በቤተ ሙከራ ልብስ የቁንጅና ውድድር ያሸነፈችው አሜሪካዊት

የቁንጅና ተወዳዳሪዋ Image copyright Getty Images

ከቨርጂኒያ ግዛት የመጣችው ባዮኬሚስት የ2020 "እመቤት አሜሪካ" የቁንጅና ውድድርን አሸንፋለች።

ከቁንጅና ውድደር ጋር ተያይዞ የነበረውን አስተሳሰብ ውድቅ ያደረገ የኬሜስትሪ ቤተ ሙከራ ሥራዋን ለዳኞች ማቅረቧ ተመራጭ አድርጓታል። ይህን ያደረገችውም በውድድሩ መድረክ ላይ ነው።

ካሚል ሺራየር ያሸነፈችው ሐሙስ ዕለት ለመጨረሻ ዙር የቀረቡ 50 ቆንጆዎችን በመብለጥ ሲሆን በተለይ የሳይንስ ሙከራዋ የዳኞችን ቀልብ በመግዛቱ ተመራጭ አድርጓታል።

ከዚህ ቀደም አሸናፊ የሚሆኑት ከዳንስ ከሙዚቃ መሣሪያ ከትወናና ተያያዥ ተሰጥኦዎች ቢኖራቸው እንጂ ሳይንቲስቶች ሆነው አያውቁም።

የዩኒቨርስቲ መምህርቷ ሞዴል፡ "ውበት ባመኑበት ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው"

ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቋ ለምን ይጠቅማታል?

የትግራይና የፌደራል መንግሥቱ ግንኙነት በጣም አሳሳቢ ነው- ዶ/ር አብረሃም ተከስተ

ካሚል ሺራየር ግን ባልተለመደ መልኩ የቤተ ሙከራ ነጭ ጋውን ለብሳ ነው የቁንጅና አክሊል የደፋችው።

ካሚል የ50ሺ ዶላር የትምህርት ዕድልና አንድ ዓመት ደግሞ "እመቤት አሜሪካ" ሆና የበጎ አድራጎት ሥራ ውስጥ እንደምትቆይ ይጠበቃል።

ቁንጅና ውጫዊ ብቻ ተደርጎ የቆየውን ያረጀ ያፈጀ አስተሳሰብ ለመስበር ነው የባዮኬሚስት ሙከራዬን ያደረኩት ብላለች።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ካሚል ሺራየር የሀይድሮጂን ፐርኦክሳይድ የላቦራቶሪ ሙከራዋን በመድረክ ላይ ስታቀርብ

የቁንጅና እመቤቷ ካሚሊ ሺረር 2 የመጀመርያ ዲግሪዎችን በሳይንስ ያገኘች ሲሆን አሁን ደግሞ የዶክትሬት ዲግሪዋን በፋርማሲ ቨርጂኒያ ኮመንዌልዝ ዩኒቨርስቲ እየተከታተለች ነው።

ለዳኞቹ እንደተናገረችው የቁንጅና ተወዳዳሪዎች እውቀት የሚስተላልፉ መሆን አለባቸው ብላለች።

"እመቤት አሜሪካ" አክሊሉን ከደፋችበት ጊዜ ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያህል በበጎ አድራጎት ሥራዎች ትሳተፋለች። በተለይም የመድኃኒት አጠቃቀምን ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እንደምታተኩር ተነግሯል።

እንደ ፈረንጆቹ ከ2018 ጀምሮ የቁንጅና ውድድሮች በፓንትና ጡት መያዣ የሚታጀቡ እንዳይሆኑ ለማድረግ አዘጋጆች ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ከዚያ ይልቅ የአእምሮ አቅማቸውንና አስተሳሰባቸውን በሚያጎሉ ሁኔታዎች እንዲፈተሹ ሲበረታታ ነበር።

ባዮኬሚስቷ ካሚላ ሽራየር የሀይድሮጂን ፐርኦክሳይድ ውህድ ጋር የተያያዘ ሙከራዋን ለዳኞች አቅርባ ስትተነትንላቸው ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ