ዋሾዎችን ለመለየት የሚረዱ መንገዶች

ከፍቅረኛው ጋር እየሄደ ሌላ ሴት የሚመለከት ወንድ Image copyright Getty Images

እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር የሚሉ ዓይነት ሰው ነዎት? ወይስ ዋሽቶ ማስታረቅ በሚለው ሀሳብ የሚያምኑ?

ብዙም ጉዳት የማያስከትሉ ውሸቶች ለማኅበረሰብ በጋራ መቀጠል አስፈላጊ እንደሆኑ ይታመናል።

ሰዎች የሚናገሩት ነገር ውሸት ይሁን ወይም እውነት ማወቅ ቀላል ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ሰዎች ሲዋሹ ለማወቅ የሚረዱ መንገዶች አሉ።

ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ

በሳዑዲ የደረሰው ጥቃት እጅጉን እንዳሳሰባቸው የኔቶ ኃላፊ ገለፁ

በመዋሸት ሰላምን ማስጠበቅ

ለመሆኑ ውሸት ምንድን ነው?

አንድ ሰው ሆነ ብሎ፣ ለማታለል አቅዶ፣ ከእውነታ የራቀ መረጃ ሲሰጥ እየዋሸ ነው እንላለን። ግን ምን ያህሎቻችን ሙሉ በሙሉ እውነት እንናገራለን?

ከአንድ ሰው ጋር ሲያወሩ፤ ያ ሰው ስለእርስዎ የሚያስበውን ነገር አንዳችም ሳያስቀር የሚነግርዎ ይመስልዎታል? ሰዎች ስለእርስዎ ያላቸውን አመለካከት አንድም ሳያስቀሩ ቢዘረግፉት፤ አብሮነታችሁ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ይችላል።

ብዙዎቻችን መቶ በመቶ ሀቀኛ መሆን አዋጭ እንዳልሆነ እናምናለን።

ስለዚህ አንድን ሰው 'ውይ ጸጉርህ ሲያስጠላ' አንለውም። ምንም እንኳን ጸጉሩን ባንወደውም፤ እውነታውን እንደብቃለን። እውነታውን በመደበቃችንም ከሰውየው ጋር ያለን ግንኙነት ጤናማ ይሆናል።

ከሦስት ሰው አንዱ በየቀኑ ይዋሻል

የሥነ ልቦና ተመራማሪው ሪቻርድ ዊስማን እንደሚናገሩት፤ ከሦስት ሰዎች አንዱ በየቀኑ ቢዋሹም፤ ወደ አምስት በመቶ የሚሆኑ ሰዎች 'ዋሽተን አናውቅም' ይላሉ።

ሰዎች በቀላሉ መዋሸት ቢችሉም ሌላ ሰው ሲዋሽ ለማወቅ እንደማይችሉ ተመራማሪው ያስረዳሉ።

ተመራማሪው ቤተ ሙከራ ውስጥ የሚዋሹ ሰዎች የሚታይበት ቪድዮ ከፍተው 'እነዚህ ሰዎች እየዋሹ ነው?' ብለው ብዙ ሰዎችን ጠይቀው ነበር። ከተጠያቂዎቹ መካከል ቪድዮው ላይ ከሚታዩት ሰዎች ዋሾዎቹን መለየት የቻሉት 50 በመቶው ብቻ ናቸው።

ተመራማሪው እንደሚናገሩት፤ ፖሊሶች፣ ጠበቆች እና ዳኞችም ዋሾዎችን ለመለየት ይቸገራሉ።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ውሸታም ሰዎችን በማወቅ ረገድ ውጤታማ ሆነው የተገኙት ታራሚዎች ናቸው።

ሶስት ሚሊየን ሶሪያውያን ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ ነው

የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃ

ሰው ሲዋሽ ለማወቅ አይንዎን ሳይሆን ጆሮውን አስልተው ይጠብቁ

ብዙ ጊዜ ሰዎች ሲዋሹ ማወቅ የማንችለው ትኩረታችን እይታ ላይ ስለሆነ ነው። አዕምሯችንም ለእይታ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል።

በርካቶች ዋሾዎችን ለመያዝ የሚጠቀሟቸው መንገዶች አነዚህ ናቸው፦ ግለሰቡ ሲያወራ ይቁነጠነጣል? ፊቱ ላይ ዋሾነት ይነበባል?

ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን እይታ ብቻውን በቂ አይደለም። እንዲያውም የሰዎችን ንግግር አትኩሮ በማዳመጥ እየዋሹ መሆን ወይም አለመሆኑን መረዳት ይቻላል፥

ውሸታም ሰዎች ለአንድ ጥያቄ መልስ ከመስጠታቸው አስቀድመው ዘለግ ላለ ሰዓት ያሰላስላሉ። ራሳቸውን ከወሬው ለማራቅ ስለሚሞክሩ 'እኔ'፣ 'የኔ' የሚሉ አገላለጾችን አብዝተው አይጠቀሙም።

ግንባርዎ ላይ 'ኪው' በመስራት ዋሾ መሆን አለመሆንዎ ሊታወቅ ይችላል

የሥነ ልቦና ተመራማሪው ሪቻርድ ዊስማን፤ ሰዎች በጣታቸው የኪው ምልክት ሠርተው ግንባራቸው ላይ እንዲያሳዩ በማድረግ ውሸታም ናቸው ወይስ ሀቀኛ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ።

"Q" የተባለቸውን የእንግሊዘኛ ፊደል በጣትዎ ከሠሩ በኋላ ግንባርዎ ላይ ሲያሳርፉት የፊደሉ ጭራ ያደላው ወደ ግራ አይንዎ ነው ወይስ በስተቀኝ ወዳለው አይንዎ?

የፊደሉን ጭራ ወደግራ አይንዎ ካደረጉ የለየልዎ ውሸታም ነዎት ማለት ነው። የ 'ኪው' ጭራ ወደቀኝ አይንዎ ካደላ ደግሞ ሀቀኛ የመሆን እድልዎ ሰፊ ነው።

ተመራማሪው ከዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሱት ያለምክንያት አይደለም። አንድ ሰው 'ኪው' ሠርቶ ግንባሩ ላይ ሲያሳርፍ ሰው ጭራውን ማየት በሚችልበት አቅጣጫ ካደረገ፤ ለሰዎች አመለካከት ከፍተኛ ቦታ ይሰጣል ማለት ነው። ስለዚህም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ይዋሻል።

በተቃራኒው የፊደሉ ጭራ ለተናጋሪው በሚታይበት አቅጣጫ ከሆነ፤ ተናጋሪው ሰዎች እንዴት ያዩኛል? ብሎ ብዙም ሳይጨነቅ እቅጭ እቅጩን እንደሚያወራ ያሳያል።

አል-ቃይዳ ከቢን ላደን ልጅ መገደል በኋላ

አውስትራሊያዊው ተናካሽ ቁራ ሲሸሽ ከብስክሌት ወድቆ ሞተ

ሰው ብቻ ሳይሆን እንስሳትም ይዋሻሉ

እዚህ ምድር ላይ የሚዋሹት የሰው ልጆች ብቻ አይደሉም። እንስሳትም አጭበርባሪ ናቸው።

ለምሳሌ ስክዊድ የተባለው የአሳ ዝርያ ራሱን ከአጥቂ ወንድ ለመከላከል ሴት መስሎ ይንቀሳቀሳል። ወንድ ዶሮ ምግብ በአካባቢው ባይኖርም፤ ምግብ ሲያገኝ የሚያወጣውን ድምጽ ተጠቅሞ ሴት ዶሮ ይጠራል። ጥሪው ውሸት ላይ የተመሰረተ ነው።

የሰው ልጅ መዋሸት የሚጀምረው መቼ ነው?

ተመራማሪው ሪቻርድ እንደሚናገሩት፤ ሰዎች ከልጅነታቸው አንስቶ ሊዋሹ ይችላሉ።

ለምሳሴ አንድን ህጻን 'ከኋላህ የምትወደውን መጫወቻ አስቀምጬልሀለሁ፤ ነገር ግን ዞር ብለህ እንዳታይ' ብለነው ከአንድ ክፍል ብንወጣ፤ ልጁ መጫወቻውን ዞሮ መመልከቱ አይቀርም።

ተመራማሪው በሠሩት ጥናት መሰረት፤ 50 በመቶው ልጆች 'መጫወቻውን አላየሁም' ብለው ዋሽተዋል። በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት ህጻናት ከሦስት ዓመት አይበልጡም።

ጥናቱ ሰዎች በለጋ እድሜያቸው መዋሸት እንደሚጀምሩ ማሳያ ነው።

የሰው ልጅ ከጥንትም ይዋሻል

የሰው ልጅ በስልት መዋሸትን የተካነበት ከጥንት ጀምሮ ነው።

ለምሳሌ ቺምፓንዚዎች ምግብ ለማደን ሲሉ ብዙ ስልቶች ይጠቀማሉ። ቺምፓንዚዎች ምግብ ለማግኘት እርስ በእርስ የሚጣሉ ከሆነ ጸቡ ማቆሚያ አይኖረውም፤ ስለዚህ አንዳቸው ሌላቸውን የሚያታልሉበት መንገድ ይዘይዳሉ።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ዘመናዊ ሰው ይህንን ስልት እያሳደገ መጥቷል። መዋሸት ለሰው ልጆች አብሮነትና፣ ለማኅበረሰቡ በጋራ መቀጠል አስፈላጊ እንደሆነ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።