የአርሰናሉ ኮከብ ዴቪድ ሉዊዝ በሩዋንዳ የሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረገው ለምን ይሆን?

የአርሰናሉ ኮከብ ዴቪድ ሉዊዝ በሩዋንድ የሁለት ቀናት ጉብኝት አደረገ Image copyright MUHIZI_Serge

የአርሰናሉ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ዴቪድ ሊዊዝ በሩዋንድ የሁለት ቀናት ጉብኝት አደረገ።

ባደረገው የሁለት ቀን ጉብኝት የሩዋንዳን እንግዳ ተቀባይነት፣ አስደናቂ ተፈጥሯዊ ሃብቶችንና ሩዋንዳውያን ሃገራቸውን ለመለወጥ የሚያደርጉትን አንድነትና ትብብር ተመልክቷል።

እናቱንና እጮኛውን አስከትሎ ኪጋሊ የደረሰው ሉዊይዝ፤ የጉብኝቱ መጀመሪያ ኪጋሊ የሚገኘውን የ1994 የዘር ፍጅት ማስታወሻ ሙዚየም ነበር። በዚህም ሩዋንዳውያን ያንን አስቸጋሪ ጊዜ አልፈው አሁን ለአፍሪካ ሞዴል የሆነችን ሃገር ለመገንባት ያደረጉትን ጥረት መታዘብ ችሏል።

ከፍተኛ ገንዘብ የተከፈለባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው?

ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ?

አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ

በመቀጠልም ሉዊይዝ ከፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ተገናኝቶ ውይይት ካደረገ በኋላ በቮልካኖ ብሔራዊ ፓርክ የሃገር ውስጥ ችግኝ ተክሏል። ምሽቱን ደግሞ የሩዋንዳን ባህላዊ ጭፈራና በከበሮ የታጀበ አስደማሚ የሙዚቃ ቅንብር በኪጋሊ አቅራቢያ በሚገኘው ሎጅና መዝናኛ በመገኘት ከቤተሰቦቹ ጋር ሆኖ ታድሟል።

ወደ ሩዋንዳ ብሔራዊ ስታዲየም በመሄድም የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችንና ደጋፊዎችን አግኝቷል።

Image copyright MUHIZI_Serge

በኪጋሊ የስብሰባ ማዕከል ተገኝቶም ለአርሰናል ደጋፊዎች ስለአጠቃላይ የእግር ኳስ ህይወቱና የሩዋንዳ ቆይታውን አስመልክቶ ጥያቄዎች ተነስተውለት መልስ ሰጥቷል።

የሉዊይዝ ጉብኝት በአርሰናል፣ በሩዋንዳ እግር ኳስ ፌደሬሽንና የባህልና ስፖርት ሚንስቴር መካከል የተደረገው ስምምነት አካል ነው። ባለፈው ዓመት ስምምነት ከተደረገ በኋላ ዴቪድ ሉዊይዝ በመጫወት ላይ ያለ ሩዋንዳን የጎበኘ ብቸኛው ተጫዋች ሆኗል።

ሉዊይዝ ግብኝቱን ሲያጠናቅቅ "ይችን አስደናቂ አገርና እንግዳ ተቀባይነትን ባህሉ ያደረገ ህዝብ ማየት በመቻሌ በጣም ደስተኛ ነኝ። እዚህ የመጣሁት ባለፉት 25 አመታት ሩዋንዳ የተጓዘችበትን መንገድ ለማየት ነበር። እውነት ለመናገር ካሰብኩት በላይ በፍጥነት ተጉዛለች። በፈጣን የእድገት ጎዳና ላይ ያለች ሃገር ነች።" ሲል ብራዚላዊው እግር ኳሰኛ አስተያየቱን ሰጥቷል።

Image copyright MUHIZI_Serge

"እኔና ቤተሰቤ ለዚህ ጉብኝት ስለተጋበዝንና እዚህ ያሉትን የኳስ አድናቂዎቼን በማግኘቴ በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ። ተመልሰን እንደምንመጣ አልጠራጠርም። ጓደኞቼም የእረፍት ጊዜያቸውን ሩዋንዳ እንዲያሳልፉ በሚገባ እነግራቸዋለሁ" በማለት አስተያየቱን የሰጠው ሉዊዝ የሁለት ቀን ጉብኝቱን አጠናቅቆ ወደ እንግሊዝ ተመልሷል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ቸልሲን ለቅቆ አርሰናልን የተቀላቀለው ዴቪድ ሉዊይዝ፤ ወደ ኪጋሊ ከመብረሩ በፊት አርሰናል በርን ማውዝን በሜዳው አስተናግዶ አንድ ለባዶ ሲያሸንፍ ብቸኛዋን ማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ዴቪድ ሉዊይዝ ነበር።

በአርሰናል ቆይታውም ለሉዊይዝ ይህች ግብ የመጀመሪያው ነች።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ