የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "መደመር" መጽሐፍ ተመረቀ

መደመር መጽሐፍ Image copyright facebook

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 'መደመር' የተሰኘው የመጽሐፍ ምረቃ ሥነ ሥርዓት አዲስ አበባ ውስጥ በሚሌኒየም አዳራሽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ተካሂዷል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ባለሰልጣናትና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ፣ እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ መደመር የሚል ጽሑፍ የሰፈረበትን ኬክ በመቁረስ መጽሐፉ ተመርቋል።

በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ከእንግዶቹ ጀርባ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ መጽሐፉን በስጦታ መልክ አበርክተውላቸዋል።

ዛሬ ከተመረቅው መጽሐፍ ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥነ ሥርዓቱ ላይ አራት የታተሙ ሁለት ያልታተሙ መጽሐፎች እንዳሏቸውና የታተሙትም 'ዲርአዝ' በተሰኘ የብዕር ስም እንደቀረቡ ገልፀዋል።

ከመጽሐፎቻቸው መካከል 'እርካብና መንበር'ና 'ሰተቴ' የተሰኙ የሚገኙ ሲሆን ይህ መጽሐፍ በስማቸው የታተመ የመጀመሪያው ስራቸው ነው።

ሐሰተኛ ዜና ወይስ የተቀለበሰ ውሳኔ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባደረጉት ንግግር መደመር ነገን ያያል በማለት "የእኔና የእናንተ፣ የሁላችንም መጽሐፍ ነው" ብለዋል። መጽሐፉን የሚያነቡ ሰዎች መተቸት ብቻ ሳሆን የተሻለ አማራጭ ሃሳብ በማምጣት ሀሳቡን እንዲያዳብሩ ጠይቀዋል።

መደመር መነሻውም መድረሻውም ሰውና ተፈጥሮ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር አስተሳሰብ አገርኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሚሌኒም አዳራሽ ዝግጅትን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከመፅሐፉ መግቢያ ላይ በአማርኛና በኦሮምኛ በማንበብ አስጀምረዋል።

መጽሐፉ በዛሬው ዕለት ከ20 በላይ በሀገሪቱ ከተሞች እየተመረቀ መሆኑንም በወቅቱ ተገልጿል።

የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን?

ደራሲና ጋዜጠኛ አዜብ ወርቁ ከ'መደመር' መጽሐፍ ቀንጭበው ያነበቡ ሲሆን አቶ ሌንጮ ባቲ ደግሞ ዳሰሳ አቅርበዋል።

አቶ ሌንጮ ዋና ዋና ነገሮች የኢትዮጵያን መሰረታዊ የህብረተሰባዊ ግንኙነት ስብራት፣ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሃብት ችግሮች የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ችግሮች ይፈታል ወይ? በማለት በመጠየቅ ጽሁፋቸውን አቅርበዋል።

እንደ አቶ ሌንጮ ሃሳብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መጽሐፍ ውስጥ በስፋት ተዳሰሰው የመደመር ፍልስፍና "ትልቁ የመደመር እሳቤ የማደራጀት አቅም አለው፤ የለውም የሚለው ነው" በማለት ዳሰሳቸውን በዝርዝር አቅርበዋል።

ተጨባጭ የሆኑ ጉዳዮችን መጽሐፉ ይዟል ያሉት አቶ ሌንጮ መጽሀፉ አራት ዋና ዋና ምዕራፎች እንዳሉት ተናግረዋል።

Image copyright facebook

አቶ ሌንጮ ቀዳሚው ምዕራፍ የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች ምንድን ናቸው፣ ፖለቲካዊ ዕይታን ሦስተኛው መምጣኔ ኃብት፣ አራተኛው የውጪ ግንኙነትን ይዟል ሲሉ ተናግረዋል።

መጽሀፉ እንደ ህዝብና እንደ ሀገር እንዴት ነው የምንቀጥለው የሚለውን ለመፍታት ይሞክራል ያሉት አቶ ሌንጮ፤ ደራሲው የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር ብቸኝነት ነው ሲል እንደሚያቀርብ ይጠቅሳሉ።

ይህ ብቸኝነት በአንድ ላይ ተሰባበስበን ችግራችንን ለመፍታት አቅም አሳጥቶናል ሲሉ የመደመርን አስፈላጊነት ይናገራሉ።

"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

ፉክክርና ትብብር ሚዛን አለመጠበቃቸውን በመጽሐፉ ላይ ተጠቅሷል ያሉት አቶ ሌንጮ፤ በአጠቃላይ ፍላጎትን፣ አቅምን፣ ሀብትን በማሰባሰብ እና በማከማቸት አቅም ፈጥረን ወደ ማካበትና ወደ ውጤት መምራት አለብን የሚል እይታ አለው ብለዋል።

የተሰሩ መልካም ሥራዎችን ጠብቆ ማቆየት ያስፈልጋል የሚል ሀሳብ በመጽሐፉ ውስጥ መነሳቱን የጠቀሱት አቶ ሌንጮ የመደመር እሳቤ ከዜሮ አይነሳም በማለት እስካሁን ለተሰሩት ትልልቅ ሥራዎች እውቅና ይሰጣል በማለት መሰረተ ልማት ላይ፣ ጤና ላይ፣ ትምህርት ላይ ለተሰሩት ሥራዎች እውቅና ይሰጣል ብለዋል።

የመደመር ግብ የዜጎችን ክብር ማረጋገጥ ነው ያሉት አቶ ሌንጮ ይህ ደግሞ ሀገራዊ አንድነት ሲኖር ነው ሲሉ፤ የብሔራዊ አንድነት ሊኖር እንደሚገባ ከዚያም ሁሉን አቀፍ የሆነና ዙሪያ መለስ ብልጽግና እንደሚመጣ ይገልጻሉ።

የመደመር እንቅፋቶች ተብለው በመጽሐፉ ውስጥ ከተጠቀሱት ነጥቦችም መካከል በማንሳት ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፖለቲካ፤ ያለ ችግርን ሁሉ ትናንትናና ዛሬ ላይ ማላከክ እንዲሁም በአስተሳሰብም በተግባርም የሚፈጸም ሌብነት ነው ሲሉ አቶ ሌንጮ ባቲ ተናግረዋል።

አክለውም ለእድገትና አብሮ ለመሆን ታታሪነት ወሳኝ ነው፤ ጉልበት እንኳ ባይኖር መልካም ፈቃድ መኖር አለበት ሲሉም ገልጸዋል።

ዶ/ር ምሕረት ደበበ በበኩላቸው ይህ የመደመርን የሀሳብ ዘር የተሸከመ "የመደመር ፍሬ" ነው ሲሉ ገልጸዋል።

መጽሐፉ ሁለት ዕይታዎችን እንድናይ ያደርገናል በማለትም እነዚያም ሀሳብና ሰው መሆናቸውን ገልፀዋል።

ሀሳብ በሰዎች ውስጥ አድረጎ በሰው ውስት ትልቅ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት አለው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ