።

የብራዚል ፕሬዝዳንት በእስር ቤቶች ያለውን ቁጥጥር ለማጥበቅ ቃል የገቡ ሲሆን ተጨማሪም ማረሚያ ቤቶች ለመገንባት ያላቸውን እቅድ ተናግረው ነበር።

ነገር ግን እስር ቤቶቹ በክልሎች ቁጥጥር ስር የሚገኙ በመሆኑ ፕሬዝዳንቱ እንዳሰቡት ቀላል ላይሆን ይችላል ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ