የሳዑዲዋ ልዕልት በፓሪስ የቧንቧ ሠራተኛውን በማገቷ ተፈረደባት

የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን

የሳዑዲዋ ልዕልት በፈረንሳይ በሚገኘው ቅንጡ መኖሪያዋ የቧንቧ ሠራተኛ በመደብደብና በማገት ተከሳ፤ ከዚህ በኋላ ሌላ ጥፋት ካጠፋች ተፈፃሚ የሚሆን የአሥር ወር ቅጣት ተፈረደባት።

የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን እህት የሆነችው የ43 ዓመቷ ሐሳ ቢንት ሳልማን የንጉሥ ሰልማን ሴት ልጅ ነች።

የግል ጠባቂዋ ቧንቧ ሠራተኛውን እንዲደበድብ አዛለች ተብላ የተከሰሰች ሲሆን፤ የሠራተኛው ጥፋት ነው ያለችው ደግሞ የቤቷን የውስጥ ክፍል ፎቶ ማንሳቱን ነበር።

የቧንቧ ሠራተኛው አሽራፍ ኢድ እንደተናገረው፤ የግል ጠባቂዋ ጠፍንጎ ካሰረው በኋላ የልዕልቷን እግር እንዲስም አስገድዶታል።

ከ22 ዓመት በኋላ በ 'ጉግል ማፕ' አስክሬኑ የተገኘው ግለሰብ

በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ

ሐሙስ ዕለት ችሎት የዋለው የፈረንሳይ ፍርድ ቤት፤ ልዕልቷ በተመሰረተባት ክስ ጥፋተኛ ነች ሲል ፍርዱን ሰጥቷል።

ልዕልቷ በቁጥጥር ሥር እንድትውል ዓለም አቀፍ ማዘዣ የወጣባት ሲሆን፤ በተአቅቦ የ10 ሺህ ዩሮ ቅጣት እንድትከፍል ተወስኖባታል።

ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ፤ የልዕልቷ ጠበቃ የሆኑት ኢማኑዔል ሞይኔ፤ የቧንቧ ሠራተኛው ውንጀላ "በምኞት የተሞላ" ነው በማለት ይግባኝ እንደሚሉ ተናግረዋል።

ምን ነበር የሆነው?

እኤአ በ2016 መስከረም ወር ላይ፣ ኢድ ፈረንሳይ ውስጥ ወደሚገኝ የልዕልቷ ቅንጡ መኖሪያ አፓርትመንት አምስተኛ ፎቅ የተበላሸ የእጅ መታጠቢያ እንዲጠግን ጥሪ ቀረበለት።

ግብፃዊው ሠራተኛ፤ መታጠቢያ ክፍሉን ሲመለከተው አላስቻለውም። ስልኩን መዥረጥ አድርጎ አውጥቶ ፎቶ ማንሳት ጀመረ። በእርግጥ "ለሥራዬ የሚረዳኝ ነገር ስላየሁ ነው ያነሳሁት" ብሏል።

ነገር ግን ልዕልቷ በመስታወት ውስጥ የሚታየው ምስሏ ፎቶ ውስጥ መግባቱ አስቆጣት። ከዚያም የግል ጠባቂዋን ሰይድን ጠርታ አስሮ እንዲገርፈው አዘዘች።

ቧንቧ ሠራተኛው እንደሚለው፤ እግሯን እንዲስም ተገዷል፤ ለበርካታ ሰዓታትም እንዳይወጣ ታግቶ ቆይቷል። እንደውም ልዕልቷ የሆነ ሰዓት ላይ ብልጭ ብሎባት "ይህንን ውሻ ግደለው፤ ሊኖር አይገባውም" ብላ ነበር ብሏል።

"የአምባቸው ሕልም የተጠናከረ አማራን፣ የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት ነበር" አቶ ቹቹ አለባቸው

የልዕልቷ ጠባቂ ሐምሌ ወር ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዳስረዳው፤ ወደ መታጠቢያ ቤት የሄደው የልዕልቲቱን የድረሱልኝ ጩኸት ሰምቶ ነበር። ሲደርስም ልዕልቲቱና ቧንቧ ሠራተኛው ስልኩን ይዘው ይታሉ ነበር።

"ከዛም የዚህ ሠራተኛ ዓላማ ምን እንደሆን ባለማወቄ በጉልበት ስልኩን አስጥየዋለሁ" ብሏል። ምስሉን ሊሸጠው አስቦ ይሆናል ሲል ግምቱንም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

በሳዑዲ ሕግ መሰረት ልዕልቲቱን ፎቶ ማንሳት ክልክል ነው።

የልዕልቲቱ ጠበቃ፤ የቧንቧ ሠራተኛው ከክስተቱ በኋላ በተከታታይ ወደ አፓርታማው እንደሄደና የ21ሺህ ዩሮ ክፍያ እንደጠየቀ ተናግሯል።

የሳዑዲዋ ልዕልት ሐሳ፤ በበጎ አድራጎቷ እና በሴቶች መብት ተከራካሪነትዋ የምትንቆለጳጰስ ናት።