የኔይማር የመድፈር ክስ ውድቅ ሆነ

የኔይማር ክስ ውድቅ ሆነ Image copyright Reuters

ብራዚላዊው እግር ኳሰኛ አንዲት ብራዚላዊትን ደፍሯል ተብሎ የቀረበበት ውንጀላ በቂ ማስረጃ ባለመገኘቱ ምክንያት ውድቅ መሆኑን የብራዚል መርማሪዎች አሳውቀዋል።

የሳኦ ፓውሎ አቃቤ ሕግ ቢሮ እንዳሳወቀው ክሱ ውድቅ ሊሆን የቻለው በቂ የሆነ ማስረጃ ባለመገኘቱ ነው፤ ነገር ግን የመጨረሻውን ውሳኔ የማስተላለፍ አቅም ያለው ዳኛው ነው።

ብራዚላዊቷ ሞዴል ናሂላ ትሪኒዳዴ ፓሪስ የሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ኔይማር የመድፈር ወንጀል ፈፅሞብኛል ማለቷን ተከትሎ ነበር ክሱ የተከፈተው።

ኔይማር ጉዳዩን አልፈፀምኩም፤ ሤራ ነው እየተፈፀመብኝ ያለው ሲል ክሱን ሲያጣጥል ከርሟል። የኔይማር አፈ-ቀላጤ ደንበኛዬ ስለጉዳዩ አሁን አስተያየት መስጠት አይችልም ሲል ተደምጧል።

ኔይማር የቀረበበትን ወሲባዊ ትንኮሳ ክስ አጣጣለ

የፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የሆነው ኔይማር ነፃ ነኝ ሲል ናሂላ ጋር የተለዋወጠውን የፅሑፍ መልዕክት በማሕበራዊ ድር-አምባዎች ላይ ከለቀቀ በኋላ ነው ጉዳዩ ትኩረት ያገኘው።

ናሂላ ትሪኒዳድም ቢሆን ስለጉዳዩ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርባ ቃለ-መጠይቅ መስጠቷ አይዘነጋም። ሁለቱ ግለሰቦች እሰጥ-አገባ ውስጥ ሲገቡም የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቃ ነበር።

ፖሊስ ከተንቀሳቃሽ ምስሉ በኋላ ሞዴሏን በስም ማጥፋት ወንጀል ከሷት ነበር።

በርካታ የሕግ ሰዎች ለሞዴሏ ለመቆም አለመስማማታቸውም ተነግሯል።

ከ15 ቀናት በኋላ አቃቤ ሕግ መርምሮ ያቀረበለትን ክስ ሙሉ በሙሉ ውድቅ የማድረግ መብት ያለው ክሱን የያዘው ዳኛ መሆኑም ታውቋል።

ኔይማር ደፍሮኛል ያለችው ሴት ቲቪ ላይ ቀርባለች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ