ሩዋንዳ በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ተቀብላ ልታቆይ ነው

በሊቢያ፣ ትሪፖሊ የሊቢያ መንግሥት ስደተኞችን በሚያቆይበት ጣቢያ ደጃፍ ቆመው Image copyright Getty Images

ሩዋንዳ በሊቢያ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማማች።

የሩዋንዳ መንግሥት፣ የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች ኤጀንሲ (ዩ. ኤን. ኤች. ሲ. አር.) እና አፍሪካ ሕብረት ትናንትና ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይፋ አድርገዋል።

የመጀመሪያዎቹ 500 ሰዎች በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በአውሮፕላን ወደ ሩዋንዳ እንደሚጓጓዙ ተናግሯል።

መምህራንን ተክቶ ያስተማረው ወታደር እየተወደሰ ነው

በዚህ ቡድን ውስጥ ሕፃናት፣ እና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶች እንደሚካተቱበት የተገለጠ ሲሆን አብዛኞቹ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ የሄዱ ስደተኞች ናቸው ተብሏል።

በርካታ ስደተኞች በየዓመቱ በሜዲትራኒያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር በማሰብ ወደ ሊቢያ ያመራሉ።

በባህር ወደ አውሮፓ ለመሻገር ያልተሳካላቸው ግለሰቦች በስደተኛ ማቆያ ውስጥ እንዲቀመጡ ይደረጋሉ፤ እንደተባበሩት መንግሥታት ከሆነ 4700 ግለሰቦች ከፍተኛ ስጋት ካንዣበበባቸው ከእነዚህ ማቆያዎች በፍጥነት ወደ ሌላ ስፍራ መጓጓዝ አለባቸው።

የጃማል ኻሾግጂ አገዳደል በዝርዝር ይፋ ሆነ

ሩዋንዳ ስደተኞች ለመቀበል መጀመሪያ የተስማማችው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017፣ ሲ.ኤን.ኤን. በሊቢያ ስደተኞች ለባርነት ጨረታ ቀርበው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ከለቀቀ በኋላ ነበር።

የሩዋንዳ የስደተኞች ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ጀርሜይን ካማዪሬሳ ሀገራቸው ስደተኞችን ለመቀበል ገንዘብ ተቀብላለች መባሉን አስተባብለው ነበር።

Image copyright Getty Images

"ሰብዓዊ ተግባር ነው" በማለት በኪጋሊ ለጋዜጠኞች የተናገሩት ሚኒስትሯ አክለውም "ማንኛውም አፍሪካዊ ተመሳሳይ ተግባር ለመፈፀም መስማማት አለበት። ሩዋንዳ ገንዘብ ተቀብላለች የሚሉ አካላት ጋር አልስማማም"ሲሉ ተደምጠዋል።

መግለጫው ከሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን የመጡ ስደተኞች ሩዋንዳ ከደረሱ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት አማራጮችን እንደሚፈልግላቸው ያትታል።

"ሰዓረ ሙዚቃ በጣም ያዝናናው ነበር" ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ

" አንዳንዶች ወደ ሶስተኛ ሀገር ሄደው እንዲኖሩ ሊደረግ ይችላል። አንዳንዶቹ ደግሞ ከዚህ ቀደም ጥገኝነት ጠይቀው ወዳገኙበት ሀገር ይመለሱ ይሆናል፤ ወይንም ሀገራቸው ሰላም ከሆነ ወደዚያው ሊመለሱ ይችላሉ" ይላል።

ከዚህ ቀደም ሩዋንዳ ከእስራኤል እንዲወጡ የተደረጉ አፍሪካዊ ስደተኞችን ለመቀበል ስምምነት ላይ መድረሷን አስተባብላ ነበር።

ይህ ስደተኞችን በአፍሪካ ውስጥ መጠለያ አግኝተው እንዲቆዩ የማድረግ ፖሊሲ የአውሮፓ ሕብረት አፍሪካውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ ለማድረግ የተጠቀመበት ፖሊሲ ነው።

ማይግሬሽን ፖሊሲ ኢንስቲትዩት የተባለው ድርጅት ውስጥ የምትሰራው ካሚሌ ሌ ኮዝ ለቢቢሲ እንደተናገረችው ይህ ስምምነት በአውሮፓ ሕብረትና በኒጀር መካከል ያለ ሲሆን አፍሪካውያን ስደተኞች አውሮጳ መግባት እስከሚፈቀድላቸው ድረስ እንዲቆዩ ለማድረግ የተደረሰ ስምምነት ነው።

"ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በትንሳኤ በዓል ነበር" የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ እናት

በሐምሌ ወር የተባበሩት መንግሥታት በሊቢያ የሚገኙ ሁሉንም የስደተኛ ማቆያ ጣቢያዎች ስደተኞችን ለማቆየት ብቁ አይደሉም በማለት እንዲዘጉ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

በተለያዩ ማዕከላት ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች በጣቢያው ግርፋት፣ መደፈር እንዲሁም የምግብ እጥረት እንደሚያጋጥማቸውና የቲቢ በሽታም መዛመቱን በመጥቀስ ስሞታቸውን ያሰማሉ።

አምኒስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ደግሞ ሁኔታውን የገለጸው "ሰብዓዊ ያልሆነ" እና "አሰቃቂ" በማለት ነበር።

ባለፈው ወር ሊቢያ በሚስራታ፣ ታጆራ እና ኮህምስ የሚገኙ ሶስት የስደተኞች ማቆያ ጣቢያዎችን ለመዝጋት ማቀዷን አስታውቃ ነበር።

በሐገሪቱ ያለውን ሁኔታ የሚቃኙ ድርጅት የእነዚህ ስደተኛ ማቆያዎች መዘጋት በሌሎች ማቆያ ጣቢያዎች ላይ መጨናነቅ ይፈጥራል ሲሉ ስጋታቸውን ተናግረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ