የደቡብ ኮርያ ፖለቲከኞች ለምን ጸጉራቸውን በአደባባይ ይላጫሉ?

ሁዋንግ ኪዮ-አህን ጸጉራቸውን በአደባባይ ተላጭተዋል Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ሁዋንግ ኪዮ-አህን ጸጉራቸውን በአደባባይ ተላጭተዋል

የደቡብ ኮርያ ፖለቲከኞች ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ጸጉራቸውን በአደባባይ እየተላጩ ነው።

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የሰሜን ኮርያን መንግሥት በመንቀፍ ጸጉራቸውን ደጋፊዎቻቸው ፊት ሙልጭ አድርገው ለመቆረጥ ወስነዋል።

ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ

በሳዑዲ የደረሰው ጥቃት እጅጉን እንዳሳሰባቸው የኔቶ ኃላፊ ገለፁ

ሶስት ሚሊየን ሶሪያውያን ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ ነው

ሁዋንግ ኪዮ-አህን የተባሉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ፤ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት ጸጉራችን በመላጨት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

የአገሪቱ ፖለቲከኞች መንግሥትን መቃወም የጀመሩት፤ በሙስና የተወነጀሉ ቾ ኩክ የተባሉ ግለሰብ የፍትህ ሚንስትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ነበር።

ሁዋንግ ኪዮ-አህን፤ አዲሱን የፍትህ ሚንስትር "ወንጀለኛ" ብለዋቸዋል። ጸጉራቸውን መላጨታቸው፤ ከተቃውሞ እንደማያፈገፍጉ ማሳያ መሆኑንም አክለዋል።

ቾ ኩክ እና ቤተሰበባቸው በሙስና ቢወነጀሉም፤ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። በዚህ ምክንያትም ባለፈው ሳምንት ሁለት ሴት የሕዝብ እንደራሴዎች ጸጉራቸውን ተላጭተው ነበር።

የሕዝብ እንደራሴዎቹ፤ ቾ ሥልጣን እንዲለቁ እንደሚሹም ገልጸዋል።

የሕግ መምህር የነበሩት ቾ ኩክ፤ ከትምህርት ሥራቸው ጋር በተያያዘ እንዲሁም በገንዘብ ማጭበርበርም ተወንጅለዋል። የሕግ መምህርት የሆኑት የግለሰቡ ባለቤት፤ ልጃቸው ነጻ የትምህርት እድል እንድታገኝ የትምህርት ማስረጃ አጭበርብረዋል በሚል ተከሰዋል።

ቾ ፍርድ ቤት ቀርበው፤ ልጃቸው የተጭበረበረ ማስረጃ በማግኘቷ ይቅርታ ከጠየቁ በኋላ፤ የሕግ ሥርዐቱን ፈር የማስያዝ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ጸጉር መላጨት ለምን አስፈለገ?

ደቡብ ኮርያውያን ተቃውሞ መግለጽ ሲፈልጉ ጸጉራቸውን የመላጨት ልማድ አላቸው።

የ 'ኮንፊሽየስ' አስተምህሮትን መሰረት በማድረግ፤ ጸጉርን በመላጨት ተቃውሞ መግለጽ ለዓመታት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህል ነው።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የደቡብ ኮርያ ወታደራዊ ጭቆናን በመቃወም ብዙዎች ጸጉራቸውን ይላጩ ነበር።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሴቶች ለሕዝባዊ ተቃውሞ ጸጉራችን ተላጭተው ነበር

ባለፉት ዓመታት ይሄው ልማድ ቀጥሎ፤ የመብት ተሟጋቾች ጸጉራቸውን በመላጨት አቋማቸውን መግለጹን ተያይዘውታል።

አምና፤ የደቡብ ኮርያ ሴቶችን ለመሰለል መጸዳጃ ቤት ውስጥ ስውር ካሜራዎች መተከላቸውን በመቃወም የአገሪቱ ሴቶች ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ፤ ጸጉራቸውን ተላጭተው ነበር።

ከሁለት ዓመት በፊት፤ የአሜሪካ ጸረ-ሚሳኤል ተቃውሞ ላይ ወደ 900 የሚጠጉ የአገሪቱ ዜጎች ጸጉራቸውን ተላጭተው እንደነበር ይታወሳል።

2007 ላይ የኢንዱስትሪ ማስፋፋያ የት ይሠራ? በሚል በተነሳ ውዝግብ በርካቶች ጸጉራቸውን ተላጭተው ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች