ዓለም ላይ አንድ ተጨማሪ አገር ሊመዘገብ ይሆን?

ደሴቷ በቅኝ ገዢዎች ተይዛ ስለነበር ነዋሪዎች ለነጻነታቸው ትግል አድርገዋል Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ደሴቷ በቅኝ ገዢዎች ተይዛ ስለነበር ነዋሪዎች ለነጻነታቸው ትግል አድርገዋል

በፓፓዋ ኒው ጊኒ የምትገኘው ቦውጋይንቪል ደሴት ራሷን የቻለች አገር ትሁን በሚለው ላይ ሕዝበ ውሳኔ ሊካሄድ ነው።

ራሷን የቻለች አገር እንድትሆን አብላጫ ድምጽ ከተሰጠ፤ በዓለም የአገሮች ዝርዝር አንድ ተጨማሪ አገር ይመዘገባል ማለት ነው። ለዚህም የፊታችን ቅዳሜ 207,000 ሰዎች ድምጽ ይሰጣሉ።

ደሴቷ በቅኝ ገዢዎች ተይዛ ስለነበር ለነጻነታቸው ትግል አድርገዋል። ለዘጠኝ ዓመታት ከዘለቀ ጦርነት በኋላም ሰላም ሰፍኗል።

እሷ ማናት?፡ ማየትና መስማት የተሳናት የመብት ተሟጋችና የሕግ ባለሞያዋ ሃበን ግርማ

የብዙ ኢትዮጵያውያንን ህይወት እየቀየረ ያለው የተፈጥሮ ጥበቃ ስራ

ኢትዮጵያ አርባ በመቶ ዕፀዋቶቿን ልታጣ እንደምትችል ተነገረ

ደሴቷ ስያሜዋን ያገኘችው በ18ኛው ክፍለ ዘመን ከነበረ ፈረንሳዊ አሳሽ ነው። ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ የጀርመን ቅኝ ግዛት ነበረች።

በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወቅት አውስትራያ ደሴቷን ተቆጣጥራ ነበር።

ፓፓዋ ኒው ጊኒ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1975 ነጻነቷን ስትቀዳጅ ቦውጋይንቪል አንድ ግዛት ሆነች።

'ሪፐብሊክ ኦፍ ዘ ኖርዝ ሰለሞንስ' የተባለ ነጻ ግዛት የመመስረት እቅድ ቢኖርም፤ አውስትራሊያ ጉዳዩን ችላ ብላው ነበር። በቦውጋይንቪል በ20ኛው ክፍለ ዘመን የማንነት ጥያቄዎች መስተጋባት ጀምረዋል። መነሻው ቅኝ ግዛትን እና የምጣኔ ሀብት ብዝበዛን መቃወም ነበር።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ 1997 ላይ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጣልቃ ገብቶ ጦርነቱ አክትሟል

የራስ ገዝ አስተዳደር ለመፍጠር የተደረገው ጥረት ሲከሽፍ፤ ዘጠኝ ዓመት የወሰደ ጦርነት ተካሂዷል። በጦርነቱ መነሻ ላይ 13 በመቶ የሚሆኑ የደሴቷ ነዋሪዎች (ከ4,000 እስከ 20,000 የሚደርሱ ሰዎች) ሕይወታቸውን አጥተዋል።

1997 ላይ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጣልቃ ገብቶ ጦርነቱ አክትሟል። የሰላም ስምምነት ላይም ተደርሷል።

ምርጫው ሲካሄድ ነዋሪዎች ነጻ አገር ለመመስረት ወይም የተሻለ የአስተዳደር ሥልጣን ለማግኘት ይመርጣሉ። ሰፊ የአስተዳደር ሥልጣን ማግኘት አብላጫ ድምጽ ካገኘ ቦውጋይንቪል ደሴት የፓፓዋ ኒው ጊኒ አካል ሆና ትቀጥላለች ማለት ነው።

ነዋሪዎች አገር ለመመስረት ድምጽ ሰጥተው ፓፓዋ ኒው ጊኒ ውሳኔውን ካላከበረች ግን ዳግመኛ ግጭት ይቀሰቀሳል።

የሕዝበ ውሳኔው ውጤት የፊታችን ታህሳስ ይፋ ይደረጋል። ሂደቱን የሚመራው በቀድሞው የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር የሚመራ ኮሚሽን ይሆናላ።

Image copyright BOUGAINVILLE REFERENDUM COMMISSION
አጭር የምስል መግለጫ የፊታችን ቅዳሜ 207,000 ሰዎች ድምጽ ይሰጣሉ

የፓፓዋ ኒው ጊኒ ማዕከላዊ መንግሥት ሕዝበ ውሳኔውን በገንዘብ አልደግፍም ብሎ ነበር። ደሴቷ የአገሪቱ አካል ሆና እንድትቀጥል ያለውን ፍላጎትም አሳይቷል።

ደሴቷ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች በመሆኗ፤ የፓፓዋ ኒው ጊኒ ማዕከላዊ መንግሥት እንድትገነጠል አይፈልግም። ቦውጋይንቪል ደሴት ከተገነጠለች ሌሎች ግዛቶችም የእንገንጠል ጥያቄ ያነሳሉ የሚልም ስጋት አለ።

ደሴቷ ተገንጥላ አገር ከሆነች፤ በ10,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ላይ የተመሰረተች አገር ትሆናለች። ይህም ከሳይፕረስና ሊባኖስ በመጠኑ የሰፋች አገር ያደርጋታል። በሕዝብ ቁጥር ረገድ ደግሞ ከዓለም አገሮች አነስተኛ ነዋሪ ያላቸውን ዝርዝር ትቀላቀላለች።

አውስትራሊያ ደሴቷን በገንዘብ ከሚደግፉ አገሮች ቀዳሚ ናት። ከዚህ ቀደም የነበረውን ግጭት በማርገብም ተሳትፎ አድርጋ ነበር። ቻይና እና አሜሪካም የሕዝበ ውሳኔውን ውጤት በአንክሮ ከሚከታተሉ አገሮች መካከል ናቸው።

ተያያዥ ርዕሶች