ኢትዮጵያ፡ እውን ድህነትን እየቀነስን ነው?

እንደ ዓለም ባንክ መረጃ ከሆነ ሕንድ በ25 ዓመታት ውስጥ ሩብ ሚሊዮን ሕዝቧን ከድህነት ማስወጣት ችላለች Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ እንደ ዓለም ባንክ መረጃ ከሆነ ሕንድ በ25 ዓመታት ውስጥ ሩብ ሚሊዮን ሕዝቧን ከድህነት ማስወጣት ችላለች

የዓለም ባንክ ከአንድ ትውልድ ዕድሜ ባነሰ ጊዜ ውስጥ 1.1 ቢሊዮን የዓለማችን ሰዎች 'ከድህነት አረንቋ' ወጥተዋል ሲል ገለፀ።

መቼም መረጃው በያዝነው ክፍለ ዘመን ከተሰሙ ዓለም አቀፍ መረጃዎች 'የሰይጣን ጆሮ ይደፈን' ከሚያሰኙት መካከል ሳይሆን አይቀርም።

ዓለም አቀፍ የድህነት መስመር ማለት በቀን ከ1.90 ዶላር በታች ማግኘት ማለት ነው ሲል ዓለም ባንክ ይተነትናል። ይህችን ቀጭን መስመር መድረስ ተስኗቸው በድህነት ሲኖሩ የነበሩ ሰዎች ቁጥር 1.9 ቢሊዮን ነበሩ፤ 1990 ላይ ማለት ነው። 2015 ላይ ግን ቁጥሩ ወደ 735 ሚሊየን ዝቅ ብሏል።

"ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች

በመቶኛ ሲሰላ ዓለማችን 36 በመቶ ድሆች ነበሯት፤ አሁን ግን ወደ 10 በመቶ ዝቅ ብሏል ማለት ነው።

አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ

የዓለም ባንክ አካታች ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ብዙም አለመስተዋሉና ግጭቶች መበራከታቸው የድሆች ቁጥር ከዚህም በታች ዝቅ እንዳይል ማነቆ ሆነዋል ይላል።

በሕንድ እና ቻይና ያሉ ድሆች ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን ዝቅ ሲል ከሰሃራ በረሃ በታች ያሉ ሃገራት ድህነት ግን ከድጡ ወደማጡ ሆኗል።

ካሮሊና ሳንቼዝ ፓራሞ የዓለም ባንክ ሠራተኛ ናቸው። «ባለፉት አስር ዓመታት ሁለት የተለያየ ዓይነት ፍጥነት ያላቸው ዝግመቶች አይተናል» ይላሉ።

እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት

አራት ምክንያቶች እንደ ማብራሪያ እንዳስቀምጥ ይፈቀድልኝ ባይ ናቸው ባለሙያዋ።

1. በተለያየ መንገድ የሚጓዙ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገቶች

«ገና ከጅማሬው የሰሃራ በረሃ በታች ሃገራትና እና ደቡብ አሜሪካ ወደኋላ ቀርተው ነው የጀመሩት። ወደ ምስራቅ እና ደቡብ እስያ ብንጓዝ ደግሞ እውነታው ሌላ ነው። ይህንን አሃዝ ከውልደት መጠን ጋር ብናጣምረው የምናገኘው ቁጥር ከምንጠብቀው በታች የሆነ ነው» ይላሉ ካሮሊና የመጀመሪያውን ነጥብ ሲያጠናክሩ።

አክለውም ሃገራት ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት የማያመጡ ከሆነ ድህነት መቀነስ ይችላሉ ብሎ ማሰብ ዘበት ነው ባይ ናቸው።

2. አቃፊ

ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገትን አመጣጥን መጓዝ ትልቅ ነገር ቢሆንም ይህ ሁሉን ነገር ይቀርፋል ማለት ግን አይደለም፤ የባለሙያዋ ሃሳብ ነው።

"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ

የበርካታ ሃገራት ዕደገት የተመጣጠነና አካታች አይደለም። በተለይ በታችኛው የሰሃራ በረሃ ባሉ ሃገራት ዕድገቱ ሥራ እየፈጠረ አይደለም።

ካሮሊና እንደሚሉት የሰው ሃብት ለድሃ ሃገራት የገቢ ምንጭ ነው። ሥራ የለም ማለት ደግሞ ድህነት እየቀነሰ አይደለም ማለት ነው።

3. መሠረተ ልማት

አንድ ሃገር አደገች ማለት ዜጎቿ ኪሳቸው ሞላ ማለት ብቻ አይደለም። የትምርህርት ዕድል እና መሠረተ ልማት ከፍተኛ ተፅዕኖ አላቸው። እነኚህ ካልተሟሉ ደግሞ ዕድገቱ ሊዛባ ይችላል።

ማሌዢያ ውስጥ ለምሳሌ፤ ዕደገቱም ሆነ መሠረተ ልማቱ አንድ ላይ ሲጓዙ ይታያል። የደቡብ እና ምስራቅ እስያ ሃገራት በዚህ አይታሙም። በዓለም አቀፍ እይታ ማሌዢያ ከ2013 ጀምሮ ከድህነት ወጥታለች። ሃገሪቱ ግን ይህን አታምንም።

ወደ ብራዚል ስንጓዝ ደግሞ 1990 ላይ የነበረው የ21 በመቶ ድህነት መጠን በ2014 ወደ 2.8 ቢወርድም የተመጣጠነ ባለመሆኑ ምክንያት እንደገና ማሻቀብ ማሳየት ጀምሯል።

4. ግጭት

በስተመጨረሻ [ለአንዳንድ ሃገራት በስተመጀመሪያ ሊቀመጥ ይችላል] ግጭት። በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግጭት ሃገራትን አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደኋላ እንዲራመዱ አድርጓቸዋል።

በአፋር ክልል በተፈፀመ ጥቃት 17 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል

«በቀላሉ ግጭት የሚነሳባቸው ሃገራት አሁንም ድህነት አላጣቸውም፤ ምንም እንኳ የሚታይ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ማምጣት ቢችሉም።»

እኤአ በ2015 ዓመት ግማሽ የዓለማችን ድሆች የሚኖሩት በአምስት የዓለማችን ሃገራት ነበር። ሕንድ፣ ናይጄሪያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ባንግላዴሽ እና ኢትዮጵያ።

በቅርቡ የወጣ አንድ ትንበያ ናይጄሪያ ሕንድን በመተካት ከፍተኛ ድህነት ያለባት ሃገር ትሆናለች ይላል። 100 ሚሊዮን ገደማ ድህነት ሰቀዞ የያዛቸው ሰዎች ሃገር በመሆን።

ለ2030 የተቀመጠው ትንበያም ከሰሃራ በታች ላሉ ሃገራት እፎይታን የሚሰጥ አይደለም። ከዓለም አቀፍ የድህነት መስመር በታች የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ይጨምር ይሆናል እንጂ አይቀንስም። እንደውም 90 በመቶው ከሰሃራ በታች ነው የሚገኙት ይላል ትንበያው።

እጅግ የደኸዩትስ. . .?

የተባበሩት መንግሥታት 2030 ላይ ድህነትን ከዚህች ዓለም ካላጠፋሁ ብሎ ቆርጦ ተነስቷል። በራሱ በድርጅቱ የተሠራ ትንበያ ግን ዕቅዱ ሊሳካ እንዳማይችል ያሳያል።

አቶ ራቫሊዮን የተሰኙ ባለሙያ ነገሩ ወዲህ ነው ይላሉ። «ፖሊሲዎች ድሆችን ከድህነት ለማውጣት እንጂ እጅግ ድሃ የሆኑትን ከግምት ውስጥ አያስገቡም።»

«አሁን አደጉ የምንላቸው ሃገራት ድሆች ነበሩ። ቀስ በቀስ እጅጉን ደሃ የሆኑ ዜጎቻቸውን ማበልፀግ በመቻላቸው ነው ለውጥ የመጣው። በተለይ ደግሞ ትምህርት እና ጤናን በሰፊው ማዳረስ ወሳኝ ናቸው።»

ለዚያ ነው በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት ወደኋላ እየቀሩ ያሉት ባይ ናቸው ባለሙያው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ