ኒውዚላንድ የፈቃድ ሞት ላይ ሕዝበ ውሳኔ ልታደርግ ነው

ጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደን Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደን

የኒውዚላንድ ፓርላማ ሰዎች በፍቃዳቸው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚፈቅድ ሕግ ላይ ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን፤ በቀጣዩ ዓመት ሕጉ ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል።

በእንግሊዘኛ አጠራሩ Euthanasia የሚባለው ሂደት፤ ሰዎች ፈቃደኛ እስከሆኑ ድረስ ያለ ስቃይ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ያግዛል።

ሕጉ፤ በጠና የታመሙና በሀኪማቸው ከስድስት ወር ያላለፈ ዕድሜ እንደሚኖራቸው የተነገራቸው ግለሰቦች፤ በሀኪሞች ታግዘው እንዲሞቱ ይፈቅዳል።

ረዥም ክርክር የተደረገበት ሕጉ፤ 69 ለ 51 የድጋፍ ድምጽ አግኝቷል። የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን፤ የፈቃድ ሞትን በተመለከተ ያለው ሕግ እንዲሻሻል ከሚፈልጉ አንዷ ናቸው።

ኒውዝላንዳውያን "ጦር መሣሪያ አንፈልግም" እያሉ ነው

መምህርነት የሚያስከብር ሙያ የሆነው የት ነው?

ሰዎች 'ፖፒ' የተሰኘችውን ቀይ አበባ ለምን ደረታቸው ላይ ያደርጓታል?

በቅርብ የተሰራ ጥናት ከኒውዝላንዳውያን 72 በመቶ የሚሆኑት የፈቃድ ሞትን እንደሚደግፉ ያሳያል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2017 ወዲህ የፈቃድ ሞትን በተመለከተ ሦስት ጊዜ በሕዝብ እንደራሴዎች ውይይት ተደርጓል።

ሕጉ፤ የስድስት ወር እድሜ የተሰጣቸው ህሙማንን ብቻ ያካት ወይስ ሌሎችም በጠና የታመሙ ግለሰቦች ተጠቃሚ ይሁኑ የሚለው አከራካሪ ነበር። የኒውዚላንዱ 'ፈርስት ፓርቲ'፤ ሕጉ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት ሕዝበ ውሳኔ መካሄድ አለበት ሲል ተከራክሯል።

ሕጉ ሰፊ ድጋፍ ቢያገኝም የሚቃወሙትም አልታጡም።

የሕዝብ እንደራሴዎች በሕጉ ላይ ውሳኔ ሲያሳልፉ፤ "እንድንሞት ሳይሆን እንድንኖር እርዱን"፣ "የፈቃድ ሞት መፍትሔ አይደለም" የሚሉ መፈክሮች በማሰማት ተቃውሟቸውን ያሰሙ ነበሩ።

በሚቀጥለው ዓመት ኒውዚላንድ አገራዊ ምርጫ ስታደርግ የፈቃድ ሞት ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይተላለፋል። ከዚህ በተጨማሪ ለህክምና የሚውል እጸ ፋርስን በተመለከተም ምርጫ ይካሄዳል።

ተያያዥ ርዕሶች