አሜሪካዊቷ ራፐር ካርዲ ቢ ወደ አፍሪካ ልትመጣ ነው

ካርዲ ቢ Image copyright Steven Ferdman
አጭር የምስል መግለጫ ካርዲ ቢ በሚቀጥለው ወር ናይጄሪያና ጋና መጥታ ልትዘፍን መሆኑ ተሰምቷል

አሜሪካዊቷ ራፐር ካርዲ ቢ ወደ አፍሪካ ልትመጣ መሆኑን የሰሙ አፍሪካውያን አድናቂዎች በደስታና በቅናት ውስጥ ናቸው ተባለ።

ካርዲ ቢ በሚቀጥለው ወር ናይጄሪያና ጋና መጥቼ አቀነቅናለሁ ማለቷ ከተሰማ ወዲህ በናይጄሪያና በጋና የሚገኙ አድናቂዎቿ በደስታ ሲፈነጥዙ በሌላ የአህጉሪቷ ክፍል የሚገኙ አድናቂዎች በቅናት 'ቅጥል' ማለታቸው ተሰምቷል።

ካርዲ ቢ ባለፈው ሳምንት አርብ በኢንስታግራም ገጿ ላይ "አፍሪካ መጣሁልሽ" ስትል የአፍሪካ ጉዞዋን ዜና አብስራለች።

የሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶች በደህንት ስጋት ተዘጉ

"ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው"

ሂላሪ ክሊንተን የሩስያ እጅ በእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ ገብቷል አሉ

ከዚያ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቿ ምላሻቸውን አስፍረዋል።

አንድ የድምጻዊቷ አድናቂ "ወደ ናይጄሪያ እንኳን በደህና መጣሽ" ያለ ሲሆን ሌላ ደግሞ "ካርዲ በጉጉት እንጠብቅሻለን" ሲል መልዕክቱን አስፍሯል።

አንድ ኬኒያዊ ግን "ናይሮቢስ? በሺዎች የምንቆጠር አድናቂዎችሽ እዚህም አለን" ሲል የተማጽኖ የሚመስል መልዕክት ጽፏል።

ደቡብ አፍሪካውያንም ተመሳሳይ መልዕክታቸውን በገጿ ስር አኑረዋል።

ድምጻዊቷ ከዚህ ቀደም ስትሪፐር [የራቁት ዳንሰኛ] የነበረች ሲሆን በዚህ ስራዋ ላይ እያለች ከእርሷ ጋር ወሲብ መፈፀም ይፈልጉ የነበሩ ግለሰቦችን በመድሃኒት በማደንዘዝ ትዘርፋቸው እንደነበር የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቶ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብታ ነበር።

ካርዲ ቢ የአንድ ልጅ እናት ስትሆን ከራፐር ኒኪ ሚናጅ ጋር ተጋጭተው በገጠሙት ቡጢም የመገናኛ ብዙኀን አጀንዳ ሆና ከርማ ታውቃለች።

ካርዲ ቢ ከድምጻዊነቱ ባሻገር 'ሃስለርስ' በተሰኘውና ጄኔፈር ሎፔዝ በመሪ ተዋናይነት ላይ በተሳተፈችበት ፊልም ላይ የተወነች ሲሆን ከዚህ ቀጥሎም በ'ፋስት ኤንድ ፉሪየስ 9' ላይም እንደምትተውን ተነግሯል።

ካርዲ ቢ ሙሉ ስሟ ቤልሳሊስ ማርሌኒስ አልማንዘር ሲሆን በ2019 ምርጥ የራፕ አልበም ግራሚን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት ራፐር ሆናለች።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ