ኬንያ ራስተፈሪያኒዝም ኃይማኖት ነው ስትል በየነች

ኬንያ ራስተፈሪያኒዝም ኃይማኖት ነው ስትል በየነች Image copyright Phil Clarke Hill

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ራስተፈሪያኒዝም ከሌሎች ኃይማኖቶች እኩል ኃይማኖት ነው ሲል በየነ።

አንድ ትምህርት ቤት አንዲት ልጅ ፀጉሯን በራስተፈሪያን እምነት መሠረት 'ድሬድሎክ' አድርጋለች ሲል ከትምህርት ማገዱን ተከትሎ ነው ክስ የተመሠረተው።

ዳኛ ቻቻ፤ ልጅቱ እምነቷን ተከትላ ነውና ፀጉሯን 'ድሬድሎክ' ያደረገችው፤ የመማር መብቷን ልትከለከል አይገባም ሲል ፍርድ ሰጥተዋል። ራስተፈሪያኒዝም ጃማይካ ውስጥ እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1930ዎቹ የተመሠረተ እምነት ነው።

የልጅቱ ወላጆች ናቸው። «ልጃችን በኃይማኖቷ ምክንያት ትምህርት ተነፍጋለች፤ ፀጉሯ ደግሞ የእምነቷ ምልክት ነው፤ ልትላጨውም አትችልም» ሲሉ ነው ክሳቸውን ያሰሙት።

የኬንያ ሕገ-መንግሥት ማንም ሰው በኃይማኖት፣ በሃሳብ፣ በእምነት እና አስተያየቱ ምክንያት መገለል ሊደርስበት አይችልም ቢልም ልጃችን ግን መገለል ደርሶባታል ሲሉም አክለው ክሳቸውን አሰምተዋል።

ኬንያ ትምህርት ቤት ውስጥ መተግበር ያለበት አለባበስን የሚወስን ሕግ ባይኖራትም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ሥርዓትን የማይውክ ሕግ እንዲያወጡ ይገደዳሉ። በኃይማኖት ምክንያት ግን ማንም እምነቱን ሊቀይር አይገባም የሚል ሕግ ተቀምጧል።

«ወደ አህጉረ አፍሪካ ተመልከቱ! አንድ ጥቁር ይነግሣል፤ ነፃነትም ይሆናል» ጃማይካዊው የመብት ታጋይ ማርከስ ጋርቬይ ነበር ይህን 'የተነበየው'። ኢትዮጵያን ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ የገዙት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በ1923 ዓ. ም. የንግሥና ዙፋናቸውን ጫኑ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አማኞች ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለስላሴ ከአምላክነት ጀምሮ የተለያየ ስፍራ ተሰጥቷቸዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ