የአማራ ክልል ረዳት ፖሊስ ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በዋስትና ተለቀቁ

ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ

የፎቶው ባለመብት, ADP Facebook page

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በዋስትና መለቀቃቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የታሰሩት ረዳት ኮሚሽነሩ በዋስትና እንዲለቀቁ መወሰኑን ቢቢሲ ከባለቤታቸው ወ/ሮ ሰሚራ አህመድ ማረጋገጥ ችሏል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ለሳምንታት በክልሉ ሥራ አመራር ተቋም ውስጥ ስልጠናና ግምገማ ካካሄዱ በኋላ ረዳት ኮሚሽነሩ መታሰራቸውን በወቅቱ ቢቢሲ ከቅርብ ምንጮች አረጋግጦ ነበር።

ረዳት ኮሚሽነሩ የታሰሩት ባለፈው ዓመት ሰኔ 15 ባህርዳር ውስጥ ከተከሰተው የከፍተኛ አመራሮች ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው እንደነበር ዘግበን ነበር።

ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር ተያይዞ በጥርጥሬ ተይዘው የነበሩት የአማራ ክልል የደህንነትና ፀጥታ ሃላፊዎች ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞና ኮሎኔል አለበል አማረ ከጥቂት ቀናት በፊት በዋስ መለቀቃቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይ ከ15ቱ ግድያ ጋር ተያይዞ በሽብር ተጠርጥረው ለአራት ወራት እስር ላይ የነበሩት የባልደራስ አባላት እንዲሁም የብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት ከትናንት በስቲያ በዋስ መለቀቃቸውም ይታወቃል።