በማላዊ አንድ ፖሊስ በተቃዋሚ ሰልፈኞች በድንጋይ ተደብድቦ ተገደለ

የማላዊ ፖሊስ Image copyright AMOS GUMULIRA

በማላዊ በፀጥታ ኃይሎችና በግንቦት ወር የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊውን ምርጫ በሚቃወሙ ሰልፈኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት አንድ ፖሊስ በተቃዋሚዎች ተገደለ።

የማላዊ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከመዲናዋ ሊሎንግዌ በምዕራብ በኩል በምትገኘው ምሱንድዌ ነው ፖሊሱ የተገደለው።

የፖሊስ ቃል አቀባይ ጄምስ ካዳድዘራብ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ሟቹ ፖሊስ ኡሱማኒ ኢሜዲ በድንጋይ ተደብድቦ እንደሞተ ገልፀው ገዳዮቹም "ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችና ወንጀለኞች ናቸው" ብለዋል።

እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት

የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው

በምሱንድዌ የሚገኘውን ዋነኛ መንገድ ዘግተው የነበሩትን ተቃዋሚዎችን ፊት ለፊት ተጋፍጦም ነበር ተብሏል።

አወዛጋቢ በተባለው ምርጫ ያሸነፉት የፕሬዚዳንት ፒተር ሙታሪካ ደጋፊዎች በትናንትናው ዕለትም ሰልፍ ለማካሄድ አቅደው የነበረ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ይሄንን በመቃወም ሰልፍ ወጥተዋል።

የምርጫ ኮሚሽኑ እንዲህ አይነት የድምፅ መጭበርበሮች አጋጥሞ ቸል ማለቱ ተቃዋሚዎቹን አበሳጭቷል።

የሃገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ኒኮላስ ዳውሲ እንደገለፁት መንገዱ በተቃዋሚዎች መዘጋቱን ተከትሎ ተጠቃሚዎች የፀጥታ ኃይል ጣልቃ እንዲገባ በጠየቁት መሰረት ነው ፖሊስ በስፍራው የተሰማራው ብለዋል።

"መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ያስገባል"ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

"ፖሊስ በአካባቢው ሲደርስ ተቃዋሚዎች ድንጋይ መወርወር ጀመሩ፤ በዚህ አጋጣሚም ነው የፖሊስ አባላችንን ያጣነው" ብለዋል።

ፖሊስ ተቃዋሚዎቹ ላይ አስለቃሽ ጋዝ በመርጨት ለመበተን ቢሞክርም "ተቃዋሚዎቹ እንደገና በመሰባሰብ በድንጋይ መፋለም ቀጠሉ። በዚህ ቀውስ መካከል ነው አንደኛውን ፖሊስ ነጥለው ወስደው በድንጋይ ደብድበው የገደሉት" በማለት የአይን እማኝ ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

እስካሁን ባለው 12 ሰዎች መታሰራቸውንም የሃገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል።

ሁኔታው ረገብ ካለ በኋላ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ፒታር ሙታሪካ በመዲናዋ በተደረገ የድጋፍ ሰልፍ ተገኝተው "ሃገራችን ናት፤ አናቃጥላት፣ አናፍርሳት" ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች