ድሬ ዳዋ ስለሚገኙት የለገ ኦዳ የዋሻ ሥዕሎች ያውቃሉ?

የለገ ኦዳ ዋሻ
አጭር የምስል መግለጫ የለገ ኦዳ ዋሻ

ከድሬ ዳዋ ከተማ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የለገ ኦዳ ዋሻ ወደ 600 የሚጠጉ ጥንታዊ የዋሻ ሥዕሎች ይገኙበታል። በ1920ዎቹ አካባቢ በተመራማሪዎች ዕውቅና እንዳገኙ የሚነገርላቸው የዋሻ ሥዕሎች ከ7,000 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠሩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

በብዛት በቀይ፣ በቢጫና ግራጫ ቀለም ከተሠሩት ሥዕሎች መካከል የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳ ቁሶች እንዲሁም እንስሳት የሚያሳዩት ይገኙበታል።

"የዘረፉትን ቅርስ በውሰት እንመልስ ማለታቸው ተገቢ አይደለም" ሚኒስትር ሂሩት ካሳው

የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች

ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን?

የድሬ ዳዋ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ባለሙያ የሆኑት አቶ ደረጄ ታደሰ፤ ሥዕሎቹ ጥንት በአካባቢው ይኖሩ በነበሩ ሰዎች እንደተሠሩና፤ የአኗኗር ዘይቤያቸውን እንደሚያሳዩ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ሥዕሎቹ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋም እንደተጋረጠባቸው አቶ ደረጄ ተናግረዋል። ዋሻ ሥር የሚገኙት ሥዕሎች በዝናብ ሳቢያ እየደበዘዙ መጥተዋል። በሰው ንክኪ ምክንያትም የቀድሞ ይዘታቸውን እያጡ ነው።

አቶ ደረጄ እንደሚሉት፤ ቅርሱ በአግባቡ ባለመያዙ የአገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል።

ቅርሱን ከዝናብ ለመከላከል መጠለያ ቢሠራም፤ የበለጠ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ባለሙያው ተናግረዋል። የቢቢሲ ባልደረባ ወደሥፍራው አቅንቶ ካነሳቸው ፎቶግራፎች የሚከተሉት ይገኙበታል።

አጭር የምስል መግለጫ በለገ ኦዳ ዋሻ ከሚገኙት ጥንታዊ ሥዕሎች አንዱ
አጭር የምስል መግለጫ በቢጫና ግራጫ ቀለም ከተሠሩት ሥዕሎች መካከል የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳ ቁሶች እንዲሁም እንስሳት የሚያሳዩት ይገኙበታል
አጭር የምስል መግለጫ የዋሻ ሥዕሎቹ ከ7,000 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠሩ ይነገርላቸዋል
አጭር የምስል መግለጫ በዋሻው ውስጥ ወደ 600 ሥዕሎች ይገኛሉ
አጭር የምስል መግለጫ ሥዕሎቹ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋም ተጋርጦባቸዋል
አጭር የምስል መግለጫ ሥዕሎቹን ከዝናብ ለመከላከል የተሠራው መጠለያ
አጭር የምስል መግለጫ የለገ ኦዳ ዋሻ
አጭር የምስል መግለጫ የዋሻ ሥዕሎቹ በ1920ዎቹ አካባቢ በተመራማሪዎች እውቅና ማግኘታቸው ይነገራል

ተያያዥ ርዕሶች