የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት የማግባታቸው ወሬ ቢነፍስም ቀዳማዊቷ እመቤት ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

ቀዳማዊት እመቤት Image copyright PIUS UTOMI EKPEI

የናይጄሪያ ቀዳማዊት እመቤት አይሻ ቡሃሪ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ሁለተኛ ሚስት ሊያገቡ ነው እየተባለበት ባለበት ሁኔታ ከሁለት ወራት ከውጭ ቆይታቸው በኋላ ቅዳሜ ተመልሰዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ለሃይማኖታዊ ጉዞ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው የነበረ ሲሆን በመቀጠልም ወደ እንግሊዝ አምርተው ነበር።

ከተመለሱ በኋላም ሀሰተኛ ዜናዎችም ወደማይታሰብ ስቃይ እንደሚመራ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል።

የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል?

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው

ቀዳማዊቷ ከተመለሱ በኋላም ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ሁለተኛ ሚስት ለማግባት ማቀዳቸውንም የተነዛውንም ጭምጭምታ ተጠይቀውም በሽሙጥ መልሰዋል

ሳዲያ ፋሩቅ የተባሉ ፖለቲከኛ ለማግባት ማቀዳቸው ተነግሯል። ሰርጉ ባለመከናወኑ፤ ፖለቲከኛዋ መበሳጨታቸውን ቀዳማዊቷ እመቤት ለቢቢሲ ሃውሳ በቅኔ መልኩ አስረድተዋል።

"ሊያገባት ቃል የገባላት ሰው ሰርጉ እንደሚፈጠር አያውቅም። እሷም ሳዲያ ፋሩቅ ቀኑ እስከሚያልፍ ድረስም ጋብቻው እንደሚከናወን አልካደችም ነበር" ብለዋል።

"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ

ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የተወራ ሲሆን ባለፈው አርብ ዕለት ሰርጉ ሊከናወንም ነበር የሚሉ ወሬዎችም ተናፍሰዋል።

ፕሬዚዳንት ቡሃሪም ሆነ ሳዲያ ፋሩቅ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቀዳማዊቷ የፕሬዚዳንቱ እህት ልጅ ጋር ሲከራከሩ የሚያሳየውንም ቪዲዮ እውነትነት ቢያረጋግጥጡም ከጋብቻው ጋር ያልተገናኘና የቀድም እንደሆነ ነው።

የፕሬዚዳንቱ እህት ልጅ ፋጢማ ማማን ዱራምም ቪዲዮው የቆየ መሆኑን አረጋግጣ አሁን የወጣበትም ምክንያት ሌላ ትርጉም እንዲሰጠው ነው ብላለች።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ