የሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶች በደህንት ስጋት ተዘጉ

ሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶች በደህንት ስጋት ተዘግተዋል። Image copyright Reuters

በሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶች በደህንነት ስጋት ተዘግተዋል።

ፖሊሶች በዩኒቨርስቲዎች ቅጥር ጊቢ ገብተው ተማሪዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የተኮሱ ሲሆን፤ በባቡር ጣቢያዎች ተሳፋሪዎችን እየፈተሹ በመሆኑም መጨናነነቅ ተፈጥሯል።

ባለፈው ሰኞ ከፍተኛ ተቃውሞ መካሄዱ ይታወሳል።

''ፕሬዝደንት ትራምፕ እባክዎ ሆንግ ኮንግን ይታደጉ'' ሰልፈኞች

ተቃውሞ በቻይና፡ መንግሥት 'የውጭ ኃይሎችን' እየወቀሰ ነው

የሆንግ ኮንግ 'የተቃውሞ' ኬክ ከውድድር ታገደ

አንድ የመብት ተሟጋች በፖሊስ የተተኮሰበት ሲሆን፤ ሌላ ተሟጋች ደግሞ በእሳት ተቃጥሏል። ሁለቱም በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

ዛሬ በርካታ ትምህርት ቤቶች የደህንት ስጋት በመኖሩ እንደሚዘጉ ለተማሪዎቻቸው ቤተሰቦች በአጭር የጽሁፍ መልዕከት አስታውቀዋል። የሆንግ ኮንጓ ካሪ ላም በበኩላቸው አለመረጋጋት ቢኖርም ትምህርት ቤቶች እንደማይዘጉ ገልጸዋል።

ሰኞ ተማሪዎችና ፖሊሶች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የባቡር አገልግሎት ተስተጓጉሎ፣ መንገዶች ተዘግተውም ነበር።

በ 'ቻይኒዝ ዩኒቨርስቲ' ተቃዋሚዎች ፖሊሶች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ፖሊሶች ደግሞ በምላሹ የፕላስቲክ ጥይት ሲተኩሱ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት አቋርጠዋል።

ሰኞ ከ260 በላይ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፤ ተቃውሞው ከጀመረበት ጊዜ እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 3,000 ደርሷል።

ካሪ ላም ተቃዋሚዎች "የሕዝብ ጠላት" ናቸው ሲሉ፤ አሜሪካ ደግሞ ሆንግ ኮንግ የገባችበት ውጥንቅጥ አሳስቦኛል ብላለች።

የሆንግ ኮንግ እስረኞች ለቻይና ተላልፈው ይሰጡ የሚል ረቂቅ አዋጅን በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ፤ ረቂቁ ውድቅ ቢደረግም እንደቀጠለ ነው።

የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ዴሞክራሲ ይስፈን፣ ፖሊሶች ለተግባራቸው ተጠያቂ ይደረጉ ሲሉ ድምጻቸውን ማሰማቱን ቀጥለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች