ኦክስፎርድ ከዓለማችን ቀዳሚው ዩኒቨርስቲ ተባለ

ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ Image copyright Getty Images

ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በዓለማችን ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሁሉ ለተከታታይ አራትኛ ዓመት ቀዳሚ መሆኑ ተገለፀ።

የዓለማችን ግዙፍና ስመጥር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ የሚያወጣው ተቋም ካምብሪጅን ሶስተኛ ኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደንን አስረኛ አድርጎ በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ አስቀምጧል።

ነገር ግን ደረጃውን የሚያወጡ አካላት ሌሎች የዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሌላ ሀገር ተቋማት ጋር ባለባቸው ፉክክር የተነሳ "ደረጃቸውን ይዘው ለመቆየት እየታገሉ ነው" ብለዋል።

በአውሮጳ ስመጥር ከሆኑ ዩኒቨርስቲዎች መካከል የጀርመን ዩኒቨርስቲዎች የዩናይትድ ኪንግደም አቻዎቻቸውን በመቀናቀን የበላይነቱን ይይዛሉ ሲሉ ግምታቸው በማስቀመጥ አስጠንቅቀዋል።

ከነፍስ የተጠለሉ የዘሪቱ ከበደ ዜማዎች

የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ

ኦክስፎርድ ዳግመኛ የዓለማችን ምርጡ ዩኒቨርስቲ በመሆን አንደኛነቱን የተቆናጠጠ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ሆኗል።

የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ከምርጥ አስሮቹ መካከል ሰባቱን በመያዝ የደረጃ ሰንጠረዡን በበላይነት የተቆጣጠሩት ሲሆን ከ200 ዩኒቨርስቲዎች መካከል ደግሞ 60ዎቹ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ናቸው።

የእሲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ የዋዛ አለመሆናቸው ነው የሚነገረው። ቻይናና ጃፓን ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ብቅ እያሉ መጥተዋል።

በዚህ ዓመት ሳትጠበቅ ምርጥ የአለማችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እግሯን ያስገባች ጠንካራ ተፎካካሪ አገር ኢራን ናት።

የዓለማችን ምርጥ 10 ዩኒቨርስቲዎች

  1. ኦክስፎርድ
  2. ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ
  3. ካምብሪጅ
  4. ስታንፎርድ
  5. ማሳቹስቴስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ
  6. ፕሪንሴቶን
  7. ሐርቫርድ
  8. ያሌ
  9. ቺካጎ
  10. ኢምፒሪያል ኮሌጅ ለንደን

መምህራንን ተክቶ ያስተማረው ወታደር እየተወደሰ ነው

የዓለማችን ምርጥ ዩኒቨርስቲ ዝርዝር ከ92 ሀገራት የተገኙ 1300 ዩኒቨርስቲዎች የተካተቱበት ሲሆን ለደረጃ መመዘኛ መስፈርት ሆኖ ያገለገለው የማስተማር ብቃት፣ የምርምርና ስርፀት ስራዎች፣ ለማጣቀሻነት የዋሉ የምርምር ስራዎች እንዲሁም የኢንደስትሪው ገቢና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ናቸው።

የጀርመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳጎስ ያለ ገንዘብ በማውጣት ዩኒቨርስቲዎቻቸው ላይ ኢንቨስት እያደረጉ መሆኑን ከደረጃው ጋር ተያይዞ የወጣው ዳሰሳ ያስረዳል።

የእንግሊዝ ዩኒቨርስቲዎች የሆኑት ሶስቱ ተቋማት ኦክስፎርድ፣ ካምብሪጅና ሎንዶን ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ ዛሬም እርስ በእርስ ባላቸው ትብብር ጥንካሬያቸው አብሯቸው አለ ተብሏል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ