በቡና መደፋት ምክንያት በረራ ተቋረጠ

አውሮፕላን አብራሪው የአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ላይ ቡና በማፍሰሱ፤ በረራው ተቋርጦ እንደነበር የዩናይትድ ኪንግደም መርማሪዎች ተናግረዋል Image copyright AAIB
አጭር የምስል መግለጫ አውሮፕላን አብራሪው የአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ላይ ቡና በማፍሰሱ፤ በረራው ተቋርጦ እንደነበር የዩናይትድ ኪንግደም መርማሪዎች ተናግረዋል

ባለፈው የካቲት ላይ፤ 337 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረ አውሮፕላን አብራሪ፤ የአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ላይ ቡና በማፍሰሱ፤ በረራው ተቋርጦ እንደነበር የዩናይትድ ኪንግደም መርማሪዎች ተናገሩ።

ከጀርመን፣ ፍራንክፈርት ወደ ካንኩን፣ ሜክሲኮ እየተጓዘ የነበረው አውሮፕላን፤ በአየርላርንዷ ሻኖን ለማረፍ ተገድዶ ነበር።

ሻምፓኝ እና ፅጌረዳ ያጀበው የአዲስ አበባ-አሥመራ በረራ

ለሥራ ከከተማ የወጣ ሰራተኛ ወሲብ ሲፈጽም በመሞቱ ቀጣሪው ኃላፊነቱን ይውሰድ ተብሏል

ንቦች የአውሮፕላን በረራ አስተጓጎሉ

መርማሪዎቹ እንዳሉት፤ የአውሮፕላን አብራሪው የድምጽ መቆጣጠሪያ እየቀለጠና ጭስ እየወጣውም ስለነበረ በረራው ተቋርጧል። አብራሪውና ረዳት አብራሪው ኦክስጅን የሚያመነጭ ጭንብል ለማጥለቅም ተገደው ነበር።

በበረራው ወቅት ምንም ጉዳት አልደረሰም።

አውሮፕላኑ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በኩል እያለፈ ሳለ፤ ዋናው አብራሪ ረዳቱን እየተቆጣጠረ ባለበት ወቅት ነበር ቡና የቀረበላቸው። ቡናውን የያዘው ፕላስቲክ ክዳን እንዳልነበረውም ተመልክቷል።

ዋናው አብራሪ ቡናውን ጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠው በኋላ ፕላስቲኩ ተንሸራቶ እንደወደቀ መርማሪው 'ኤር አክሲደንትስ ኢንቨስትጌሽን ብራንች' ገልጿል።

ቡናው ከአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ መሣሪያዎች ጥቂቱ ላይ ከፈሰሰ በኋላ በረራው ተቋርጧል።

'ኤር አክሲደንትስ ኢንቨስትጌሽን ብራንች' እንዳለው፤ አውሮፕላን ውስጥ ቡና የሚቀርብበት ፕላስቲክ ክዳን እንዲኖረው ትዕዛዝ ተላልፏል።