ሳይንቲስቶች ውሃ ለመቆጠብ ዓይነ-ምድር አንሸራታች ሽንት ቤት ሠርተዋል

የሽንት ቤት መቀመጫ Image copyright Getty Images

አሜሪካዊያን ሳይንቲስቶች ውሃ መቆጠብ ያስችል ዘንድ ዓይነ-ምድር አንሸራታች ቅባት ሠርተናል እያሉ ነው።

የፔን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች፤ አዲሱ ፈጠራ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ዓይነ-ምድርን ለመጠራረግ የምናፈሰውን ውሃ በ90 በመቶ ይቀንሳል ይላሉ።

አልፎም የመፃዳጃ ቤት ነጭ የሸክላ መቀመጫ ላይ የሚከማችን ባክቴሪያ ያጠፋል፤ አላስፈላጊ ሽታንም ያስወግዳል ይላሉ ተመራማሪዎቹ።

"በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መጸዳጃ ቤት የለውም"

ቅባቱ የሽንት ቤት መቀመጫ ላይ የሚረጭ ሲሆን ዓይነ-ምድርና ሽንትን በፍጥነት ወደታች እንዲዘልቅ ያደርጋል።

በየቀኑ በዓለማችን 141 ቢሊዮን ሊትር ውሃ ለሽንት ቤት ጥቅም ይውላል። አፍሪካ ውስጥ ለመጠጥ ውሃ የሚውለው መጠን ከዚህ አሃዝ በስድስት እጥፍ ያነሰ ነው።

የተመራማሪዎቹ ዋነኛ ዓላማ ፈጠራው ሰዎች ለዓይነ-ምድር መጠራሪጊያ የሚያውሉትን ንፁህ ውሃ መጠን መቀነስ ነው።

ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች

«ቡድናችን ተፈጥሮን መሠረት ያደረገ ጠንካራ ፈሳሽ ሠርቷል። መፀዳጃ ቤት ራሱን በራሱ እንዲያፀዳ የሚያደርገው ፈሳሽ ምርት ፀረ-ባክቴሪያ ነው» ይላሉ የፔን ስቴት ዩነቨርሲቲው ተባባሪ ፕሮፌሰር ታክ-ሲንግ ዎንግ።

«ዓይነ-ምድር ከመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ላይ ሲጣበቅ ለተጠቃሚዎች ቀፋፊ ከመሆኑ ባሻገር ጤናማ አይደለም» የሚሉት ተመራማሪ ዓላማቸው በዓለም ዙሪያ በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ቴክኖሎጂ መፍጠር እንደሆነ ያስረዳሉ።

ፈጠራው መቼ ለገበያ ቀርቦ ሰዎች ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ለጊዜው የተባለ ነገር የለም።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ