የ2011 ዓ.ም አበይት ክንውኖች በፎቶ

ዛሬ 2011 ዓ. ም. ን ተሰናብተን 2012 ዓ. ም ን ተቀብለናል። ያለፈውን ዓመት ወደኋላ ስንቃኘው አበይት ከነበሩት ክንውኖች ጥቂቱን መራርጠን እንዲህ በምስል አጠናቅረነዋል።

ይናገራል ፎቶ. . . ይባል የለ?

በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ

2011፡ በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት

የኢትዮጵያ ሙዚቃ- ከመስከረም እስከ መስከረም

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ በዓመቱ ጎልተው ከወጡ ኩነቶች አንዱ ነው
Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሱዳን ባለፈው ዓመት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መክረሟን ተከትሎ ውጥረቱን ለማርገብ ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች እንደነበር ይታወሳል
Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የጤና ጥበቃ ሚንስትር በየወሩ ከመኪና ነጻ ቀን የጀመረው በ2011 ዓ. ም. ነበር
Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በአፋር 3.8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ ሙሉ የራስ ቅል መገኘቱ የተገለጸበት ዓመትም ነበር
Image copyright OFFICE OF THE PRIME MINISTER
አጭር የምስል መግለጫ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ጠቅላይ ሚንስትሩ አቀባበል አድርገውለታል
Image copyright MICHAEL TEWELDE
አጭር የምስል መግለጫ ዘንድሮ 350 ሚሊዮን ችግኞች በመላው አገሪቱ መተከሉ ተገልጿል
Image copyright MICHAEL TEWELDE
አጭር የምስል መግለጫ የ2011 የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያነሳው መቀለ 70 እንደርታ
Image copyright GEGNIT ETHIOPIA/ TWITTER
አጭር የምስል መግለጫ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከካቢኔያቸው 50 በመቶውን ሴቶች አድርገዋል
Image copyright Jemal Countess
አጭር የምስል መግለጫ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተሳፈሩ 157 ተጓዦች ሕይወታቸውን አጥተዋል
Image copyright Yonas Fisehaye
አጭር የምስል መግለጫ የዛላምበሳ ድንበር የዛሬ ዓመት ለእንቁጣጣሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት ተከፍቶ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ከወራት በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ተዘግቷል።
አጭር የምስል መግለጫ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንቶች ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በዚህ ዓመት ነበር ይህቺን ዓለም በሞት የተሰናበቱት