የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ

በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍ Image copyright AMMA
አጭር የምስል መግለጫ በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍ

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ አካሂደዋል።

የተቃውሞ ሰልፍ ከተካሄደባቸው ስፍራዎች መካከል፤ የአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባህርዳር፣ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያ እና ምሥራቅ ጎጃም ደብረ ማርቆስ ይጠቀሳሉ።

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ

ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ጥያቄን አወግዛለሁ አለ

የሰልፉ ተሳታፊዎች በቤተክርስቲያኗ፣ በኃይማኖት አባቶች እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ይቁም የሚል መልዕክት ይዘው ወጥተዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከተሰሙ ድምጾች መካከል፤ ''በቤተ-ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸሙት ጥቃቶች ይቁሙ፣ ጥፋተኞች ለሕግ ይቅረቡ'' የሚሉ ይገኙበታል።

Image copyright AMMA
አጭር የምስል መግለጫ በወልዲያ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍ

በደብረ ማርቆስ ከተማ የተካሄደውን ሰልፍ ከሚያስተባበሩት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በሪሁ ተስፋዬ "እጅግ በርካታ ሰዎች እየተሳተፉ የሚገኙበት ሰልፍ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ነው" ብለዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እየተሰሙ ካሉ መፈክሮች መካከል ''የቅዱስ ሲኖዶስ ድምጽ ይሰማ'' እና ''የቤተክርሰቲያን እና የኦሮቶዶክሶዊያን መገደል ይቁም'' የሚሉት ጎልተው እንደሚሰሙ አቶ በሪሁ ተናግረዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት ፅህፈት ቤት ጥያቄን በሰላሳ ቀናት እንዲመልስ ተጠየቀ

የዛሬ ሳምንት ዕሁድ በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር።

በደሴ፣ ደብረ ታቦር እና ጎንደር ከተማ በተካሄዱት እና በሰላም በተጠናቀቁት ሰላማዊ ሰልፎችም ''በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ቤተ-ክርስቲያን ያቀጠሉ እና ምዕመናንን የገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣ መንግሥት ቤተ-ክርስቲያንን ሊያከብር ይገባል'' የሚሉ ተመሳሳይ የተቃውሞ ድምጾች ነበር የተሰሙት።

ተያያዥ ርዕሶች