በሙስና የተከሰሱት ኔታንያሁ ነገሩ "የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ" ነው አሉ

ቤንጃሚን ኔታንያሁ Image copyright AFP

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጉቦ በመስጠት፣ በማጭበርበር እንዲሁም እምነት በማጉደል ክስ ቢቀርብባቸውም፤ ከሥልጣናቸው እንደማይነሱ ተናገሩ።

ክሱን "የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ" ብለውት፤ "የውሸት ክስ እንዲያሸንፍ አልፈቅድም" ሲሉ ተናግረዋል።

ክሱ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሀብት ከናጠጡ ነጋዴዎች ስጦታ ተቀብለዋል፣ በመገናኛ ብዙኅን በጎ ገጽታ ተላብሰው ለመታየትም ያላግባብ ውለታ ገብተዋል ቢልም፤ ጠቅላዩ ግን "አገሪቱን በሕጉ መሠረት መምራቴን እቀጥላለሁ" ብለዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር የሙስና ክስ ይጠብቃቸዋል

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በሙስና ሊከሰሱ ነው

ኔታንያሁ፤ ፖሊሶች እንዲሁም ፍርድ ቤትም ጭምር "እያሴሩብኝ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። ክሱ ፖለቲካዊ አጀንዳ እንዳለውም ገልጸዋል።

"ምርመራው እውነታው ላይ ለመድረስ ሳይሆን እኔን ለማጥመድ ነው" በማለትም ምስክሮች እንዲዋሹ መደረጉን ተናግረዋል።

አቃቤ ሕግ አቪቻይ ማንደልብሊት በበኩላቸው፤ ማንም ከሕግ በላይ አይደለም፣ ሕግን ማስከበር የፖለቲካ ጉዳይም አይደለም ብለዋል።

ክሱ ይፋ የተደረገው አገሪቱ ሁለት ጊዜ ምርጫ ማካሄዷን ተከትሎ ነው። ባለፈው እሮብ የኔታንያሁ ተቀናቃኝ ቤኒ ጋንዝ፤ ጥምር መንግሥት ለመመስረት እንዳልቻሉ ተናግረውም ነበር። ክሱ ይፋ ሲደረግ አቃቤ ሕጉን እንደሚደግፉ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ፕሬዘዳንት ሬቩን ሪቭሊን፤ አገሪቱ ወደ ሦስተኛ ዙር ምርጫ እንዳትገባ፤ ሕግ አውጪዎች በቀጣይ 21 ቀናት እጩ ጠቅላይ ሚንስትር እንዲያሳውቁ ጠይቀዋል።

ኔታንያሁ የተከሰሰሱት በምንድን ነው?

አቃቤ ሕግ ማንደልብሊት እንዳሉት፤ ኔታንያሁን በሦስት የተለያዩ ጉዳዮች ክስ ያቀርቡባቸዋል። ክሶቹ፤ ኬዝ 1,000፣ ኬዝ 2,000 እና ኬዝ 4,000 ይሰኛሉ።

  • ኬዝ 1,000ኔታንያሁ በማጭበርበር እና እምነት በማጉደል ተከሰዋል። ከሀብታም ወዳጃቸው ሻምፓኝ፣ ሲጋራና ሌሎችም ውድ ስጦታዎች በጉቦ ተቀብለዋል ተብሏል። ኔታንያሁ ግን ስጦታዎቹ የወዳጅነት መግለጫ እንጂ ጉቦ አይደሉም ብለዋል። ጓደኛቸውም ምንም ስህተት አልተሠራም ብለዋል።
  • ኬዝ 2,000 በዚህ ላይም ኔታንያሁ በማጭበርበር እና እምነት በማጉደል ተከሰዋል። የዜና ሽፋን ለማግኘት ከጋዜጣ አሳታሚ ጋር ተዋውለዋል ተብሏል። አሳታሚውም ክስ ተመስርቶበታል። ሆኖም ግን ኔታንያሁና አሳታሚው አንዳችም ስህተት አልሠራንም ብለዋል።
  • ኬዝ 4,000ይህ ከሁሉም ክሶች ከባዱ ነው። ኔታንያሁ በጉቦ፣ በማጭበርበር እና እምነት በማጉደል ተከሰዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዜና ሽፋን ሲሉ አውራ የቴሌኮም ድርጅትን የሚጠቅም ሕግ አስተዋውቀዋል ተብለዋል። ሕጉ በባለሙያዎች የተደገፈ እንደሆነ የገለጹት ኔታንያሁ ግን ከተቋሙ ምንም ጥቅም እንዳላገኙ ተናግረዋል። ድርጅቱም ምንም አለማጥፋቱን ገልጿል።

የምንሊክ ሀገር አንኮበርና ታሪካዊ ቅርሶቿ

ሴቶችን የማያሳትፈው በሴቶች ላይ የሚመክረው ስብሰባ ቁጣ ቀሰቀሰ

ኔታንያሁ ፍርድ ቤት እስኪቀርቡ ወራት ሊወስድ ይችላል። አሁን ላይ ከሥልጣን መነሳትም አይጠበቅባቸውም። ክሱ እስኪጠናቀቅ ዓመታት ሊወስድም ይችላል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የፍርድ ቤት ሂደት እየተከታተሉ አገር መምራት እንደሚቸግራቸው ግን እየተነገረ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች