የ23 አመቷ ሴት የናይጄሪያ አየ ስርወ መንግሥትን ለመምራት 'ንጉስ' ሆና ተሾመች

የ23 አመቷ ንጉስ

የህክምና ተማሪ የሆነችው ታይዎ ኦየቦላ አጎብና የአባቷን ሞት ተከትሎ ያልተጠበቀና አስገራሚ ዜና ደርሷታል።

"የአካባቢው መሪዎች ከአማልክት ጋር የሚያገናኙ አዋቂዎችን ባማከሩበት ወቅት እኔ ንጉስ እንድሆን እንደመከሯቸውና፤ ዙፋኑንም እኔ መቆጣጠር እንዳለብኝ ተነገራቸው" በማለት ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ገልፃለች።

በደቡብ ምዕራብ ናይጀሪያ በምትገኘው ኦንዶ ግዛት ውስጥ ባልተለመደ መልኩ የአየ ስርወ መንግሥት ቀጣይዋ ንጉስ ለመሆን ተመርጣለች።

''ለ 12 ዓመታት ባልተደፈረው ቦክስ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ መወከል እፈልጋለሁ'' ተመስገን ምትኩ

ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ

የሃያ ሶስት ዓመቷ አየብላ ዜናውን መጀመሪያ ስትሰማ ማመንም ስላልቻለች ጆሮዋን ተጠራጥራ የነበረ ሲሆን ጉዳዩን በጥልቀት ለማጤንና ለማሰብ ያስችላት ዘንድ የሶስት ሳምንት ጊዜ እንዲሰጧት ጠይቃለች።

የትግራይና የፌደራል መንግሥቱ ግንኙነት በጣም አሳሳቢ ነው- ዶ/ር አብረሃም ተከስተ

በመጨረሻም ተስማማች፤ነገር ግን ዙፋኑን የምትቆጣጠረው በዘላቂነት ሳይሆን ስርወ መንግሥቱን የሚያስቀጥል ሌላ ወንድ እስኪመረጥ ድረስ ነው ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች