ዓይነ ስውሩ ሬዲዮ ጠጋኝ

ዓይነ ስውሩ ሬዲዮ ጠጋኝ

ሬዲዮ መጠገንን ከልጆቹ እኩል እንደሚወድ የሚናገረው መሐመድ በሙያው ከ30 ዓመት በላይ ቆይቷል። ስራውን እንደጀመረ ሰዎች ሬዲዮናቸውን ለማስጠገን አማራጭ ሲያጡ ብቻ ወደ እርሱ እንደሚመጡ የሚናገረው መሐመድ የሚጠግነውን ሬዲዮ ችግር በመነካካትና በማድመጥ ይለያል።