በደረቀ ቆራጣ ጣት መጠጥ የሚቀምመው ካናዳዊ ሞተ

ካፒቴን ዲክ ስቴቨንሰን ለራሱ መጠጥ ሲቀዳ Image copyright Courtesy Downtown Hotel
አጭር የምስል መግለጫ ካፒቴን ዲክ ስቴቨንሰን ለራሱ መጠጥ ሲቀዳ

የአልኮል መጠጦችን ቀላቅሎ፣ ቅጠላ ቅጠል ጠብ አድርጎ በመቀመም የተካኑ ብዙ ናቸው። ካናዳዊው ካፒቴን ዲክ ስቴቨንሰን የሚታወቀው ግን መዐዛማ ቅጠሎችን ከጠንካራ የአልኮል መጠጦች ጋር ደባልቆ፣ በመዐዛ እያወዱ በመጠጥ ጉልበት በማስከር ብቻ አይደለም። "ሶርቶ ኮክቴል" በተሰኘው መጠጥ እንጂ።

የዚህ መጠጥ ስም ወደ አማርኛ ሲመለስ፤ ወዙ ቢመጠጥም፣ በአጭር ቃል ግን 'ቆራጣ ጣት ጣል ያለበት መጠጥ' ማለት ነው።

ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና

እንዳይበላሽ ሆኖ የደረቀው ጣት፤ እውነተኛ የሰው ልጅ ጣት ነው። ሲጠጡት ደግሞ ሕግ አለው።

ግጥም፤ ጭልጥ አልያም ፉት ሊያደርጉት ይችላሉ፤ ነገር ግን ውስጡ ያለው ጣት ከንፈርዎን ሊነካ ግድ ነው።

የዚህ መጠጥ ፈጣሪ ካፒቴን ዲክ በ89 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ተሰናብቷል። ካፒቴኑ ማስከር ሥራው ነበር። ከማስከርም በላይ ግን በደረቀ ቆራጣ ጣት የተከሸነ መጠጥ በመቀመም የተካነ ነበር።

Image copyright Downtown Hotel
አጭር የምስል መግለጫ እኤአ ከ1973 ጀምሮ ከመቶ ሺህ ሰዎች በላይ የሶርቶ ኮክቴል ክለብን ተቀላቅለዋል

የዚህ መጥ ሃሳብ እንዴት ተገኘ?

ይህ የ89 ዓመት አዛውንት መጠጡን ለደንበኞቹ መቸብቸብ የጀመረው እኤአ በ1970ዎቹ ነበር። በ1973 ግድም እርሱና ጓደኞቹ በአንድ የተረሳ የልብስ ሳጥን ውስጥ ቆራጣ ጣት ያገኛሉ።

አረቄ ከእንቁላል ደባልቆ በመጠጣት እውቅና ያተረፈው ቻይናዊ

ጣቱ እንዳይበላሽ ሆኖ የደረቀ ነበር። ያኔ ታዲያ ከሚጠጡት የአልኮል መጠጥ ጋር እንዴት አድርገው ሊቀምሙት እንደሚችሉት አወጡ አወረዱና የሶርቶ ኮክቴልን ሃሳብ አመነጩ።

ከዚህ ሃሳብ መጠንሰስ አንስቶ፤ መጠጡ የሚሸጥበት ግሮሰሪ ከ 10 በላይ የሰው እጅ ጣቶችን በስጦታ አግኝቷል።

እኤአ ከ1973 ጀምሮ ከመቶ ሺህ ሰዎች በላይ የሶርቶ ኮክቴል ክለብን ተቀላቅለዋል። ግሮሰሪው የሚገኝባት የካናዳዋ ዳውሰን ከተማ ነዋሪዎች፤ ስቴቨንሰንን "ጀግናችን" ሲሉ በሞቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጠዋል።

የከተማዋ አስተዳደሮችም በትዊተር ገፃቸው ላይ "ከተማችን አትረሳዎትም" ሲሉ ውለታውን አንቆለጳጵሰዋል።

ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች

በከተማዋ የሚገኝ ሆቴልም "የከተማችን አምባሳደር" ብሎታል

ልጁ ዲክሲ ስቴቨንሰንም፤ የአባቴ የመጨረሻ ቃል ጣቶቹ ተጠብቀው ለሶርቶ ኮክቴል ክለብ እንዲሰጡለት ነው ስትል ለሲቢኤስ የዜና ወኪል ተናግራለች።

ሆቴሉም ከቤተሰቡ ጋር በመሆን በደረቀ ጣት የተከሸነ መጠጥ ቀማሚውን ለማሰብ እቅድ እዟል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ