"የለቀቅኩበትን ምክንያት ለወደፊት አሳውቃለሁ" የትራምፕ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ

ጆን ቦልተን Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ጆን ቦልተን የትራምፕ ሦስተኛው ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ነበሩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ተገዳዳሪ' ነበሩ ካሏቸው የብሔራዊ ደህንነት አማካሪያቸው ጆን ቦልተን ጋር "በጣም ሳይስማሙ" መቆየታቸውን ተናገሩ።

"ጆን የሥራ መልቀቂያ እንዲያስገባ ጠይቄው ነበር፤ ዛሬ ማለዳ አስገብቷል" ብለዋል ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው። አክለውም በሚቀጥለው ሳምንት አማካሪያቸውን የሚተካ ሰው እንደሚሾሙ ገልፀዋል።

ጆን ቦልተን ሥራቸውን መልቀቃቸውን ገልፀው፤ የለቀቁበትን ምክንያት ወደፊት ለማሳወቅ ቃል ገብተዋል።

መምህራንን ተክቶ ያስተማረው ወታደር እየተወደሰ ነው

ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ከአፍጋኒስታን እስከ ኢራን ድረስ ባሉ በርካታ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ አይስማሙም ነበር።

ቦልተን ከ2018 ሚያዚያ ወር ጀምሮ በአማካሪነት ያገለገሉ ሲሆን፤ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ሦስተኛው የብሔራዊ ደህንነት አማካሪም ነበሩ። ከእርሳቸው ቀደም ብሎ ማይክ ፍሊን እና ኤች አር ማክ ማስተር በቦታው ላይ ተሹመው ነበር።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ላይ የብሔራዊ ደህንንት አማካሪያቸው መሰናበትን እንዳሳወቁ፤ ቦልተንም ወደ ትውተር ገፃቸው ጎራ ብለው ስለ ሁኔታው የራሳቸውን ሃሳብ አስፍረዋል።

ቦልተን የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ገልጠው፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን "ነገ እንነጋገርበት" እንዳሏቸው አስፍረዋል።

2011፡ በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት

ዜናው ይፋ እንደሆነ ለዋሺንግተን ፖስቱ ጋዜጠኛ ሮበርት ኮስታ፤ "ወደፊት ስለሁኔታው እገልጣለሁ" እና እጅጉን የሚያሳስበኝ የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ነው" በማለት መልዕክት ልከውለታል።

ቦልተን ሥራ መልቀቃቸው ከመነገሩ ሁለት ሰዓት አስቀድሞ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ እና ከግምጃ ቤት ፀሐፊው ስቲቭን ምኑቺን ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ በዋይት ሐውስ ለመስጠት ቀጠሮ ተይዞ ነበር።

የእርሳቸውን ስፍራ በጊዜያዊነት የያዙት ምክትላቸው የነበሩት ቻርልስ ኩፐርማን መሆናቸውን ከነጩ ቤተ መንግሥት ለቢቢሲ ተገልጧል።

ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት ከሆነ ፕሬዝዳንት ትራምፕን የሚያማክረው የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ በቦልተን የሥልጣን ዘመን በዋይት ሐውስ ተነጥሎ ብቻውን ቆሟል።

ከዚህ ቀደም በትራምፕ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ላይ የነበሩና ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ ግለሰብ ለቢቢሲ እንደገለፁት " ቦልተን ከሌላው የዋይት ሐውስ ተነጥለው ብቻቸውን ይንቀሳቀሱ ነበር"

እንደ ግለሰቡ ከሆነ ሚስተር ቦልተን ስብሰባዎችን አይካፈሉም፤ የሚከተሉትም የራሳቸውን ሥራዎች ብቻ ነበር።

በስህተት ገቢ የተደረገላቸውን 3 ሚሊዮን ገደማ ብር የተጠቀሙት ጥንዶች ክስ ተመሰረተባቸው

የዋይት ሐውስ ባለስልጣን የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት " ቦልተን ራሳቸው የሚያስቀድሟቸው ጉዳዮች ነበሩ። ፕሬዝዳንቱን "የትኞቹ ጉዳዮች እንዲቀድሙ ይፈልጋሉ በማለት አይጠይቁም" ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ ግለሰብ ለሲቢኤስ እንዳሉት "የራሳቸው ቃል ካልሆነ ዓለም ያልፋል" ሲሉ ይህ ጉዳይ በዋይት ሐውስ ውስጥ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ የበርካቶችን ደም ማፍላቱን ይገልፃሉ።

የቦልተንን መልቀቅ ተከትሎ ኤች አር ማክማስተር እንዲተኳቸው ንግግር መጀመሩን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ምንጮች አረጋግጠዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ