ናይጄሪያ፡ ከንቲባው "ክቡርነትዎ" አትበሉኝ አሉ

ከንቲባ ባባጂዴ ሳኖዎ-ኦሉ Image copyright Getty Images

የናይጄሪዋ ሌጎስ ከንቲባ "ክቡርነትዎ" ብላችሁ አትጥሩኝ ማለታቸው ተሰምቷል።

ከንቲባ ባባጂዴ ሳኖዎ - ኦሉ እንዳሉት፤ "ክቡርነትዎ" የሚለው አጠራር አምባገነን መሪን ያመለክታል። "አጠራሩ መታበይን፣ ራስን እንደ ጣኦት መመልከትን ያሳያል" ብለው፤ ሰዎች "ከንቲባ" ብለው እንዲጠሯቸው አሳስበዋል።

ከንቲባ ለመሆን ፈተናዎችን የሰበረች

ታግተው የነበሩት የትሪፖሊ ከንቲባ ተለቀቁ

የጆሃንስበርግ ከንቲባ በዘር ምክንያት ከሥልጣናቸው ለቀቁ

ከንቲባው እንደሚሉት፤ "ክቡርነትዎ" የሚለው አጠራር የሕዝብ ተመራጮች ጨቋኞች እንዲሆኑ ያነሳሳል፤ ባለሥልጣኖች የሕዝብ ኃላፊነት እንዳለባቸው እንዲዘነጉም ያደርጋል።

ስለዚህም፤ "የጨዋ አጠራር ለመጠቀም እንዲሁም በሰዎች ሕይወት ለውጥ ለማምጣትም" መወሰናቸውን አስረድተዋል።

የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው፤ ጥያቄያቸው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ጉዳይ እንጂ፤ ከንቲባው እንዴት ይጠሩ? የሚለው ግድ እንደማይሰጣቸው ተናግረዋል።

ሌጎስ ውስጥ በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውና ለጥገና በቂ በጀት ያልተመደበላቸው ጎዳናዎች የትለሌ ናቸው።

ተያያዥ ርዕሶች