አሜሪካ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች

አፍቃሪ ቱርክ ተዋጊዎች Image copyright AFP

አሜሪካ ቱርክ በሶሪያ ድንበር ላይ እየወሰደችው ላለው የጦር ጥቃት ምላሽ ሁለት የቱርክ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችንና ሶስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቱርኩ አቻቸው ጣይብ ኤርዶጋን ስልክ የደወሉ ሲሆን የስልክ ልውውጡም በፍጥነት ተኩስ የሚቆምበት ላይ እንደነበር ምክትል ፕሬዝዳንቱ ማይክ ፔንስ ተናግረዋል።

ማይክ ፔንስ አክለውም ወደ ቱርክ " በተቻለ ፍጥነት" እንደሚሄዱ ተናግረዋል።

ትራምፕ ቱርክን አስጠነቀቁ

ቱርክ ከሶሪያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ በፈፀመችው ጥቃት በርካቶች ተገደሉ

በአፋር ክልል በተፈፀመ ጥቃት 17 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል

የሶሪያ ጦር ወደ ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የገባ ሲሆን ይህም በቱርክ ከሚረዱ አማፂያን ተግዳሮት ገጥሞታል።

የሶሪያ ጦር ወደ አካባቢው የተሰማራው እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የአሜሪካ አጋር ከነበረው በኩርዶች ከሚመራው ጦር ጋር ከተደራደረ በኋላ ነው።

ቱርክ ከሶሪያ ጋር በሚያዋስናት አካባቢ ጦሯን አሰማርታ ውጊያ የጀመረችው በአካባቢው "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" ለመፍጠር መሆኑን ደጋግማ ትናገራለች።

ይህ "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" ስፍራ በሶሪያ ግዛት ውስጥ 30 ኪሎ ሜትርን የሚሸፍን ሲሆን፣ በዚሁ ቦታ ቱርክ በአሁን ሰዓት በግዛቷ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ 2 ሚሊየን የሶሪያ ስደተኞችን የማስፈር ሃሳብ አላት።

እነዚህ ስደተኞች አብዛኞቹ ኩርዶች ስላልሆኑ ይህንን የቱርክ ሀሳብ የሚተቹ አካላት ጉዳዩ አንድ ብሔር ላይ ያተኮረ ጥቃት ነው ሲሉ የአንካራን መንግሥት ይተቻሉ።

ሰኞ ዕለት ከዋሺንግተን ለጋዜጠኞች ቃላቸውን የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ ስቴቨን ማንቺን ማዕቀቡን "በጣም ጠንካራ" በማለት የቱርክ ኢኮኖሚን እንደሚጎዳ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ላይ ማዕቀቡ ሁለት የቱርክ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን የሚመለከት ሲሆን እነዚህ ተቋማትም የመከላከያና የኃይል እንዲሁም የሀገር ውስጥ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ናቸው ብለዋል።

" የቱርክ መንግሥት ባህሪ ንፁኃንን ለአደጋ ያጋለጠ እንዲሁም ቀጠናውን የሚያተራምስ ነው። በተጨማሪም አይኤስን ለማሽመድመድ የሚደረገውን ጥረት ፍሬ ቢስ የሚያደርግ ነው" ይላል መግለጫው።

ማይክ ፔንስ በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቱርክ አቻቸው ጋር በስልክ ማውራታቸውን ገልጠዋል።

አሜሪካ የቱርክ ያልተገባ ባህሪ በሶሪያ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ የአይ ኤስ ጦር አባላት እንዲለቀቁ ምክንያት ሆኗል ስትል ተናግራ ነበር።

የአውሮፓ ሕብረትም የሕብረቱ አባል ሀገራት ወደ ቱርክ የሚላኩ የጦር መሳሪያዎችን እንዳይልኩ ሀሳብ እንዳለው ገልጾ ነበር።

በምላሹም ቱርክ ከአውሮጳ ሕብረት ጋር ያላትን የትብብር ማዕቀፍ " አድሏዊና የሕግ መሠረት በሌለው ርምጃው የተነሳ" ዳግመኛ ለመፈተሽ እንደምትገደድ አስታውቃ ነበር።

"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው

በግጭቱ እስካሁን ድረስ 160 ሺህ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው መሸሻቸውን የተባበሩት መንግሥታት ያስታወቀ ሲሆን 50 ንፁኃን በሶሪያ ውስጥ 18 ደግሞ በደቡብ ቱርክ ድንበር ላይ መገደላቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

የኩርድ ኃይሎች 56 ተዋጊዎቻቸው መገደላቸውን የተናገሩ ሲሆን ቱርክ በበኩሏ 3 ወታደሮቿና 16 አፍቃሪ ቱርክ አማፂያን መሞታቸውን ገልጣለች።

ቱርክ ወደ ሶሪያ ጦሯን ያዘመተችው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በድንገት በስፍራው የነበረ የአሜሪካ ጦር እንዲወጣ ካዘዙ በኋላ ነው።

ይህ የአሜሪካ እርምጃ ቱርክ በአካባቢው በሚገኙ በኩርዶች የሚመራው ጦር ላይ ጥቃት ለመክፈትና የድንበር ከተሞችን በእጇ ለማስገባት ሰበብ ሆኗታል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ