በዩኔስኮ የተመዘገበው የጃፓኑ ሹሪ ቤተመንግሥት ተቃጠለ

የተቃጠለው ዋናው የሹሪ ቤተመንግስት ክፍል Image copyright EPA

በደቡባዊ ጃፓን ኦኪናዋ ደሴት የሚገኘውና 500 ዓመት ያስቆጠረው የሹሪ ቤተመንግስት ዋና ክፍል ትናንት ተቃጠለ።

ከ500 ዓመታት በፊት በሪኩዩ ሥርወ መንግስት የተገነባው የሹሪ ቤተመንግሥት እንደ አውሮፓውያኑ በ1933 የጃፓን ቅርስ ተብሎ ተመዝግቦ ነበር።

ይህ ቤተመንግሥት በሁለተኛው የአለም ጦርነት ሙሉ በሙሉ ወድሞ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ይዞታው እንደ አዲስ የተሰራ ነበር።

"ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው" አርቲስት ታማኝ በየነ

የሠርጋቸው ቀን ምሽት ለትዳራቸው መፍረስ ምክንያት የሆነባቸው ሴቶች

እስካሁን በግልፅ የተቀመጠ የውድመት መጠን የሌለ ሲሆን ስለ ቃጠሎው መንስኤም የታወቀ ነገር የለም።

የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የቤተመንግሥቱ ዋና እንዲሁም ሰሜናዊና ደቡባዊ ክፍሎች በእሳቱ ወድመዋል።

ቤተመንግሥቱ እንደ አውሮፓውያኑ እስከ 1970 ድረስ ላለበት ከተማ ኦኪናዋ ዋና ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን ዋና የቱሪስት መስህብ የሆነ ቦታም ነው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ