ሥራ ቦታ ጋደም ማለት መፈቀድ አለበት?

ሜትሮናፕ በዩኒቨርስቲ፣ በአውሮፕላን ማረፊያ፣ በሆስፒታል ውስጥ ይገኛል Image copyright MetroNaps
አጭር የምስል መግለጫ ሜትሮናፕ በዩኒቨርስቲ፣ በአውሮፕላን ማረፊያ፣ በሆስፒታል ውስጥ ይገኛል

አሜሪካ፤ ሠራተኞች ቢሮ ውስጥ ጋደም ማለት የለባቸውም የሚል አቋም ስታራምድ ቆይታለች። በቅርቡ ደግሞ ቢሮ ውስጥ አጠር ላለ ጊዜ መተኛት በሕግ ተከልክሏል።

ሕጉ፤ ያለ ኃላፊዎች ፍቃድ ቢሮ ውስጥ መተኛትን ያግዳል።

ሕጉን ማውጣት ለምን እንዳስፈለገ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ሕግ አውጪዎቹም በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም።

ከዓመት በፊት ከካሊፎርንያ የወጣ ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ ሞተር ነጂዎች በቀን ቢያንስ ለሦስት ሰዓት ጋደም ማለታቸው የሞተር ሳይክል ተቋምን ከ40,000 ዶላር በላይ አሳጥቶታል።

የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው?

ሥራ እና ፍቅር፡ ከሥራ አጋርዎ ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመር ሊያስባርር ይገባል?

በእርግጥ በሥራ ቦታ ላይ ዘለግ ላለ ሰዓት መተኛት ሥራ ላይ ጫና ቢያሳድርም፤ አጭር ጊዜ ጋደም ማለት ውጤታማ ያደርጋል የሚሉ ተመራማሪዎች አሉ።

በአሜሪካ የእንቅልፍ ህክምና ተቋም ፕሬዘዳንት የሆኑት ዶ/ር ሎረንስ ኤፕስቲን እንደሚሉት፤ 70 ሚሊዩን የሚደርሱ አሜሪካውያን የእንቅልፍ መዛባት ችግር አለባቸው።

ከ150,000 ሰዎች መካከል በቀን ከሰባት ሰዓት እስከ ስምንት ሰዓት የሚተኙት 35.6 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን አንድ ጥናት አሳይቷል። ቁጥሩ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ 30.9 በመቶ ወርዷል። በቂ እንቅልፍ ከማያገኙት ሰዎች ገሚሱ ፖሊሶችና የህክምና ባለሙያዎች ናቸው።

ዶ/ር ሎረንስ ኤፕስቲን እንደሚናገሩት፤ ይህንን ችግር ያስተዋሉ መሥሪያ ቤቶች ለውጥ ለማምጣት እየሞከሩ ቢሆንም መንግሥት ግን የድርሻውን እየተወጣ አይደለም።

እንቅልፍ ማጣት የሰዎች ጤናና ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ዶ/ር ሎረንስ ያስረዳሉ።

እንቅልፍ ማጣት ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ የልብ ህመም፣ ስትሮክ፣ ስኳር፣ ድብርትና ሌሎችም የአዕምሮ ህመሞች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ከአራት ዓመት በፊት የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው፤ እንቅልፍ ባጡ ሠራተኞች ሳቢያ በዓመቱ፣ በአሜሪካ ምጣኔ ሀብት ላይ የ411 ቢሊየን ዶላር ጫና ይደርሳል።

ዶ/ር ሎረንስ ኤፕስቲን እና ሌሎቸም ተመራማሪዎች ሠራተኞች ቢሮ ውስጥ ለአጭር ጊዜ መተኛት ሊፈቀድላቸው ይገባል ይላሉ።

ሥራ የማዘግየት ልማድን ለመቅረፍ የሚረዱ 8 ነጥቦች

በጃፓን ሴት ሠራተኞች መነጽር እንዳያደርጉ መከልከላቸው ጥያቄ አስነሳ

"በአግባቡ ያልተኙ ሰዎች ውጤታማ አይሆኑም፤ በሥራ ቦታ አደጋ አስከትለው ቀጣሪዎችን ለተጨማሪ ወጪ ሊዳርጉም ይችላሉ" ይላሉ።

ሠራተኞች ጋደም እንዲሉ በመፍቀድ ረገድ ጃፓን ጥሩ ተሞክሮ አላት። ረዥም ሰዓት የሚሠሩ ሠራተኞች የሚተኙበት ክፍል ይዘጋጃል። ለሠራተኞቻቸው ምቹ ወንበርና ብርድ ልብስ የሚያቀርቡ ድርጅቶችም አሉ።

ካናዳ ውስጥ 'ናፕ ኢት አፕ' የተባለ ለሠራተኞች በ25 ደቂቃ መተኛ ክፍል የሚያከራይ ድርጅት አለ። መስራቿ ለረዥም ሰዓት በባንክ ውስጥ ትሠራ የነበረችው ማህዝባን ራህማን ናት።

'ሜትሮናፕ' የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን እውቅናው እየጨረ መጥቷል። በተለይም 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሠጡ እንደ ሆስፒታል፣ አውሮፕላን ማረፊያ እና ፋብሪካ ያሉ ተቋሞች ይህን አማራጭ ይጠቀማሉ።

ማህዝባን ራህማን እንደምትለው፤ ሥራውን ሲጀምሩ ብዙ ደጋፊ አልነበራቸውም።

"ስንጀምር፤ ብዙዎች ሥራ ቦታ መተኛትን የምናበረታታ መስሏቸው ነበር" ትላለች። አሁን ግን ሠራተኞቻቸው ጋደም ብለው ወደ ሥራ በመመለሳቸው ውጠታማ መሆናቸውን ያስተዋሉ ድርጅቶች ሀሳባቸውን እየቀየሩ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች