ሩዋንዳ ሁለተኛ ዙር ስደተኞችን ከሊቢያ ተቀበለች

ዛሬ ማለዳ 124 ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ሩዋንዳ ተወሰደዋል Image copyright Rwanda's ministry of emergency management
አጭር የምስል መግለጫ ስደተኞቹ ዛሬ ማለዳ ከሊቢያ ወደ ሩዋንዳ ተወሰደዋል

በሊቢያ የስደተኞች ማቆያ ውስጥ የነበሩ ስደተኞች ዛሬ ሩዋንዳ መድረሳቸው ተሰማ።

እነዚህን ስደተኞች ሩዋንዳ ወስዶ በተለያዩ ቦታዎች ለማስፈር የተደረሰውን ስምምነት መሰረት በማድረግ ነው ወደ ኪጋሊ የመጡት ተብሏል።

ከስደተኞቹ መካከል 99 ወንዶች፣ 24 ሴቶች ሰሲሆኑ ከእነዚህ መካከልም 59ኙ ታዳጊዎች እንደሆኑ የሩዋንዳ የአደጋ ጊዜ መከላከል ሚኒስትር ገልፀዋል።

ዛሬ ወደ ሩዋንዳ ከመጡት መካከል አንዳንዶቹ በሊቢያ በነበራቸው ቆይታ ለተለያየ አደጋዎች ተጋላጭ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ላይ የሞት ቅጣት ልትጥል ነው

በኬንያ ወርቃማ የሜዳ አህያ ተገኘች

በኢኳዶር የተቃዋሚ ሰልፈኞች ፖሊሶችን አገቱ

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ እንዳለው ከሆነ 106 ኤርትራውያን፣ 15 ሶማሊያውያን፣ ሁለት ሱዳናውያንና አንድ የሶሪያ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ናቸው ዛሬ ማለዳ ሩዋንዳ የደረሱት።

ስደተኞቹ ወደ ሩዋንዳ የመጡት የተባበሩት መንግሥታት እና አፍሪካ ህብረት ከሊቢያ 500 ስደተኞችን በማውጣት ሩዋንዳ ለማስፈር ከመንግሥት ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው።

በመጀመሪያ ዙር ከሊቢያ ወደ ሩዋንዳ የመጡት 66 ስደተኞች ሲሆኑ፣ ከዋና ከተማዋ ኪጋሊ በስተምስራቅ በምትገኘው የንግድ ከተማዋ ሃሾራ እንዲያርፉ ተደርጓል።

የአሁኖቹም እዚሁ እንዲኖሩ መታሰቡን ለማወቅ ተችሏል።

እንደስምምነቱ ከሆነ ስደተኞቹ በሩዋንዳ ቋሚ መኖሪያ መጠየቅ፣ ካልሆነም ወደ ሌላ ሀገር ለጥገኝነት ማመልከት የሚፈልጉ ከሆነ ደግሞ ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንዲመለሱ መጠየቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሩዋንዳውያን ስደተኞቹን በደስታ መቀበላቸው እየተገለፀ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ