ሆንዱራስ በእስር ቤት ግጭቶች እየተናወጠች መሆኑ ተገለፀ

በሆንዱራስ እስር ቤት የተፈጠረው ግጭት Image copyright Reuters

በሆንዱራስ እስር ቤት በተፎካካሪ የተደራጁ ቡድኖች መካከል በተፈጠረ ግጭት አስራ ስድስት እስረኞች ተገድለዋል፤ እንዲሁም ሁለት ቆስለዋል።

ኤል ፖርቬንይር የሚል መጠሪያ ባለው በዚህ እስር ቤት በተነሳው ግጭት እስረኞቹ ሽጉጦች፣ ቢላዎችና ቆንጨራዎች እንደተጠቀሙ ተገልጿል።

በእስር ቤት በሚነሱ ግጭቶች እየተናወጠች ባለችው ሆንዱራስ ከሁለት ቀናት በፊትም በሌላ ወህኒ ቤት ግጭት አስራ ስምንት እስረኞች የተገደሉ ሲሆን አስራ ስድስትም ቆስለዋል።

በአሜሪካ ኒውዮርክ እስር ቤት ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ

የወህኒ ቤቶች ቀውስ አሳሳቢ በሆነባት ሆንዱራስ እስር ቤቶቹም ከመጠን በላይ በሰው በመሞላታቸው ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል።

እነዚህንም ግድያዎች ተከትሎ በሃገሪቱ ውስጥ በሚገኙ እስር ቤቶች ሁሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን፤ ነገሮች እስኪስተካከሉም የማዕከላዊ መንግሥቱ ፌደራል ፖሊስ የደህንነታቸውን ሁኔታ ይቆጣጠራል።

በማስታገሻ ብቻ የሚታከሙ እስረኞች

የቀድሞው ፕሬዝደንት ልጅ በጉልበት ብዝበዛ ወንጀል ተፈረደባቸው

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦርላንዶ ሄርናንዴዝ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ኤምኤስ 13 የሚባለው ቡድን አምስቱ አባላቱ በእስር እያሉ መገደላቸውን ተከትሎ ነው።

እንዲህ አይነት ግጭቶች ለምን እንደተነሱ ግልፅ ባይሆንም የመንግሥት የፀጥታ ኃይል ኃላፊ የሆኑት ሉዊስ ሱዋዞ የተደራጁ ቡድኖች አባላት የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት ለመቀልበስ ነው ብለዋል።

"ሟቾቹም ሆነ የቆሰሉት በጥይቶች እንዲሁም በስለታማ መሳሪያዎች ነው" በማለት የፀጥታ ኃላፊው ገልፀዋል።

ግብጻዊቷ ዘፋኝ አባይ ላይ ቀልደሻል ተብላ እስር ተፈረደባት

ምንም እንኳን የሆንዱራስ ወህኒ ቤቶች እስረኛ የመያዝ አቅማቸው ስምንት ሺ ያህል ቢሆንም፤ በሃገሪቷ ውስጥ ከሃያ ሺ በላይ እስረኞች አሉ ተብሏል።

በእስር ቤቶች ውስት በቡድን ተከፋፈሎ መጋጨት የተለመደ ሲሆን ይህም በእስር ቤት ውስጥ ያለውን ይዞታ ለመቆጣጠር የሚደረግ ሩጫ መሆኑም ተነግሯል።