ካሊፎርኒያ በአዲስ የእሳት ወላፈን እየተቃጠለች ነው

ሰደድ እሳት በካሊፎርኒያ Image copyright MediaNews Group/The Mercury News via Getty Images

በካሊፎርኒያ ከተማ ትናንት ጠዋት ሰደድ እሳት መነሳቱን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የሎስአንጀለስ ኗሪዎች መኖሪያቸውን ጥለው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

በከተማዋ ጌቲ የተሰኘው የጥበብ ማዕከል ከሚገኝበት አካባቢ የተነሳው ሰደድ እሳት 500 ኤክር መሬት በመሸፈን የከተማዋ ውድ መንደሮች ወደሚገኙበት አካባቢ ደርሷል።

3300 የሚሆኑ ቤቶች ኗሪዎች የግድ መኖሪያቸውን መልቀቅ እንዳለባቸው ተወስኗል።

የካሊፎርኒያ ገዥ በመላ ካሊፎርኒያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። የካሊፎርኒያ የቀድሞ ገዥ ተዋናይ አርኖልድ ሽዋዚንገርም በእሳቱ መኖሪያውን መልቀቁን አስታውቋል።

"ልቀቁ የተባለበት አካባቢ የምትገኙ ከሆነ አታቅማሙ ለቃችሁ ውጡ" ሲል በትዊተር ገፁ አስፍሯል።

የከተማዋ ከንቲባ ኤሪክ ጋርሲቲ የአደጋ ጊዜ ሰነድ ተፈራርመው ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት ተጨማሪ ገንዘብና ሃይል እንደሚመድቡ አስታውቀዋል።

መኖሪያችንን አንለቅም በሚል ከባለስልጣናት ጋር ሙግት ውስጥ የገቡ እንዳልታጡም ዘገባዎች እያመለከቱ ነው።

በአሜሪካው ሰደድ እሳት የጠፉ ሰዎች ቁጥር 600 ደረሰ

'የዓለም ሳምባ' የሚባለው አማዞን ጫካ በአስፈሪ ሁኔታ እየነደደ ነው