ስቶርምዚ በካምብሪጅ የጥቁር ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ አድርጓል ተባለ

ስቶምዚ በየዓመቱ ወደ ካምብሪጅ ለሚገቡ ጥቁር ተማሪዎች ወጪያቸውን ይሸፍናል Image copyright Mabdulle
አጭር የምስል መግለጫ ስቶምዚ በየዓመቱ ወደ ካምብሪጅ ለሚገቡ ጥቁር ተማሪዎች ወጪያቸውን ይሸፍናል

የብሪታኒያዊው ራፐር ስቶርምዚ "በጎ ተፅዕኖ" በርካታ ጥቁር ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ኦፍ ካምብሪጅ እንዲገቡ ማስቻሉ ተገለፀ።

ዩኒቨርስቲው ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአጠቃላይ ተማሪዎቹ 3 በመቶ የሚሆኑ ጥቁር ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብሏል።

ስቶርምዚ በየዓመቱ ወደ ዩኒቨርስቲው ለሚገቡ ሁለት ጥቁር ተማሪዎች ወጪያቸውን ለመሸፈን ቃል ገብቶ ነበር።

ዩኒቨርስቲው ይህ ቁጥር የአጠቃላዩን የዩኬ ማህበረሰብ የሚያሳይ ነው ብሏል።

"የሞራል ባቢሎን ውስጥ ነን፤ በጎና እኩይ መለየት አቅቶናል" ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

የከተማው ትምህርት ቢሮ 300ሺህ ተማሪዎችን ለመመገብ እየተዘጋጀ ነው

ዘንድሮ ወደ ዩኒቨርስቲው 91 ጥቁር ተማሪዎች የገቡ ሲሆን በ 2018 በመስከረም ወር ትምህርት ከጀመሩት ከግምሽ በላይ የሚሆኑት ጥቁሮች ናቸው ተብሏል።

ዩኒቨርስቲው አክሎም ስቶርምዚ የሁለት ተማሪዎችን ወጪ እችላለሁ ማለቱ ከተሰማ በኋላ ከዩኒቨርስቲው ውጪ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚፈልጉና ስለተለያዩ ኮርሶች የሚጠይቁ ጥቁር ተማሪዎች ቁጥር ጨምሯል።

በዩኒቨርስቲው ለሚማሩ ጥቁር ተማሪዎች ቁጥር መጨመር ሌላው ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው በርካታ ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ዩኒቨርስቲውን ለማስተዋወቅ የወሰዱት ርምጃ ነው።

ዩኒቨርስቲው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘንድሮ ከ200 በላይ ጥቁር ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል።

በዩኒቨርስቲው ውስጥ የትምህርት ጉዳዮች ምክትል ቻንስለር የሆኑት ፕሮፌሰር ግርሃም ቪርጎ " ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥቁር ተማሪዎች የተመዘገቡበት ዓመት ሲሆን በራሳቸው በተማሪዎችና በዩኒቨርስቲው ጥረት የተሳካ ነው ። እኛ የመግቢያ ነጥባችንን አልቀነስነም" ብለዋል።

በዩኒቨርስቲው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዋኒፓ ንድሎቩ እንደሚገልፁት የተማሪዎቹ ቁጥር መጨመሩ " ጥቁሮችና ካሪቢያኖች የዩኒቨርስቲው የቀደመ ባህልን ለመስበር ጠንክረው በመስራታቸው ነው" ብለዋል።

"ለሌሎች ጥቁር ተማሪዎች በካምብሪጅ ቦታ እንዳላቸውና ስኬታማ እንደሚሆኑ ጥሩ ማሳያ ይሆናል" ሲሉም አክለዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ