ቱርክ ከሶሪያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ በፈፀመችው ጥቃት በርካቶች ተገደሉ

ከሶሪያ የተተኮሰ ሮኬት በሚኖሩበት አቅራቢያ ሲያርፍ ከቤታቸው ሸሽተው የወጡ እናቶች Image copyright Reuters

ቱርክ በሶሪያዊ ሰሜናዊ ክፍል በኩርዶች ቁጥጥር ስር ያሉ ስፍራዎች ላይ በፈፀመችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተሰማ።

ቢያንስ 11 ንፁኀን ዜጎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን እንዲሁም በኩርዶች የሚመራው እና ከቱርክ መገንጠል የሚደግፈው ቡድን ወታደሮችም መሞታቸው ታውቋል።

የቱርክ ወታደራዊ ኃይል አንድ ወታደር እንደተገደለበትና ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉበት አስታውቋል።

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥቃቱ እንዲቆም እየጠየቀ ይገኛል።

ሪፐብሊካን ቱርክ ላይ ማዕቀብ ይጣልልን እያሉ ነው

ጠ/ሚ ዐብይ ለኖቤል በመታጨት ሁለተኛው የኢትዮጵያ መሪ መሆናቸውን ያውቃሉ?

ሐሙስ እለት የቱርክ ወታደሮች በድንበር አቅራቢያ የሚገኙትን ራስ አል አይንና ታል አብያድ ከተሞች መክበባቸው ተነግሯል። በኩርድ የሚንቀሳቀሰው ቀይ ጨረቃ፣ 11 ንፁኀን ዜጎች መሞታቸውን አረጋግጦ 28 ክፉኛ ተጎድተዋል ብሏል።

ከሟቾቹ መካከል ሕፃናት እንደሚገኙበትም ለማወቅ ተችሏል።

29 የሶሪያ ዲሞክራቲክ ግንባር የተሰኘውና በኩርድ ወታደሮች የተመሰረተው ግንባር አባላት እንዲሁም 17 የሌላ አማፂያን ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል።

እስካሁን ድረስ 10 መንደሮች በቱርክ ወታደሮች እጅ ገብተዋል።

Image copyright EPA

የአሜሪካውያን ተቃውሞ

በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የሚገኙ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ቱርክ በሶሪያ ለከፈተችው ጥቃት ማዕቀብ እንዲጣል የሚመክር ሰነድ ለማዘጋጀት እያሰቡ መሆኑን ተናግረዋል።

የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ሊዝ ቼኒ እንደሚሉት ከሆነ ቱርክ " የኩርድ አጋሮቻችን ላይ ያለ ርህራሄ ጥቃት በመክፈቷ ጠንካራ ርምጃ መውሰድ አለብን" ብለዋል።

ዲሞክራቶች በበላይነት በሚቆጣጠሩት ምክር ቤት የሚገኙ 29 ሪፐብሊካን ቱርክ ላይ ማዕቀብ የሚጥል ሕግ አስተዋውቀዋል። ይህ የምክር ቤቱ አባላት ንግግር የተሰማው ዶናልድ ትራምፕ በግጭቱ ዙሪያ ለማሸማገል ሀሳብ እንዳላቸው ከገለፁ በኋላ ነው።

በበዴሳ ከተማ ታዳጊውን ለመታደግ የሞከሩ 4 ሰዎች የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ

ቱርክ ወደ ሰሜናዊ ሶሪያ ረቡዕ እለት በመግባት ጥቃት የከፈተችው አሜሪካ ጦሯን ከአካባቢው ማስወጣቷን ተከትሎ ነው።

"ቱርክ ከአሜሪካ ወዳጆች እንደ አንዷ መስተናገድ ከፈለገች፣ ጠባይዋ እንደ አንዳቸው መሆን አለበት" ያሉት ቼኒ " በኩርድ አጋሮቻችን ላይ ጦርነት በመክፈቷ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል" ሰሲሉ ተደምጠዋል።

ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ አካላት አሜሪካ ጦሯን ከአካባቢው ማስወጣቷ ለቱርክ ጥቃት ይኹንታን የሰጠ ነው በማለት የተቹ ሲሆን፣ ጣይብ ኤርዶጋን ግን 480 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው የሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ " ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና ለመፍጠር" መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንን ድንበር አካባቢ ይቆጣጠሩ የነበሩት የኩርድ ወታደሮች ሲሆኑ ቱርክ "ሽብርተኞች" ፀረ ቱርክ አቋምን የሚደግፉ ስትል ትወነጅላቸዋለች።

ይህ የሶሪያ ዲሞክራቲክ ግንባር የተሰኘውና በኩርድ ወታደሮች የተመሰረተው ግንባር የአሜሪካ ብርቱ አጋር የነበረ ሲሆን አሜሪካ በአካባቢው አይ ኤስን እንድታስወግድ ከረዷት አጋሮች

መካከል አንዱ ነው።

Image copyright Getty Images

ኦሳማ ቢን ላደንን ለማግኘት ሲ አይ ኤን የረዱት ዶክተር

የአሁኑ የአሜሪካ መንግሥት ውሳኔ ግን ወዳጅነታቸውን ያላገናዘበ " ከጀርባ የተሰራ ደባ" እንደሆነ እንዲሰማቸው እንዳደረገ እየተነገረ ነው።

ይህ የቱርክ ጥቃት ዳግመኛ አይ ኤስ በስፍራው እንዲያንሰራራ እና ኩርዶችን ለይቶ በማጥቃት ወደ ዘር ጭፍጨፋ እንዲይሄድ በሩን እንዳይከፍት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው የአሜሪካ ወታደሮችን ለማስወጣት መወሰናቸው ትክክል መሆኑን እየገለፁ ነው። በአንድ ንግግራቸውም ኩርዶችን " በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት አልረዱንም" ሲሉ ተደምጠዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ