የዘመናዊ ሰው መነሻ በቦትስዋና መገኘቱ ተነገረ

ዛምቢዚ ወንዝ ዛሬ ላይ በጨው ግግር ቢሸፈንም ጥንት በሰፊ ሀይቅ የተሸፈነ ቦታ ነበር Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ዛምቢዚ ወንዝ ዛሬ ላይ በጨው ግግር ቢሸፈንም ጥንት በሰፊ ሀይቅ የተሸፈነ ቦታ ነበር

በሰሜናዊ ቦትስዋና የሚገኘው ዛምቢዚ ወንዝ ዛሬ ላይ በጨው ግግር ቢሸፈንም ጥንት በሰፊ ሀይቅ የተሸፈነ ቦታ ነበር። ይህ አካባቢ የዘመናዊ ሰው ዝርያ መነሻ እንደሆነ ተመራማሪዎች ገልጸዋል።

አካባቢው ከ200,000 ዓመታት በፊት የነበሩ ሰዎች መኖሪያ ነበር ተብሎ ይታመናል። በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ለ70,000 ዓመታት ያህል በሥፍራው ኖረዋል። የአካባቢው የአየር ንብረት ሲለወጥ ግን ለም መሬት ፍለጋ መሰደዳቸውን ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

በአፋር 3.8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ ሙሉ የራስ ቅል መገኘቱ ተገለጸ

እስራኤል በቁፋሮ መስጂድ አገኘች

አውስትራሊያ በሚገኘው 'ጄኔቫ ኢንስቲትዮት ኦፍ ሜዲካል ሪሰርች' የተባለ ተቋም የዘረ መል ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጄነሳ ሀይስች እንደሚሉት፤ ከ200,000 ዓመታት በፊት ዘመናዊ የሰው ልጅ አፍሪካ ውስጥ ስለመኖሩ ማስረጃ አለ።

"የሰው ልጆች መነሻ አካባቢ የት ነው? የሚለውና እንዴት ወደሌሎች አካባቢዎች እንደተጓጓዙ ለዓመታት አከራካሪ ነበር" ሲሉ አስረድተዋል።

ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት፤ ጥንታዊ ሰዎች ማካጋዲካጋዲ የተባለ ሀይቅ አካባቢ ሰፍረው ነበር። በዚህ ለምለም ቦታ ለ70,000 ዓመታት ከኖሩ በኋላ ወደሌሎች አካባቢዎች ተጉዘዋል።

የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች?

የቀደመው ዘመናዊ ሰው ከአፍሪካ ውጪ ተገኘ

የጥንታዊ ሰው የፊት ገጽታ ይፋ ተደረገ

Image copyright Chris Bennett, Evolving Picture, Sydney, Australia
አጭር የምስል መግለጫ በሰሜናዊ ቦትስዋና የሚገኘው አካባቢ የዘመናዊ ሰው መነሻ ነው ተብሏል

ተመራማሪዎቹ የሰው ልጆችን ዘረ መል ናሙና በመውሰድ እና የአየር ንብረት ለውጥን በማጥናት አፍሪካ ከ200,000 ዓመታት በፊት ምን ትመስል እንደነበር የሚያሳይ ሞዴል ሠርተዋል።

በሌላ በኩል አንዳንድ ተመራማሪዎች የሰው ልጆችን ዘረ መል በማጥናት ብቻ የሰው ልጆች መነሻ ይህ አካባቢ ነበር ለማለት አይቻልም ሲሉ አዲሱ ጥናት ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

የሰው ልጆች ቅሪተ አካል ላይ በተሠራ ጥናት የሰው ልጅ መነሻ ምስራቅ አፍሪካ መሆኗን የሚያሳይ መረጃ መገኘቱን እንደማስረጃ በመጠቀም የተከራከሩም አሉ።