አሜሪካ፡ አዛውንቱ በቀለጠ አለት የተሞላ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ

የ71 ዓመት አዛውንት፤ በቅጥር ግቢያቸው ዛፍ እየቆረጡ ሳለ፤ በእሳተ ገሞራ ሳቢያ የተፈጠረ የቀለጠ አለት ውስጥ ወድቀው ሕይወታቸው አለፈ። Image copyright Getty Images

የ71 ዓመት አዛውንት፤ በቅጥር ግቢያቸው ዛፍ እየቆረጡ ሳለ፤ በእሳተ ገሞራ ሳቢያ የተፈጠረ የቀለጠ አለት ውስጥ ወድቀው ሕይወታቸው አለፈ።

አሜሪካ ሀዋይ ግዛት ውስጥ ይኖሩ የነበሩት አዛውንት፤ 7 ሜትር በሚረዝመው የቀለጠ አለት የተሞላ ጉድጓድ ውስጥ መውደቃቸውን ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

በእሳተ ገሞራ አማካይነት የተፈጠረው በቀለጠ አለት የተሞላ ጉድጓድ፤ በስስ አለት ተሸፍኖ ስለነበር አዛውንቱ አላዩትም ነበር። አለቱን ሲረግጡት ወደ ጉድጓዱ ወድቀው ሕይወታቸው አልፏል።

የሚንቀለቀል እሳተ ገሞራ ጉድጓድ ውስጥ የገባው ሰው ተረፈ

'የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም'፡ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች

አዛውንቱን ለቀናት ያላዩ ጓደኞቻቸው ለፖሊስ ጥቆማ ካደረሱ በኋላ፤ አስክሬናቸው ተገኝቷል።

ናሽናል ጂኦግራፊክ እንደሚለው፤ የቀለጠ አለት በቀናት ወይም በሳምንታት ጊዜ ሊፈጠር ይችላል። የቀለጠው አለት ወደ 40 ማይል የሚደርስ ትቦ ሊፈጥርም ይችላል።

የሀዋይ ፖሊስ ክፍል ሻለቃ ሮበርት ዋግነር 'ቢግ አይላንድ ናው' ለተባለው ሚድያ እንደተናገሩት፤ አዛውንቱ የወደቁት ወደ ሁለት ጫማ ወይም 60 ሴንቲ ሜትር የሚሰፋው የቀለጠ አለት ያለው ጉድጓድ ውስጥ ነው። የእሳት አደጋ ተከላካዮች የአዛውንቱን አስክሬን ማውጣታቸውንም አክለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ