ግሬታ ተንበርግ፡ ሰዎች 'የተቆጡ ሕጻናትን' ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ

ግሬታ ተንበርግ Image copyright AFP

የአየር ጠባይ ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ፣ አዋቂ ሰዎች ታዳጊዎችን በዓለም ሙቀት መጨመር ምከንያት "ማስቆጣታቸውን" ቢያቆሙ ይሻላል ስትል ተናገረች።

ተንበርግ ፖርቹጋል፣ ሊዝበን፣ ከመሄዷ በፊት በሰጠችው ቃለምልልስ ወቅት ላይ ነው እንዲህ ማለቷ የተሰማው። ግሬታ ተንበርግ ከፖርቹጋል በኋላ ወደ አሜሪካ ቨርጂኒያ እንደምታቀና ይጠበቃል።

" ሰዎች የተቆጡ ሕጻናትን አቅም ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ" ብላለች ለጋዜጠኞች።

የአየር ጸባይ ለውጥ ላይ የሚመክረው ስብሰባ ምን ይዞ ይሆን?

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል?

የ16 ዓመቷ ማድሪድ ወደሚካሄደው COP25 የአየር ጠባይ ጉባዔ እያቀናች ትገኛለች።

በዚህ ጉዞዋ በካይ ከሆኑ መጓጓዣዎች ራሷን ለመጠበቅ በአውሮፕላን ወይንም በመኪና ላለመጠቀም ወስናለች። ለአየር ንብረት መበከል ዝቅተኛ አስተዋጽኦ አላቸው በተባሉ መርከቦች ወደ ጉባዔው እንደምታመራ ታውቋል።

ከጋዜጠኞች አዋቂዎች የተቆጣች አድርገው እንደሚመለከቷት ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ " ተቆጥተናል፣ የተበሳጨነው ግን ለበጎ ምክንያት ነው" ብላለች።

"እንዳንቆጣ ከፈለጉ፣ የሚያስቆጣንን ነገር ከማድረግ መቆጠብ ነው ያለባቸው" ስትልም አክላለች።

ግሬታ የመጀመሪያ እቅዷ የነበረው በደቡብ አሜሪካ ቺሊ የሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነበር።

ነገር ግን በደቡብ አሜሪካ ሊካሄድ የታቀደው ጉባዔ በሀገሪቱ አለመረጋጋት ምክንያት ተሰርዟል። በዚህ ምክንያት የስብሰባው ስፍራ ወደ ስፔን ሲቀየር በመርከብ ለመሄድ መወሰኗ ተሰምቷል።

ግሬታ በዚህ ጉዞዋ ላይ ከአውስትራሊያዊ ዩቲዩበርና ከእንግሊዛዊቷ የመርከብ ቀዛፊ ጋር የምትጓዝ ይሆናል።

መርከባቸው የፀሐይ ብርሃንና ከውሃ የሚመነጭን ኃይል እንደሚጠቀም ታውቋል።

ግሬታ ተንበርግ በዘንድሮው የኖቤል ሽልማት ላይ እጩ እንደነበረች ይታወቃል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ