ሂላሪ ክሊንተን የሩስያ እጅ በእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ ገብቷል አሉ

ሂላሪ ክሊንተን

«እጅግ አሳፋሪ ነው፤ ቃላት የሚያሳጣ» ሂላሪ ክሊተን የሩስያ እጅ የእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ መኖሩን የሚያሳየው ዘገባ አለመውጣቱን አስመልክተው ያሰሙት ንግግር ነው።

ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸው ሂላሪ ዘገባው ከሚቀጥለው የዩናይትድ ኪንግደም ምርጫ በፊት መውጣት አለበት ባይ ናቸው።

የሩስያ እጅ የእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ ደርሶ ይሆን አይሆን የሚያትተው ዘገባ ታኅሣሥ 2 ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ሂላሪ ክሊንተን ሪፖርቱ ከምርጫው በፊት ቢወጣ ለመራጩ ሕዝብ ይጠቅማል ይላሉ።

ሚሼል ኦባማ በአሜሪካ እጅግ ተወዳጇ ሴት ተባሉ

ስፖርታዊ ፍልሚያ ለማየት ስታድየም የገቡት ትራምፕ ያላሰቡት ገጠማቸው

ትራምፕ በትልቁ ቡሽ ቀብር ላይ ይገኙ ይሆን?

ከእንግሊዝ ሕዝብ እንደራሴዎች በተወከሉ መርማሪዎች የተሠራው ሪፖርት፤ ስለላ፣ ጣልቃ ገብነት እና ሕግን ያልተከተለ አሠራር የእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ ተንፀባርቀው እንደሆንና የሩስያ እጇ ምን ያህል ረዝሟል የሚለውን አጣርቷል ተብሏል።

እንግሊዝ ከአውⶂጳ ሕብረት ጋር ፍቺ ለመፈፀም ያደረገችው ሕዝበ ውሳኔና የዛሬ ሁለት ዓመት የተደረገው ጠቅላላ ምርጫ የሩስያ እጅ አለበት እየተባለ ነው።

ባለፈው መጋቢት የተጠናቀቀው ሪፖርት የእንግሊዝ መንግሥት መቀመጫ ወደሆነው መንገድ ቁጥር 10 ቢመራም እስካሁን ይፋ አልተደረገም። የቦሪስ ጆንሰን መንግሥት ሪፖርት እንዳይወጣ ጫና አድርጓል በማለት የሕዝብ እንደራሴዎች ይወቅሳሉ።

መፅሐፋቸውን ለማስተዋወቅ ወደ እንግሊዝ ያቀኑት ሂላሪ ክሊንተን ከቢቢሲ ራድዮ 4 ጋር ቆይታ አድርገዋል። «አገራችንም አይተነዋል። አውሮጳም እንዲሁ። እዚህ እንግሊዝም ቢሆን። ሩስያ የምዕራቡን ዓለም ፖለቲካ ለመቆልመም ቆርጣ ተነስታለች» ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

«የአገራችሁ መንግሥት ዘገባውን ማዘግየቱ እጅግ አሳፋሪ ነው፤ ቃላት የሚያሳጣ ነው» ሲሉ ነው ሂላሪ ቁጭታቸውን ለጋዜጠኛዋ የገለፁት።

ሂላሪ፤ ሩስያ አሁንም በአሜሪካ የምርጫ ሂደት ውስጥ አለች ብለው ያምናሉ። እርሳቸው በተሸነፉበት ምርጫም እጃቸው እንዳለበት አይጠራጠሩም።

«እኔም ልክ እንደሌላው ሰው ሪፖርቱ ምን እንዳዘለ አላውቅም። ነገር ግን በወር ጊዜ ውስጥ ድምፁን ለመስጠት የሚሄው ሰው መረጃ ሊደርሰው ይገባል።»

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ