የሊቢያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች 'ሊያመልጥ ነበር' ያሉትን ሱዳናዊ ስደተኛ ተኩሰው ገደሉ

የሊቢያ የባሕር ዳርቻ ጠባቂ ስደተኞችን ሲጠብቅ Image copyright AFP

ወደ አውሮጳ በሜዲትራኒያን በኩል ሊያቋርጥ የነበረ ሱዳናዊ ስደተኛ በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ጠባቂዎች ተገደለ።

ስደተኛው የተገደለው ከበርካታ ሱዳናዊ ስደተኞች ጋር በባሕር ዳርቻ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ውሎ ወደ ትሪፖሊ ከተወሰደ በኋላ መሆኑን የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦኤም) አስታውቋል።

ሐሙስ እለት በባሕር ጠረፍ ጠባቂዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ስደተኞች አንድ መቶ ይሆናሉ የተባሉ ሲሆን፣ ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ወደሚገኝ የስደተኞች ማቆያ ጣቢያ ሲመልሷቸው ስደተኞቹ ለማምለጥ በየአቅጣጫው መሮጥ መጀመራቸው ተገልጿል።

"ዛሚ አልተሸጠም፤ በትብብር እየሠራን ነው" ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ

በምዕራብ ወለጋ መንዲ በመከላከያ ካምፕ ላይ የተወረወረ ቦምብ አንድ ሰው ገደለ

በምዕራብ ኦሮሚያ የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ ግድያ የነዋሪውን ስጋት አባብሷል

የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎቹ የሚሮጡት ስደተኞችን ለማስቆም የተኮሱ ሲሆን በዚህ መካከል አንድ ሱዳናዊ ተመትቶ ሕይወቱ ማለፉን አይ ኦ ኤም በመግለጫው ላይ አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጊቱን ያወገዘ ሲሆን የሊቢያ መንግሥት በአስቸኳይ ምርመራ አድርጎ ተጠያቂ ሆኑ ግለሰቦችን ለፍትሕ እንዲያቀርብ ጠይቋል።

" ባልታጠቁ ንፁኀን ስደተኞች ላይ ጥይት መተኮስ፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፣ የስደተኞችና ሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ደህንነት ላይም ስጋት እንዲገባን ያደርጋል" ብሏል በመግለጫቸው።

"ሟች ግለሰብ በአይኦኤም ሐኪም ጉዳቱ በደረሰበት ስፍራ ወዲያውኑ የሕክምና እርዳታ ተሰጥቶት በቅርብ ወደሚገኝ ወደ ክሊኒክ ቢወሰድም ከሁለት ሰዓት በኋላ ህይወቱን አልፏል" ሲል የነበረውን ሁኔታ አብራርቷል።

የሊቢያ የባህር ላይ ጠባቂዎች ባለፉት ስድስት ቀናት ብቻ ከ500 በላይ ስደተኞች ትሪፖሊ አቅራቢያ ከሚገኝ የባህር ዳርቻ አካባቢ በቁጥጥር ስር አውለው ወደ ስደተኞች ማቆያ መመለሳቸውን ተናግረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች