"ፌስቡክ ለሂትለር ፀረ ሴሜቲክ ማስታወቂያዎችን ይፈቅድ ነበር"-ኮሜዲያን ባሮን ኮሀን

ብሪታኒያዊው ኮሜዲያን ሳቻ ባሮን ኮሀን Image copyright Reuters

ብሪታኒያዊው ኮሜዲያን ሳቻ ባሮን ኮሀን፤ ፌስቡክ በ1930ዎቹ ቢኖር ኖሮ ለሂትለር ፀረ ሴሜቲክ እምነቶች ማስተላለፊያ መድረኩን ያመቻችለት ነበር ሲል ተናገረ።

ኮሜዲያኑ ይህን የተናገረው ኒውዮርክ በነበረው አንድ መድረክ ላይ ነው።

በተጨማሪም ጎግልን፣ ትዊተርን እንዲሆን ዩቲዩብን የተቸ ሲሆን "ቅሉ የጠፋውን ነገር ሁሉ ለቢሊየኖች ያሰራጫሉ" ሲል ኮንኗቸዋል።

ግዙፍ የማህበራዊ ሚዲያ ተቋማትና የኢንተርኔት ኩባንያዎች በፖለቲካ ቅስቀሳ ዘመቻዎች ወቅት የተሳሳተ መረጃን እንዲከላከሉ ግፊቱ እየበረታባቸው ነው።

ትዊተር በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ከሕዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ማስታወቂያዎች አንደሚያግድ አስታውቆ ነበር።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይም ጉግል የፖለቲካ ማስታወቂያ እንዲለቀቅላቸው የሚፈልጉ አካላት የፍለጋ መረጃቸውንና [ጉግል ሰርችን] ሌሎች መረጃዎችን በመጠቀም "በንዑስ ተደራሽ" እንዲሆኑ ማድረጉን እንደሚያቆም አስታውቋል።

ጉግል የፖለቲካ ማስታወቂያዎች ላይ እገዳ ሊጥል ነው

ትዊተር የትኛውንም የፖለቲካ ይዘት ያለው ማስታወቂያ ሊያግድ ነው

“ከብሔርም ከሐይማኖትም በላይ ሰውነት ከሰሃራ በረሃ ስቃይ አውጥቶኛል"

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካላት ፌስቡክም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት እየተደረገ መሆኑን ይናገራሉ።

ባሮን ኮሀን የፌስቡክ መስራችና የበላይ ኃላፊ ማርክ ዙከንበርግን በመጥቀስ "ፌስቡክ ከከፈላችሁት የምትፈልጉትን የፖለቲካ ማስታወቂያ ያስተላልፍላችኋል። ውሸትም ቢሆን። ከዚህም አልፎ ያ ውሸት እያንዳንዱ ተጠቃሚ ጋር እንዲደርስ ማድረግና ከፍ ያለ ተፅዕኖ እንዲያመጣ ማድረግ ይችላል" ብሏል።

"በዚህ መሰረት ፌስቡክ በ1930ዎቹ ቢኖር ኖሮ ሂትለር፤ የአይሁዶች ችግርን እንዴት መፍታት እንደሚቻል የ30 ሰከንድ ማስታወቂያ ያሰራጭ ነበር"

ባሮን ኮሀን "ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ጥላቻን፣ የሴራ ትንተናና ውሸቶችን እንዴት እንደሚያሰራጩ ለማሰብና ለመነጋገርና መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ጊዜው አሁን ነው" ብሏል።

ዓለም አቀፍ የህግ አውጪዎች ስብሰብ በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ፣ የተወሰነ የማህበረሰብ ክፍልን ታላሚ ያደረገ የፖለቲካ ማስታወቂያ መቆጣጠሪያ መንገድ እስኪበጅለት ድረስ በማህበራዊ ሚዲያ አንዳይሰራጫ መታገድ አለበት ሲሉ ጥሪ አቅርበው ነበር።

የተሳሳተ መረጃና ሐሰተኛ ዜና ዓለም አቀፍ ኮሚቴ በበኩሉ፤ ማህበራዊ ሚዲያን የሚያንቀሳቅሱ አካላት የሚከተሉት የንግድ መርህ "ነገሮችን በማበጃጀት ትርፍ ማግኘት" መሆኑን ጠቅሰው ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ