ዚምባብዌ አሥር ጎዳናዎችን በምናንጋግዋ ልትሰይም ነው

ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ Image copyright EPA

የዚምባብዌ ምክር ቤት በመላው አገሪቱ ከሚገኙ ጎዳናዎች አሥሩን በኤመርሰን ምናንጋግዋ ለመሰየም ቀርቦለት የነበረውን ጥያቄ ተቀበለ።

ጥያቄው የቀረበው የአገሪቷን ጎዳናዎችና ህንጻዎች አዲስ ስያሜ ለመስጠት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው።

ሙጋቤ ታማኝ አይደሉም ያሏቸውን ምክትላቸውን ከስልጣን አነሱ

ዚምባብዌ የነዳጅ ቁፋሮ ልትጀምር ነው

ዚምባብዌ እንዴት ሰነበተች?

በዚምባብዌ መንግሥት የሚተዳደረው 'ሄራልድ ሪፖርትስ' እንደዘገበው፤ የስያሜ ለውጡ የአገሪቱን ጀግኖች ለማስታወስ ያለመ ነው ተብሏል።

"የአገሪቱን ብሔራዊ ጀግኖች ለማስታወስ የተወሰደ እርምጃ ነው።"

ዚምባብዌ ውስጥ ጎዳና ከሚሰየምላቸው መካከል የቀድሞው የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ሰር ሰርትስ ካህማ እና የአንጎላ የቀድሞው ፕሬዘዳንት አጎስቲንሆ ኔቶ ይገኙበታል።

የዚምባብዌ ጊዜያዊ የመረጃ ሚንስትር የሆኑት ማንጋሊሶ ንድሎቩ ለ'ሄራልድ ሪፖርትስ' እንደተናገሩት፤ ጎዳናዎች ሲሰየሙ ሁሉም ማኅበረሰብ ውክልና ያገኛል።

"ጎዳናዎችን በመሰየም ሂደት ውስጥ የእያንዳንዱ ማኅበረሰብ ማንነትና ባህል እንደሚወከል ምክር ቤቱ ተገንዝቧል። እያንዳንዱ ማኅበረሰብ ታሪኩን መናገር፣ እምነቱን መግለጽ፣ ዓለምን የሚመለከትበትን መንገድ ማንጸባረቅም ይችላል" ሲሉ አስረድተዋል።

ስያሜያቸው ይቀየራል ከተባሉት ጎዳናዎች አብዛኞቹ የቀድሞውን የአገሪቱን የቅኝ ግዛት ታሪክ የሚያሳዩ ነበሩ።

ቀድሞ የነበረ ስማቸው በአዲስ ተተክቶ በትዊተር ይፋ ከተደረጉት ጎዳናዎች መካከል፤ ኢንተርፕራይዝ ሮድ፣ ካሜሩን ሮድ እና ኪርካማን ድራይቭ ይጠቀሳሉ። አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ዚምባብዌ በርካታ አንገብጋቢ ጉዳዮች እያሏት የጎዳና ስም መለወጥን ተችተዋል።

ተያያዥ ርዕሶች