ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከነጮች ባነሰ ሁኔታ የሚኖሩባት ደቡብ አፍሪካ

በደቡብ አፍሪካ ደርባን የሚገኝ የጎልፍ መጫወቻ አጠገብ የሚገኝ የጎስቋሎች መንደር ከአየር ሲታይ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ እኤአ በ2018 ከአየር ላይ የተነሳው ምስል በደቡብ አፍሪካ ሀብታምና ደሃ እንዴት ተለያይተው እንደሚኖሩ ያሳየ ነበር

ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከነጭ አቻዎቻቸው በሦስት እጥፍ ያነሰ ገቢ እንደሚያገኙ አንድ ጥናት ይፋ አደረገ።

ጥናቱ በደቡብ አፍሪካውያን መካከል ያለውን ያልተመጣጠነ ገቢን የተመለከተ ሲሆን፤ ከአገሪቱ 80 በመቶ የሚሆኑት ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የወር ገቢያቸው በአማካኝ 13000 ብር ገደማ ሲሆን፤ የነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ግን 38 ሺህ ብር አካባቢ እንደሆነ ተቀምጧል።

“ከብሔርም ከሐይማኖትም በላይ ሰውነት ከሰሃራ በረሃ ስቃይ አውጥቶኛል"

ፓርቲዎች በክልላቸው ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚታየው ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ

ከንቲባ ታከለ ኡማ በስህተት ለወጣው የኤርትራ ካርታ ይቅርታ ጠየቁ

ጥናቱ አክሎም እንዴት የተለያዩ ብሔሮች በማኅበራዊ መደብ ውስጥ እንደተቀመጡ አሳይቷል።

ጥናቱ በአገሪቱ የስታስቲክስ መሥሪያ ቤት እኤአ ከ2002 እስከ 2017 ድረስ የተሰበሰበን መረጃ የተጠቀመ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን በሥራ ማጣት ክፉኛ እንደሚቸገሩ ያሳያል።

እነዚህ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የግል የሕክምና ተቋማትን መጎብኘት፣ መጠለያና መብራት የማግኘት ጉዳይም ቅንጦት እንደሆነባቸው ጥናቱ ያመለክታል።

ጥናቱ፤ የደቡብ አፍሪካ ከተሞችን ከዓለማችን አገራት መካከል ከፍተኛ ያልተመጣጠነ ገቢ ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባት አገር አድርጓታል።

ጥናቱ ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ አከራካሪ ለነበረው ጉዳይ ጠቅለል ያለ ምልከታን በማስቀመጥ መረጃን የሰጠ መሆኑ ተነግሮለታል።

በብሔሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የሀብት ልዩነት እንዲኖር ካደረኩጉ ምክንያቶች አንዱ የአፓርታይድ ውጤት ነው የተባለ ሲሆን፣ አፓርታይድ በቁጥር አነስተኛ የሆኑት ነጮች አገሪቱ ያላትን ውስን ሀብት ያለስስት እንዲጠቀሙና ሀብት እንዲያካብቱ አድርጓል ተብሏል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ