ከነፍስ የተጠለሉ የድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ዜማዎች

ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ በመድረክ ላይ ሥራዋን ስታቀርብ Image copyright Mekbib Tadesse
አጭር የምስል መግለጫ ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ በመድረክ ላይ ሥራዋን ስታቀርብ

ዘሪቱ ከበደ 'አርተፊሻል' በተሰኘው ነጠላ ዜማ ውስጥ ስሜታችን አርተፊሻል [ሰው ሰራሽ]፣ ምኞታችን አርተፊሻል፣ ውበታችን አርተፊሻል፣ ሕይወታችን አርተፊሻል ስትል ማኅበራዊ ትዝብቷን ታጋራለች።

ድንዛዜ፣ አልበዛም ወይ መፋዘዙ

ነቃ በሉአልበዛም ወይ ማንቀላፋት

ላፊነትን መዘንጋት

ስትል ትጠይቃለች፤ ዘሪቱ በዚሁ ሥራዋ ውስጥ. . .

ድንዛዜ በወሬያለጥቅም ያለ ፍሬ

ድንዛዜ በጭፈራ ያለ ላማ ያለ

ድንዛዜ በከተማሰው ሰው ብቻ እየሰማ ስትል የሰላ ትችቷን ታቀርባለች።

ዘሪቱ በሊቢያ አንገታቸውን በተቀሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተሰማትን ቁጣ በገለፀችበት ነጠላ ዜማዋ ላይ 'ሠይፍህን አንሳ' ስትል አቀንቅናለች።

ሠይፍህን አንሳያበራልሃል ለጠላት መልሱን ያስተምርሃል

ሠይፍህን አንሳ ትረፍ ከበቀል ኃይል ይሆንሃል እንድትል ይቅር፤

ስትል ለበደሉ ይቅርታ ማድረግን ትሰብካለች።

ዘሪቱ የምንኖርበትን ዓለም 'አሁን በብርሃን አይቼሻለሁ' ብላ መጠየፏን በገለፀችበት ሥራዋ፤ የነበረችበትበን የሕይወት መልክና ልክ ስትገልፅ. . .

"ማለለልቤ ማለለ ታለለልቤ ታለለ

ሳተ ከቆመበት ተንከባለለ. . ." እያለች ታንጎራጉራለች።

Image copyright Zeritu Kebede Instagram

"ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በትንሳኤ በዓል ነበር" የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ እናት

ድምፃዊት ዘሪቱ በተለያየ ጊዜ በሠራቻቸው እነዚህ ነጠላ ዜማዎች ማኅበራዊ ትችቷን፣ የሕይወት አቋማን ገልጻለች። 'አርተፊሻል' የተሰኘውና ለአካባቢ ጥበቃ እንደተሠራ የምትናገረው ሙዚቃ፣ 'ሠይፍህን አንሳ' የተሰኘውና በሊቢያ አንገታቸውን በአክራሪ ኃይሎች ለተቀሉት ኢትዮጵያውያን ያቀነቀነችው እንዱሁም 'ውሸታም' የተሰኘ ሙዚቃዋ ውስጥ ዓለምን መጠየፍ ይታያል።

ዘሪቱ ከእኛ ጋር ለመጨዋወት ፈቅዳ ስትቀመጥ ያቀረብንላት ጥያቄዎችም እነዚሁ ሥራዎቿን የተመለከቱ ናቸው። ቃለ መጠይቁን ከመጀመራችን በፊት ዘሪቱ ጠቆር ያለ ማኪያቶ አዛ እንዲህ አወጋን. . .

ቢቢሲ፡ እነዚህ ሦስት ሥራዎች ('አርተፊሻል'፣ 'ሠይፍህን አንሳ'፣ እንዲሁም 'ውሸታም') እርስ በእርሳቸው ግንኙነት አላቸው?

ዘሪቱ፡ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው የኔ መሆናቸው ነው። [ሳቅ] ከዚያ ውጪ ግን ያው እኔ የትኛውንም ሥራ ስሠራ ወይ ከሕይወቴ ነው፤ ወይ ከማየው ነገር፣ ከተነካሁበት ነገር ተነስቼ ነው የምደርሰው። ስለዚህ ከእኔ ጋር ግንኙነት አለው።

መጀመሪያ 'አርተፊሻል' የሚለው ነጠላ ዜማ ሲወጣ ለአካባቢ ጥበቃ ተብሎ አንደተሠራ ተነግሮ ነበር። ነገር ግን ሥራውን ልብ ብሎ ላደመጠውየአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያተኩር አይመስልም።

ዘሪቱ፡ ልክ ነው! መነሻው እንደዛ ነው። በዚያ ሰዓት 'ብሪቲሽ ካውንስል' የክላይሜት [የአየር ጠባይ ለውጥ] አምባሳደር ብሎ ከመረጣቸው አርቲስቶች ውስጥ ድምፃዊ እኔ ነበርኩ። በዚያ ሰዓት 'ኢትዮጵያ አረንጓዴ' የሚባል 'ኢኒሼቲቭ' ከሚካኤል በላይነህና ከመሐመድ ካሳ ጋር ጀምረን ለመንቀሳቀስ እንሞክር ነበር። እና በሆነ መንገድ ግንኙነት አለው [አርተፊሻል የተሰኘው ስራ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር]።

በአንድ የጦር አውድማ ላይ ከወላጅ አባቷ ጋር የተፋለመችው ታጋይ

ግን 'አርት ፕሮሰሱ' ውስጥ የምትረካበትን ነገር ትፈልጋለህ። ስለዚህ 'ብሪቲሽ ካውንስል' ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተያይዞ አንድ ሙዚቃ ይሠራ ብለው 'ኢንቨስት' [ገንዘብ ያወጡበት] ያደረጉበት ፕሮጀክት ነው። ግን ምንድን ነው፤ 'ዳይሬክትሊ' [በቀጥታ] ያንን ጉዳይ ብቻ የሚወክል ሥራ ለመሥራት ተሞክሮ የሚያረካ አልሆን አለ። እና በአጋጣሚ እዚያው 'ፕሮሰሱ' ውስጥ እያለሁ 'አርተፊሻል' የሚለውን ሙዚቃ ፃፍኩት፤ በአጠቃላይ የአካባቢ ጥበቃንም ይመለከታል። ከሁሉም በላይ ግን ተፈጥሮ ውስጥ ሰውም አለ። ስለዚህ ሰውን ጥበቃ [ሳቅ] ላይ የበለጠ የሚያተኩር ሥራ ሊወለድ ችሏል ማለት ነው።

Image copyright Zeritu Kebede Instagram

ወደ አውሮጳ ለመሻገር በስደት ላይ እያሉ በሊቢያ አንገታቸው ስለተቀሉ ወጣቶች የራሽውደግሞ 'ሠይፍህን አንሳ' ይሰኛል። ለዚያ ራ መወለድ አንቺ ውስጥ የነበረው የወቅቱ ስሜት ምን ይመስል እንደነበር እስቲ አስታውሺኝ።

ዘሪቱ፡ ኡ. . . ሠይፍህን አንሳ ከከባድ ስሜት ውስጥ ነው የተወለደው። በዚያ ሰዓት በእነዚያ ወጣቶች ላይ የደረሰው ነገር በጣም ያስፈራ ነበር። በጣም ያስቆጭ ነበር። እልህ ያሲይዝ ነበር። ቁጣ. . . እንዴት ብለህ ነው የምትገልፀው. . . ቁጣ. . . ወገን ናቸው፤ የሰው ልጅም ናቸው። በጣም ተገቢ አይደለም። ስለዚህ በጣም ቁጣ ተሰማኝ፤ በውስጤ። ከዚያ ቁጣ በኋላ ግን የትም ልሄድ አልችልም። ምንም ላደርግ አልችልም። ያ ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ሌላ የድባቴ መንፈስ፤ ስሜት አስከተለ። ያ ደግሞ የኔ ብቻ ሳይሆን አካባቢዬንም ሳይ ብዙዎቻችን ላይ ያየሁት፣ ሀገሪቱም ላይ፣ አየሩም ላይ የነበረው መንፈስ እንዴት ጨፍጋጋ እንደነበር አስታውሳለሁ። እና. . . [በረዥሙ ተንፍሳ] የሆነ ነገር ማበርከት እንዳለብኝ ተሰማኝ።

በአካባቢዬም በዚያ ስሜት ውስጥ አብረውኝ የነበሩ ወንድም እህቶቼ የሆነ ነገር ማካፈል እንዳለብን ተማመንና በዚያ ጉዳይ መፀለይ ጀመርኩ፤ ማሰብ ጀመርኩ። ስቱዲዮ ውስጥ፣ በዚያ ሰዓት ሳነበው የነበረው መጽሐፍ አለ፤ የሪክ ጆነር 'ዘ ቶርች ኤንድ ዘ ሶርድ'፣ የሚል መጽሐፍ፤ እዚያ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ያለውን የሠይፍ ምስል ሳየው መልዕክቱ እንደመጣልኝ ተሰማኝ፤ ገባኝ። ከዚያ ስቱዲዮ ውስጥ ነው 'ዴቬሎፕ' [ስራው የዳበረው] መደረግ የጀመረው።

በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ

ከዚያ ዳዊት ጌታቸው [የሙዚቃ መምህር፣ አቀናባሪና ዘማሪ] ጋር ሄድኩኝ። ዳዊት ጌታቸው ሌላ ጊዜ መዝሙር ነው የሚሠራው፤ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ይህንን ለመሥራት ፈቃደኛ ሆነ። እናም አብረን ልነሠራው ቻልን። እኔም ሆንኩ ምድሪቱ ከነበርንበት ከዚያ ስሜት ውስጥ ተስፋ ይሆናል፤ መፅናኛ ይሆናል መልስ ይሆናል ብዬ ያሰብኩበትንና የተቀበልኩትን መልዕክት ለማድረስ ነው የተሠራው።

ሙዚቀኛ ዳዊትን ስትጠቅሺው ከዚህ በፊት መዝሙር ነው ይሠራ የነበረው አልሽኝ። ይህ ራ መዝሙር አይደለም ብለሽ ነው የምታምኚው?

ዘሪቱ፡ [ሳቅ] ነው፤ መንፈሳዊ ነው። የምልህ መነሻው መንፈሳዊ ነው። መነሻ የሆነኝም መጽሐፍ መንፈሳዊ ነው። 'ሠይፍ' የሚለውም ቃል የእግዚአብሔርን ቃል፣ የእግዚአብሔርን ኃይል፣ የእግዚአብሔርን ምላሽ መወከሉ መንፈሳዊ ነው። ሃይማኖታዊ ግን አይደለም። ያ ነው ልዩነቱ እንጂ መንፈሳዊ ነው።

ከእነዚህ ራዎችሽ በኋላ ደግሞ 'ውሸታም' የሚለውን ራሽን ስታቀርቢ ዘሪቱ ዓለምን እየተጠየፈች ይሆን አልኩኝ? እውነት ዓለምን እየተጠየፍሽ ነው?

ዘሪቱ፡ 'አርተፊሻል'፣ ከሁለቱ ዘፈኖች በተለየ በቀጥታ መንፈሳዊ አይደለም። ለምን? መነሻው ማኅበራዊ ትዝብት ነው እንጂ ከመንፈሳዊነት የመነጨ አይደለም። መንፈሳዊ አይደልም ማለት ግን አይቻልም። ለምን? እንድንሆን የሚመክረው፣ ወይም አልሆንም ብሎ የሚወቅሰው ማንነት፣ እንግዲህ እኔ የማምነው አምላክ፣ እንድንሆንለት ሽቶ በአምሳሉ ከፈጠረው ማንነት ውጪ ሆነናል ነው። ለምን? በዚያ ማንነት ውስጥ ያለ ሰው አካባቢውን ይጠብቃል፤ ከሰዎች ጋር አብሮ ይሆናል። በስስት የተያዘ አይሆንም፤ ስለዚህ ሆነናል የተባሉት ነገሮች ሁሉ ሰው ስንሆን ከታለመልን፣ እንድንሆን ከታሰበልን ውጪ ሆነናል፤ ስለሆነም እንደ መንፈሳዊ መልዕክት 'ኳሊፋይ' [ያሟላል] ያደርጋል ብዬ አስባለሁ። መነሻው ግን አይደለም። ሠይፍህን አንሳና ውሸታም ግን ከመንፈሳዊ ሕይወትና በቀጥታ ከመንፈሳዊ ማንነት ጋር የተገናኙ ናቸው ለእኔ።

እና ዓለምን እየሸሽ ነው?

ዘሪቱ፡ [ፈገግታ] ያው ከዓለም ወዴት ይኬዳል [ሳቅ] ዓለማዊ አለመሆን ግን ይቻላል። የዓለም ውሸት፣ የዓለም ሽንገላ፣ ባታለለኝ ወቅት የጻፍኩት ነው። ባለማወቅ የምንሆናቸው ነገሮች አሉ። ካወቅን በኋላ ደግሞ ከእኛ የተሻለ ሲጠበቅ፣ መንገድ አሳይ መሆን ሲጠበቅብን፣ በተላላነት ተይዘን [ፈገግታ] እንደተሞኘን ሲገባን [ፈገግታ] ተመልሰን የማውቀውን! ይሄንን? ምን ነካኝ? ብለን የዓለምንና የገዢዋን ሽንገላ ለማጋለጥና ከዚህ በኋላ አንስትም የሚለውን [ሳቅ] መልዕክት ለማስተላለፍ ነው።

በፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቱ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊ ህይወቱ አለፈ

[ያዘዘችው ጠቆር ያለ ማኪያቶ መጥቶ ጭውውታችንን ለአፍታ አቋረጥን. . . ]

በስምሽ ከተሰየመው አልበምሽ ሌላ ባሉት ከእነዚህ ሦስት ስራዎችሽ ውጪ፣ 'አዝማሪ ነኝ' የሚውም ራሽን ስንመለከት በራዎችሽ የሕይወት አቋምሽን እየተናገርሽና እያስቀመጥሽ ነው የምትሄጂው ማለት እንችላለን?

ዘሪቱ፡ ልክ ነው፤ እንደዚያ ነው። የመጀመሪያው ሥራዬ [ዘሪቱ አልበም] በወቅቱ የነበረኝ ማንነት ነው። በማንነቴ ሳድግ፣ መንፈሳዊነት በውስጤ ማደግ ሲጀምር፣ በዚያ መንገድ እያደግሁ ስመጣ ወይንም ደግሞ በዚያ መንገድ መጓዝ ስጀምር፤ ያው ያንኑ የሚመስል ነገር ነው የሚወጣኝ። ስለዚህ ከአሁን በኋላም ሕይወቴን የሚመስል፣ ያለሁበትን ቦታ የሚመስል ሥራ ነው ከእኔ የሚወጣው።

Image copyright Zeritu Kebede Facebook page
አጭር የምስል መግለጫ ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ

ስለዚህ ከአሁን በኋላ እየራሽ የምትቀጥይው የሕይወቴ መርሆዎች ናቸው የምትያቸውን ብቻ ነው ማለት ነው?

ዘሪቱ፡ በፊትም እንደዛ ነው። [ሳቅ] ምንም አዲስ ነገር አይደለም። ለምን? እውነት ለኔ፣ ከመጀመሪያውም ቢሆን ጽሁፍም ሆነ ሙዚቃ፣ እውነትና ራሴን፣ ሕይወቴን፣ ታሪኬንና 'ኤክስፒሪያንሴን' [ልምምዴን] ከማካፈል ጋር የተገናኘ ነው። ስለዚህ ማንነቴ በሚሄድበት አቅጣጫ፣ ሥራዬም እየተከተለ ይሄዳል። ለምን? የሙዚቃ ስራን በሌላ መንገድ አላውቀውም። ወይንም በሌላ መንገድ ላበረክት የምችለውን፤ በጽሑፍም ሆነ በፊልም ሥራም ይሁን የማምንበትንና የሚመስለኝን፣ ለሰው ይጠቅማል ብዬ የማስበውን ወይንም መወከል አለበት ብዬ የማስበውን ማኅበረሰብ፤ ሆን ብዬና መርጬ ነው የማደርገው። እንጂ በዚህ አቅጣጫ የሆነ ነገር ቢፃፍ ገበያ ላይ የሆነ ነገር ያመጣል፣ ወይም ለኔ የሆነ ክብር ይጨምራል በሚል አይደለም። ስለዚህ ከሕይወቴ በማካፈል ነው የምቀጥለው። መርሄንም ይሁን፣ 'ኤክስፒሪያንሴንም' ይሁን፣ አስቂኝ ገጠመኝም ይሁን፣ ጥበብ ስለሆነ ሁሉንም ሳጥን ሰርተን አናስቀምጠውም። አንዳንዱ ሥራ በማንጠብቀው ሁኔታ ይመጣል።

አልበምሽ ውስጥ የማይረሱ አገላለጾች እና የቋንቋ አጠቃቀሞች አያለሁአሁን የምናወራባቸው ራዎች ላይ ግጥሞቹን ብንመለከት ጠንካራ ናቸው። ግጥምና ዜማ ላይ በጎ ተጽዕኖሳረብሽ ባለሙያ አለ?

ዘሪቱ፡ እ. . . ማንንም ሳላይ ነው መጻፍ የጀመርኩት። መጻፍ የጀመርኩት ከልጅነቴ ስለሆነ። በልጅነት ውስጥ ዝም ብዬ በዜማም ይሁን በግጥም ራሴን መግለጽ የጀመርኩት በተገኙ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ ነው። በመጀመሪያ ወደ ሙዚቃ ለመሳቤ እነሴሊንዲዮን፣ ማሪያ ኬሪ፣ ዊትኒ ሂውስተን ምክንያት ናቸው። ወደ የሙዚቃ ግጥም አጻጻፍ ስንመጣ ትሬሲ ቻፕማን፣ ቦብ ማርሌና አላኒስ ሞርሴት መነሻዎቼ ናቸው። እነዚህ ሦስት አርቲስቶች ለዘፈን ጽሁፍ ወይም ደግሞ በዘፈን ውስጥ ለሚነገሩ መልእክቶች መነሻዬ ናቸው። አንድን ሰው፣ አንድን አርቲስት ያገኘሁት ያህል፤ 'አይደንቲቲውን' [ማንነቱን]፣ መልዕክቱን፣ ጉዞውን፣ ከለሩን፣ ከልጅነቴ ጀምሮ እንዳጣጥም እና እንዲገባኝ አድርገዋል። በተለይ አላኒስ ሞርሴት እኔ የምሞክራቸው ነገሮች 'ሴንስ' [ትርጉም] እንዲሰጡ ያደረገች አርቲስት ናት። እና እነዚህ ናቸው የመጀመሪያዎቹ [ተጽዕኗቸውን ያሳረፉብኝ]!

ከዚያ በኋላስ?

ዘሪቱ፡ ከዚያ በኋላ በራሴ መንገድ ነው የሄድኩት።

ግጥሞችሽን አይተው 'እነዚህ ለዘፈን አይሆንም' ያሉ ነበሩ?

ዘሪቱ፡ እ. . . [ትንሽ አሰብ አድርጋ] አይ እንደዚያ ሳይሆን፣ እንደውም በመጀመሪያዎቹ ስቱዲዮ ውስጥ በነበርኩባቸው ጊዜያት . . . በጣም ቀላል ናቸው። ጠንከር ያለ የአማርኛ ግጥም መልክ የላቸውምና አይሆኑም ወይም አያስኬዱም የሚሉኝ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ስላልሰሟኋቸው እግዚአብሔር ይመስገን ። [ረዥም ሳቅ]። ግን ኤሊያስ በተለየ መልኩ 'ኢንካሬጅ' [ያበረታኝ] ያደርገኝ ነበር።

Image copyright Zeritu Kebede Instagram

አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ?

ዘሪቱ፡ አዎ ኤሊያስ መልካ። እንደውም እንደዚህም ይቻላል ለካ። እንደዚህ ነው መሆን ያለበት። ቀላል ሆኖ፣ ከዜማ ጋር ተዋህዶ፣ ሰው 'ኢንጆይ' እንዲያደርገው [ዘና እንዲልበት] ብሎ 'ኢንከሬጅ' አድርጎኛል [አበረታቶኛል]። በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት።

ኤሊያስን ካነሳን አይቀር፣ ኤሊያስ አለ፣ በሕይወት የሌለው እዮብ አለ፤ ሌሎችም አሁን ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው [በእናንተ ክበብ ውስጥ ያሉ] የሙዚቃ ባለሙያዎች አሉ። እነዚህን የሙዚቃ ሙያተኞች ስናይየዘመንሽን ሙዚቀኞች በራዎ በሚገባ ወክያለሁ፣ ገልጫቸዋለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ?

ዘሪቱ፡ [በረዥሙ ተንፍሳ] እ. . . እኔ በጣም ግለሰባዊ ነኝ መሰለኝ። [ሳቅ] የሆነን ወገን መወከሌ አይቀርም። ግን ከምንም በላይ እውነትን እና የራሴን ጉዞ እንደወከልኩ፤ በዚያ ውስጥ ደግሞ ብዙዎች የሚወዱህ ሰዎች በሆነ ያህል እንደተወከሉ የሚያስቡ ይመስለኛል። ስለዚህ እነርሱንም የወከልኩና ያሰማሁ ይመስለኛል።

ለምንድን ነው እንደዚያ ያልኩትበወንጌላውያን አማኝ ሙዚቀኞች ዘንድ የጦፈ ክርክር ነበር። ሙዚቃና ሙዚቀኝነትን፣ዓለማዊነትንና መንፈሳዊነትን በተመለከተ። በኋላም የዮናስ ጎርፌ 'ቤት ያጣው ቤተኛ' የተሰኘ መጽሐፍ ታትሞ ተነቧል። ይህ የሚያሳየን ከወንጌላዊያን አማኞች የተገኙ ሙዚቀኞች፣ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ያላቸውን ስፍራ ለማፅናት፣ እዚህ ጋር ነው ስፍራችን ማለትን ያየሁ ስለመሰለኝ ነው። በዚያ ወቅት ደግሞ አንቺ ራዎችሽን በዚህ መልክ ስታቀርቢ እነዚህን ወገኖች ወክላ ይሆን የሚል ጥያቄ አድሮብኝ ነው?

ዘሪቱ፡ [ከረዥም ዝምታ እና ማሰብ በኋላ]. . . ብዬ አምናለሁ። ተወክለው ከሆነ እነርሱ ያውቃሉ ይመስለኛል። የአንድ መንፈሳዊ ሰው ሕይወት እኮ አይከፋፈልም። አንድ ሰው መንፈሳዊ ነኝ ካለ በማንኛውም ጊዜ በዚያ ማንነት ውስጥ ነው ሊሆን የሚገባው። በጨዋታም ጊዜ፣ በሥራም ጊዜ፣ በፀሎትም ጊዜ፣ በሁሉም ጊዜ በመንፈሳዊ ማንነት ውስጥ ነው መቆየት ያለበት። ያ መንፈሳዊ ማንነት ደግሞ የሆነ ኃይማኖታዊ መልክ አይደለም። መልካምነት፣ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ ሰላም፣ በጎ የሆነ ነገር ሁሉ መንፈሳዊ ነው ብሎ መደምደም ባይሆንም፤ ምክንያቱም ማስመሰልም ስላለ። ግን ሥራዬ መንፈሳዊ ካልሆነ፣ ወይ ከመንፈሳዊነት የሚያጎለኝ ከሆነ፣ ከመንፈሳዊነት የሚጋጭ ከሆነ፣ ባላደርገው ነው የሚመረጠው። ስለዚህ እንደማይጋጭ እያመንኩ ነው እያደረኩት ያለሁት።

ዘሪቱ ራሷን ከሙዚቃ ውጪ በምን በምን ትገልፃለች?

ዘሪቱ፡ ፋሽን ደስ ይለኛል። 'ስታይል' መቀየር ያዝናናኛል። ልንዝናናም ደግሞ ይገባናል። ቁም ነገር የሆኑት ነገሮች እንዳሉ ሆነው፣ በምድር ላይ እስካለን ድረስ የሚያዝናኑን ነገሮች አሉ። ጉዳት የለውም። ስለዚህ በእርሱም ራሴን 'ኤክስፕረስ' አደርጋለሁ [እገልጻለሁ]። በተሰማኝ ጊዜ። ሙሉ በሙሉ በእዚያ ማንነት ውስጥ የምኖር ሰው አይደለሁም። ዝም ብዬ ስዘንጥ የምኖር ሰው አይደለሁም። [ሳቅ] ዘናጭ አይደለሁም። የሙሉ ጊዜ ዘናጭ [ረዥም ሳቅ]. . .

ልክ አሁን ስንገናኝ እንደለበስሽው ቀለል ያለ አለባበስ፣ ጅንስ ሱሪ በሸራ ጫማ በጃኬት?

ዘሪቱ፡ አዎ . . . ብዙ መታየትም አልወድም። ግን አንዳንዴ ደግሞ ያኛውም ጎን አለኝ። ለወጥ ብሎ፣ ተጫውቶ. . . እንደጨዋታ ነው የማየው። መለስ ብሎ ደግሞ ወደ ተረጋጋው የዘወትር መልኬ [ሳቅ] በእሱ እጫወታለሁ። ባለኝ በሚያስደስተኝ ሁሉ ራሴን 'ኤክስፕረስ' አድርጌ [ገልጬ] ሰዎችን ፈገግ አድርጌ፣ አዝናንቼ፣ አካፍዬ ማለፍ ነው የምፈልገው።

ትርፍጊዜሽን በምን ማሳለፍ ነው ደስ የሚልሽ?

ዘሪቱ፡ የሚያስደስተኝ ነገር ወይ ከሥራዬ ጋር የተያያዘ ነው ወይ ከቤተሰቤ ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህ ትርፍ ጊዜ ቢኖረኝም ያንኑ የሚያስደስተኝን ነገር አደርጋለሁ። ወይ አነባለሁ፣ ወይ አጠናለሁ፣ ወይ ከልጆቼ ጋር እሆናለሁ። ፊልም እመለከታለሁ። በሙዚቃ እዝናናለሁ። ትርፍ ጊዜዬም ሥራዬም ተመሳሳይ ነው። ይዘቱ ከቤተሰቤ ራቅ ያለ ነገር አይደለም። በአጠቃላይ ትርፍ ጊዜ ነው ያለኝ ማለት ነው። [ሳቅ]

Image copyright Mekbib Tadesse
አጭር የምስል መግለጫ ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ ከሦስት ልጆቿ ጋር

ለሁለተኛአልበምሽመዘግየት ምክንያት የሆነውእናት መሆንሽ ነው?

ዘሪቱ፡ አይደለም። በፍፁም ምንም ግንኙነት የለውም። እንዲሁ የሕይወት ጉዞ፣ ዝግጁ አለመሆን፣ ከራስ ማንነት መሠራት፣ መስተካከል፣ ከዚያ ያንን መፈለግ፤ ከዚያ ትክክለኛው ለጥበብ ምቹ የሆነ 'ኢነርጂ' [ኃይል]፣ 'ፓርትነርሺፕ' [አጋር] አለመመቻቸት፣ ወይ ጊዜው አለመሆን፣ ያ ያ ነው። አብዛኛው ጊዜዬ በስራ ነው የሚያልፈው። ብዙ ሥራም እሠራለሁ። በፊልምም ብዙ ሠርቻለሁ። እናትነት በጣም 'ቢዚ' [ባተሌ] አድርጎኝ አይደለም። [እናትነት] ጊዜ ቢወስድም ሙዚቃን ለመሥራት ይኼን ሁሉ ዓመት የሚያስቸግር አልነበረም። ምክንያቱ እርሱ አይደለም።

ስንት ፊልሞች ላይ ተሳተፍሽ?

ዘሪቱ፡ ከ'ቀሚስ የለበስኩለት' በኋላ [ይህ የራሷ ድርሰት ነው]፣ የቅድስት ይልማ ሥራ የሆኑት 'መባ' እና 'ታዛ' ላይ በትወና ተሳትፌያለሁ። ከዚያ አሁን በቅርቡ የወጣ 'ወጣት በ97' የሚል ፊልም አለ። አሁን ደግሞ በቅርቡ የሚወጣ 'ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ' የሚል የዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ፊልም አለ። እስካሁን እነዚህ ናቸው።

ልክ እንደ ሙዚቃሽ በፊልሙም እኔ የምወክላት እንዲህ አይነት ገጸ ባህሪ መሆን አለባት ትያለሽ?

ዘሪቱ፡ አዎ። እንደዚያ ባይሆን መሳተፌ አስፈላጊ አይደለም። የምትመስለኝን፣ ልትወከል ይገባታል ብዬ የማምነውን፣ ብትታይ ይገባታል ብዬ የማምነውን ገፀ ባህሪ ወይም ላውቃት፣ መስያት ወይም ሆኛት፣ እርሷና አካባቢዋን ልወቅ ብዬ የመረጥኳትን ገፀ ባህሪ ወይንም ደግሞ ሊተላለፍ ይገባዋል የምለው መልእክት ካልሆነ በስተቀር ተሳትፎዬ ምንም ጥቅም የለውም። ስለዚህ እስካሁንም የተሠሩት ሁሉ እንደዚያ ናቸው።

ከአሁን በኋላ ያንቺ ድርሰት የሆነ ፊልምእንጠብቅ ወይስ የሌሎች ራዎች ላይ ብቻ ነው የምትሳተፊው?

ዘሪቱ፡ አስባለሁ። ግን ያው በመጀመሪያ የፊልም ሙከራዬ በጣም ብዙ ነገር ውስጥ ስለተሳተፍኩ ደከመኝ [ሳቅ]። ጥንካሬዬ በነበሩት ነገሮች በጣም ጠንካራ ነገር ባመጣም፤ ገና ያልተማርኳቸውና ያላወቅኳቸው 'ኤክስፒሪያንስ' [ልምድ] የሚያስፈልጉኝ ነገሮች ነበሩ። ስለዚህ እነርሱን ለማግኘትና ለመለማመድ ስል ነው በተለያዩ ሰዎች ፊልም ውስጥ ተሳታፊ የሆንኩት። ጥሩ ልምድ እንዳለኝ አምናለሁ። ሀሳቦች አሉኝ። እንደውም ከዚህ በኋላ የማስበው የራሴን 'አይዲያ' [ሀሳብ]፣ የራሴን መልዕክት ብሠራ ነው። ግን መልካም ሆኖ የሚያስደስትና የሚጠቅም ሥራ ከመጣ የሌሎችን ሰዎችም እሠራለሁ።

'ዘሪቱ' የተሰኘ አልበምሽ እንደወጣከነ ሄኖክ መሀሪ ጋርትልልቅየሙዚቃ ድግሶች አዘጋጃችሁ'ጉዞ ዘሪቱ' የተሰኘ።እንደዚህ አይነት ቋሚ የሆነ የሙዚቃ ኮንሰርት የማዘጋጀት ሀሳብ የለም?

ዘሪቱ፡ አለ። ከአዲስ አበባ ወጥቶ በክልል ከተሞች ሥራዎችን ማቅረብ በጣም ነው የሚያስደስተኝ። ናፍቆት ስላለ ምላሹ በጣም አርኪ ነው። በመጀመሪያም ያደረግነው እርሱን ነው። መቼም የማይረሳን ጊዜና ታሪካዊ ልምድ ነው የሆነው። ከዚህ በኋላም ልናደርግ እናስባለን። ግን እንደሱ አይነቱን ነገር በሰፊው ለማድረግ ከአዲስ አልበም በኋላ ቢሆን የተሻለ እንደሚሆን በማመን [ሳቅ] ነው ያላደረግነው። ግን ባለንበት አካባቢ፣ በተመቻቸ ጊዜ ሁሉ እንጫወታለን።

አዲስ አልበም መቼ ይወጣል?

ዘሪቱ፡ ፀልይልኝ። [ረዥም ሳቅ] እየተሰራ ነው ባለቀ ጊዜ. . .

አልበምሽ ወጥቶ አንቺ ራዎችሽን በምታቀርቢበት ወቅት 'ያምቡሌ' በጣም ዝነኛ ነበር። ዝግጅትሽን በምታቀርቢበት ስፍራ ላይ በተፈጠረ ጉዳይ ስምሽ በተደጋጋሚ ተብጠልጥሎ ነበር። ያኔ የተፈጠረውምን ነበር?

ዘሪቱ፡ ምንድነው የሆነው? ከተወራው የተለየ ነገር የሆነ አይመስለኝም። አሁን በደንብ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ 'ዶሚኔት' [የተቆጣጠረው] ያደረገው 'ሳውንድ' [ድምፅ] ሲመጣ 'ያምቡሌ' ቀዳሚው ሥራ ነበረ። በሙዚቀኞች አካባቢ እንደ ጨዋታ እያደረግን ብዙ እናነሳው ነበረ። እኔ ደግሞ በዚያን ሰዓት ልሠራበት እየተዘጋጀሁ በነበረበት የፕላቲኒየም ክለብ፣ እየተዘጋጀሁበት የነበረው ሥራ 'ያምቡሌ'ን የማይመስል ወይንም ከኔም ሥራ ወጣ ያለ፣ ከ'ፖፑላር' ም ሥራ ወጣ ያለ፣ እንደ ጥበብ ሥራ ብቻ ልታጣጥመው የምትችል፣ ብዙ የተደከመበት፣ በጣም የተዋበ፣ አሁን ባለንበት ወቅት የተሻለ ተቀባይነት ያገኝ ነበር። እርሱን የሚመስሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ሰው 'ኢንጆይ' ያደረጋቸው። ያኔ ግን እሱ ቅንጦትና ቅብጠት ነበር የሚመስለው እንጂ . . .

በፈረንጅ "ናይት ክለብ" ጉራግኛ ሲደለቅ

በፒያኖ የታጀበ ማለት ነው?

ዘሪቱ፡ በፒያኖ ብቻ አይደለም። ፒያኖ፣ አፕ ራይት ቤዝም አለ። ፒያኖም አፕራይት ቤዝም ከሆነ ከዓመታት በኋላ ነው መድረክ ላይ የወጡት። በኢትዮጵያ 'ፖፑላር' ሙዚቃ ውስጥ ብዙ ጊዜ የማንሰማቸው መሣሪያዎች፣ ለስለስ ያለ፣ 'ሴትአፑ'ም ምኑም ወጣ ያለ ነበር። ያሰብነው ነገር በጣም እንደሚያምር ስላወቅን ምላሹን ለመቀበል ከበደን መሰለኝ። ያው በልጅነትና ባለማወቅ ውስጥ የተመልካቹ ጥፋት እንዳልሆነ [ለመረዳት አልቻልኩም ነበር]። በእርግጥ በትክክል 'ፕሮሞት' እንዳልተደረገ [እንዳልተዋወቀ] የተረዳሁት ቆይቼ ነው። ስለዚህ የመጡት ሰዎች ጥፋት አይደለም። በወቅቱ 'እንዴት ይሄ አይገባቸውም' በሚል ነው እንጂ፤ ቢያውቁና ቢጠብቁ የሚፈልጉት ሰዎች ይመጡ ነበር። እና በአንድ መንገድ ለጥበብ የተደረገ ትግል ስለሆነ ያቺን ልጅ እኮራባታለሁ። በሌላ ወገን ደግሞ ያለመብሰልና ያለማስተዋል ውጤት ነው። ለዛ ነው እንግዲህ 'ይሄ ካልገባችሁ እንግዲህ ያው 'ያምቡሌ' ይሁንላችሁ' ብላ ያለፈችው።

'ያቺኛዋ' ስትይኝ አሁን ያቺ የድሮዋ ዘሪቱ የለችም እያልሽኝ ነው?

ዘሪቱ፡ መስዋዕትነት ነው እና ያቺኛዋን ዘሪቱም ነኝ። ግን [አሁን] እንደዛ የማደርግ አይመስለኝም። ማንን መቆጣት እንዳለብኝ የማውቅ ይመስለኛል።

ሰሞኑን እያነበብሽ ያለሽው መጽሐፍ አለ? ካለ ምንድን ነው?

ዘሪቱ፡ ኦ መጽሐፍ ነው፤ ይገርምሀል አንድ ጓደኛዬ ይህንን መጽሐፍ ሰጠኝና [በቀኟ በኩል ካስቀመጠችው ቦርሳዋን ከፍታ ከመጽሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ ደብተሯ ጋር አብሮ ተቀምጦ የነበረ መጽሐፍ በማውጣት] 'ዘ ግሬተስት ፖወር ኢን ዘ ወርልድ' ይላል። የካትሪን ኩልማን መጽሐፍ ነው። እርሱን ነው እያነበበብኩ ያለሁት። አሁን እየተነበበ ያለው ይህ ነው። [ሳቅ]

ሰሞኑን የምታደምጪውስ ሙዚቃ ምንድን ነው?

ዘሪቱ፡ ሰሞኑን ምንድን ነው የማዳምጠው? [እንደማሰብ አለችና]. . . ብዙ መዝሙር እየሰማሁ ነው። ታሻ ኮምስ የምትባል ዘማሪ አለች። እርሷን በጣም [እየሰማሁ ነው]። ኢሊቬሸን ወርሺፕ እነርሱንም በጣም እሰማለሁ። አሁን የዘሩባቤል አልበም ወጥቷል። እርሱንም እየሰማሁ ነው። [ሳቅ]. . .

ለአንቺ አዲስ ዓመት የሚሰጠው ስሜት ምንድን ነው?

ዘሪቱ፡ አዲስ ዓመት ደስ ይለኛል። 'ኢንከሬጅመንት' [ማበረታታት]፣ ተስፋ፣ መለስ ብሎ 'ሪፍሌክት' አድርጎ [መለስ ብሎ መቃኘት]፣ ያለፈውን ዓመት ጉዞ፣ 'ፕሮግረስ' [ለውጥ]. . . ያው ሁሉም ነገር በዓመት ባይከፋፈልም፤ የሕይወት ጉዞን እንዲሁ ለማየት ግን ደስ ይላል። በአዲስ ተስፋ በደስታ የምቀበለው ጊዜ ነው። አንዳንዴ በዓመት ውስጥ ብዙ አዲስ ዓመቶች እናሳልፋለን። [ሳቅ] ሁሌ ዓመት አንጠብቅም። ግን 'ኢንጆይ' አደርገዋለሁ።

ለአድናቂዎችሽ የአዲስ አመት መልዕክት አለሽ?

ዘሪቱ፡ ሰላም ይሁኑ! ሰላም ይሁንላቸው! ይብዛላቸው! ከራሳቸው ጋር መሆን፣ ለሰው መሆን ይሁንላቸው! ደስታ ይብዛላቸው! ፍቅር ይብዛላቸው!

የምትወጂው ጥቅስ የቱ ነው?

ዘሪቱ፡ የምወደው ጥቅስ የቱ ነው? [አሰብ አድርጋ]. . . በሕይወቴ ውስጥ በጣም ብዙ ጥቅስ ከማስተናገዴ የተነሳ [ረዥም ሳቅ] አሁን አልከሰት አለኝ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ