በሞቃዲሾ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 76 ሰዎች ሞቱ

ሞቃዲሾ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ከሰዓት በፊት በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት በትንሹ 76 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። ዛሬ ጠዋት በርካታ ሰዎች ወደ ሥራ በሚሄዱበት ሰዓት ደረሰ በተባለው በዚህ የቦምብ ጥቃት ከሟቾች በተጨማሪ በርካቶች ቆስለዋል።

አደጋው የደረሰበት ይህ የሞቃዲሾ ክፍል ፍተሻ የሚደረግበትና በርካታ ሰዎች የሚንቀሳቀሱበት ነው።

የፖሊስ መኮንኑ ኢብራሂም ሞሐመድ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ፍንዳታው እጅግ አደገኛ ነበር።

የመዲና ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሞሐመድ የሱፍ ለአሶሽየትድ ፕረስ እንደተናገሩት 73 አስክሬኖች ተቀብለዋል።

ሳካሪ አብዱልቃድር የተባለ የአይንም ምስክር በበኩሉ "ማየት የቻልኩት እዛም እዚም የተበጣጠሰ የሰው አካል ነው፤ የአንዳንዱ ሰው ሬሳ በእሳት በመቃጠሉ መለየትም አይቻልም ነበር" ብሏል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

ዘግይተው እየወጡ ባሉ መረጃዎች ደግሞ የሟቾች ቁጥር ከተገለጸውም እጥፍ ሊደርስ እንደሚችል ይጠቁማሉ።

መሐመድ አብዱራዛቅ ተባሉ የምክር ቤት አባል የሟቾቹ ቁጥር 90 እንደደረሰ ያልተረጋገጠ አሀዝ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።