በቤልጂየም ስደተኞች ማቀዝቀዣ የተገጠመበት የጭነት መኪና ውስጥ ተደብቀው ተገኙ

በቤልጄም 12 ስደተኞች ፍሪጅ የተገጠመበት የጭነት መከና ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ፖሊስ አስታወቀ። Image copyright Getty Images

በቤልጂየም 12 ስደተኞች ማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) የተገጠመበት የጭነት መከና ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

አንትወርፕ በተባለ ግዛት ውስጥ የተገኙት ባጠቃላይ ወንዶች ሲሆኑ፤ 11ዱ ሶርያውያን አንዱ ደግሞ ሱዳናዊ ነው። የጭነት መኪናው ወዴት እያቀና እንደነበር እስካሁን አልታወቀም።

አትክልትና ፍርፍሬ የሚያመላልሰው የጭነት መኪና ሾፌር፤ መኪናው ውስጥ ሰዎች መግባታቸውን እንደሚጠረጥር ለፖሊሶች ማሳወቁን ተከትሎ ግለሰቦቹ መገኘታቸውን ፖሊስ ተናግሯል። ለስደተኞች ቢሮ ተላልፈው መሰጠታቸውንም ተገልጿል።

'የሽንት ቤት ውሃ ለመጠጣት የተገደዱት' ኢትዮጵያዊያን ከሊቢያ ስደተኞች ማጎሪያ ወጡ

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ኑሮ በደዳብ

በኢትዮጵያ ስላሉ ስደተኞች አንዳንድ ነጥቦች

ባለፈው ሳምንት በእንግሊዝ 39 ሰዎች ማቀዝቀዣ የተገጠመበት የጭነት መከና ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ይታወሳል። በቤልጄም በኩል ወደ እንግሊዝ የገባው የጭነት መኪና አሽከርካሪ የሰው ሕይወት በማጥፋት ተከሷል።

ወደ እንግሊዝ በሕገ ወጥ መንገድ ለመግባት ሲሉ የሞቱት 39 ስደተኞች የቬትናምና የቻይና ዜጎች ናቸው።

በርካታ ስደተኞች የጭነት መኪና ውስጥ በመደበቅ ወደ አውሮፓ አገራት ለመግባት እንደሚሞክሩ ይታወቃል።

ተያያዥ ርዕሶች