የናይጄሪያ ዩኒቨርስቲ በቢቢሲ ዘገባ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅም የታየውን መምህሩን አገደ

ቦኒፌስ ኢግቤንጉ (ዶ/ር)

በናይጄሪያ የሚገኘው ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሌጎስ የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ'ሴክስ ፎር ግሬድ' ከተላለፈ በኋላ መምህሩን ማገዱን አስታወቀ።

ቦኒፌስ ኢግቤንጉ (ዶ/ር) ከመምህርነቱ በተጨማሪም ፓስተር ሲሆን ዘጋቢ ፊልሙ ከታየ በኋላ ከሚያገለግልበት ቤተ ዕምነትም ታግዷል።

የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ የተሰራው በምዕራብ አፍሪካ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሲሆን፣ መምህራኖች የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ወሲብን እንደመደራደሪያነት እንደሚያቀርቡ ያሳያል።

ይህ የምርመራ ዘገባ በትናንትናው ዕለት ከተላለፈ በኋላ በምዕራብ አፍሪካና በሌሎች ሀገራትም በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እነርሱ በሚማሩበት ተቋምም ተመሳሳይ ነገር እንደሚፈፀም እየጠቀሱ ፅፈዋል።

"ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች

ሁለት ሜትር ከሃያ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ሴኔጋላዊ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች

"የረሃብ አድማን የመረጥነው ከራሳችን የምንጀምረው ተቃውሞ ስለሆነ ነው" አቶ ገረሱ ገሳ

ተባባሪ ፕሮፌሰር ቦኒፌስ ኢግቤንጉ፣ በዘጋቢ ፊልሙ ላይ እንደተማሪ ሆና ለቀረበችው ሪፖርተር የወሲብ ጥያቄ ሲያቀርብና ሲተነኩሳት ይታያል።

መምህሩ የሚያገለግልበት ፎር ስኬይር ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ላይ የፓስተሩን ያልተገባ ባህሪ ያልኮነነ ሲሆን ቦኒፌስ ኢግቤንጉ ከተወነጀለበት ተግባርም ራሱን ለማራቅ ሞክሯል።

ቢቢሲ ይህንን የምርመራ ዘገባ ለማጠናቀር ለአንድ ዓመት ያህል በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሌጎስና ዩኒቨርስቲ ኦፍ ጋና የምርመራ ስራውን ሲሰራ ቆይቷል።

ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሌጎስ ወሲባዊ ትንኮሳን በምንም ዓይነት ሁኔታ ተቀባይነት እንደሌለው የሚገልፅ ፖሊሲ ያለው ሲሆን ጾታዊ ትንኮሳ ሲፈፅም የተገኘ ወይንም መፈፀሙ በማስረጃ የተረጋገጠበት ከስራው ላይ ይሰናበታል ይላል።

ዩኒቨርስቲ ኦፍ ጋና በወሲባዊ ትንኮሳ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ተማሪም ሆነ መምህር ተግባርን የኮነነ ሲሆን በዘገባው ላይ ስማቸው የተጠቀሰ መምህራን ላይ ምርመራውን እንደሚያደርግ ገልጧል።

ቦኒፌስ ኢግቤንጉ (ዶ/ር) በዘገባው ላይ አስተያየታቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ተያያዥ ርዕሶች